የግብጽ እየተጠናከረ የመጣ ወታደራዊ ዝግጅት እና የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የአስዋንን ግድብ ታሳቢ ያደረገ ነው!? – ድልነሳው ጌታነህ

በአባይ ግድብ ላይ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ መሪዎች በኩል በሚሰራ የዲፕሎማሲ ስህተት ግብጽ ዓላማዋን ለማሳካት ጉልበት እንድታገኝ አድርጓታል። የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ከአምስት ዓመት በፊት ካርቱም ሱዳን ላይ የተፈራረሙት የግብጽ፣ኢትዮጵያ እና ሱዳን ብቻ ስምምነት አንዱ አጣብቂኝ ነበር። በዛ ስምምነት የቀሩትን የአባይ ተፋሰስ አገሮችን ያገለለ መሆን ብቻ ሳይሆን ካልተስማሙ ከመካከላቸው አደራዳሪ አገር መርጠው ድርድሩን ለመቀጠል የፈጠሩት ክፍተት አስቸጋሪ ነበር።

የጠ/ሚ/ር አብይ አስተዳደር አሜሪካን በግብጽ ጥያቄ በታዛቢነት ስም ሲቀበል ስህተት መፍጠሩን አምኖ በመጨረሻው የቀረበውን ስምምነት የግብጽን ጥቅም የሚያስጠብቅ ብቻ ሳይሆን የግድቡን ፕሮጀክት እንዳልነበር የሚያደርግ እና ስም ብቻ ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ውሳኔ ነው። ይህን ውሳኔ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ባለመገኘት እና እንደማትቀበል ኢትዮጵያ ከገለጸች በሁዋላ ለምንድነው ወደዚህ መድረክ የምትመለሰው? ይህ በአገር ላይ ክህደት ነው። ግብጽም የእሱዋን ጥቅም ለማስከበር የቆመውም ማንኛውም አስተዳደር ይህን በግልጽ እንዲረዱ ኢትዮጵያ ጉዳዩ የአፍሪካ ጉዳይ በመሆኑ ድርድሩን በአፍሪካ ህብረት ወይም በደቡብ አፍሪካ(ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄውን ቀደም ብለው ስላቀረቡ)ሊሆን ይገባል ማለት ይቻላል። ድርድሩን መሸፋፈን ብዙ አያዛልቅም። ስለዚህ ሌሎችን ከመክሰስ በፊት የራስን ሀላፊነት መወጣት ስልጣን ለያዘው አካል አግባብ ያላው ጥያቄ ነው። ግብጽ ሰሞኑን የምታደርገውን አባይ ግድብ ላይ ያነጣጠረ እንቅስቃሴ እና ወታደራዊ ዝግጅት ከግምት በማስገባት እስከ አስዋን ግድብ የዘለቀ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ስትራቴጂም ያስፈልጋል የሚሉ እየተደመጡ ነው። ተከታዩ ምልከታም እዚሁ ላይ ያተኩራል ነው። ያንብቡት

****************************************
በእስራኤልና በአረቦች መካከል በተደረገው የስድስቱ ቀን ጦርነት አስጊው የጦር ሀይል የግብፅ ስለነበር እስራኤል ጦርነቱን ለማሸነፍ ሁለት አማራጮች አስቀምጣ ነበር።አንደኛው አማራጭ ጦርነቱን በጦር ኃይል ውጊያ ማሸነፍ ሲሆን የመጨረሻው አማራጭ የነበረው እስራኤል በኣሮቦች ጦር የምትሸነፍ ከሆነ የመጨረሻው አማራጭ የነበረውን እስራኤል እንዳገር እንድትቀጥል የአስዋንን ግድብ መምታት/ማፈንዳት ነበር በወቅቱ በነበሩ የፖለቲካ ገምጋሚዎች መረጃ መሠረት።ደግነቱ እስራኤል ጦርነቱን በድል አድራጊነት በማሸነፏ የሁለተኛው አማራጭ ተግባር ላይ አልዋለም። ግብፅ የአባይን ግድብ በአየር ወይም በሌላ አማርጭ የጦር መሳሪያ ተመክታ ግድቡን ካፈረሰች የኢትዮጵያ መንግስትም ሶስት አማሯጮችን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል። የመጀመሪያው ቅድሚያው እርምጃ ቤት በቀል የሆኑ ባንዳዎች ላይ እርምጃ መወሰድ ሁለተኛው አማራጭ አርሶ አደሩ አባይን ለመስኖ አገልግሎት እንዲጠቀምበትና ገባር ወንዞችን እንደዚሁ ለመስኖ አገልግሎት እንዲጠቀሙበት ማድረግ።ሶስተኛውና የመጨረሻው አማራጭ ሁሉንም ጥረት ግብፅ ውድቅ አድርጋ ሃይልን እንዳማራጭ ወስዳ ዓላማዋ ኢትዮጵያን ማበርከክ ከሆነና ቀይ መስመር ካለፈች ግብፅ በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ላይ ከፍተኛ ስጋት የምታመጣ ከሆነ የአስዋን ግድብ ከጦርነቱ አማራጭ ውስጥ መኖር ይኖርበታል።

1 COMMENT

  1. ድል ነሳዉ ስምህ ይመሰክራል ዘር ይዉጣልህ ቅልብጭ ያለ ፕሮግራም መንግስት ሊከተለዉ የሚገባ ነዉ እንዳልከዉ እነ ጁዋር/በቀለ ገርባን/አህመዲን ጀበልን ዳዉድ ኢብሳን መራራ ጉዲናንና የቆሰሉ ትግረዎችን ይዞ ወደ ድርድሩ መሄድ ከቀልዶች ሁሉ የላቀ ቀልድ ነዉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.