“ወያኔን መልሱልን!” የኦፌኮ ጥያቄ!

ኦፌኮ በወያኔ ናፍቆት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት እየገለፀ ነዉ። ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ በቀለ ገርባ “ወያኔ ምንም ጥፋት የለበትም። በወያኔ ላይ ሲነሳ የነበረዉ ክስ በአብዘኛዉ ውሸት ነበር። የተቃወምነዉ ተሳስተን ነዉ” ብሏል። እንግዲህ የእሬቻዉ እልቂት፣ የማዕከላዊዉ ሰበአዊ ሰቆቃ፣ የመስቀል አደባባዩ ግልፅ ግፍ፣ የእናት በልጇ ሬሳ ላይ መቀመጥ፣ በትግሉ ላይ የጠፋዉ የአምስት ሺ ቄሮ ህይወት፣ ነዲ ገመዳን ጨምሮ ድራሻቸዉ የጣፋ ታጋዮች፣ የሲዳማዉ የሎቄ ላይ እልቂት፣ የአኟ የጋምቤላ ላይ ጭፍጨፋ፣ በሶማሌ ክልል የተፈፀመዉ ሰቆቃ፣ የ1997 እና 1998 የአዲስ አበባ እልቂት፣ የጋዲሳ ህርጳሳ እና የተስፋሁን ጨመዳ በእስር ቤት መገደል ፣ የከፍያለዉ ተፈራ እግር መቆረጥ እና ሌሎች በወያኔ ዘመን የተፈፀሙ በደሎች በሙሉ ዉሸት ነበሩ ማለታቸዉ ነዉ! በጣም ይገርማል! ይህ የነፃነት፣ የዴሞክራሲ እና የፍትህ ታጋዩ-ፌዴራሊስቱ- ኦፌኮ ነዉ! ወያኔ ‘የቅዱሳኖች ሁሉ ቅዱስ ስለሆነ ወደ መንበሩ ይመለስ’ ይለናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ዝም ብሎ ይታዝባል! ቁምነገሩ ወያኔ ዳግም ላይመለስ በህዝብ ትግል መደምሰሱ ነዉ!

2 COMMENTS

  1. Bekele Gerba is the most selfish and short sighted person. As you have stated he is devaluing the suffering of Oromos and other Ethiopians for power grab. Unlike the majority of the prisoners he., of course, received preferential treatment while he was in jail because of his popularity and woyane’s strategy to provide him the best treatment for political consumption on international human right arena. But the preferential treatment he received by no means would represent even 1% of other political prisoners which he arrogantly claims. In short Mr Bekele is rude, liar, selfish and national embarrassment.

  2. I remeber the cry of all ethiopians upon the news bekeleGerba is going to lose his vision in prison. His duaghter was crying on VOA. What a stupid person he is!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.