በታሪክ ሚዛን:-ግርማዊነታቸውን እንዴት እንመዝናቸዋለን? – ታምሩ ገዳ

ኢትዮጵያን ከአራት አስር አመታት በላይ በፊውዳላዊ ስርአት ስር ያስተዳደሩት ግርማዊነታቸው ፣ቀደማዊ ኃይለስላሴ ስማቸው ዛሬም ድረስ በኢትዮጵያኖች ዘንድ በበጎ ሆነ በመጥፎ መነሳቱ አልቀረም።

የፈረንሳይ ቻናል 24 ቴሌቭዥን የኢትዮጵያው የመጨረሻው ንጉስ ሲታወሱ ባለው ልዩ ፕሮግራሙ ” የይሁዳ አንበሳ፣የአለም ብርሃን ” የሚል መጠሪያ ስያሜ የነበራቸው ግርማዊነታቸውን የተመለከቷቸው ኢትዮጵያን ከቀኝ ገዢዎች ቀንበር እንዳትወድቅ የታገሉ፣ ያታገሉ ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመሳሰሉትን በመቆርቆር በኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣኔ እንዲመጣ መንገድ የጠረጉ፣የአፍሪካ ህብረትን ያቋቋሙ ፣የእፍሪካ እና የካሪቢያን አገራት ከጭቆና እና ከባርነት ነጻ እንዲወጡ በአለም መድረክ ላይ ቆመው የተሟገቱ ለብዙዎች ተጽእኖ የፈጠሩ የሀያኛው ክፍለዘመን ታላቅ መሪ እንደሆኑ ይናገሩላቸዋል።

በተቃራኒው እኤአ 1974 በወታደራዊው ደርግ ከስልጣን የተወገዱት ፣የተሰሩት፣አሟሟታቸውም እስከ ዛሬ ድረስ አነጋጋሪ የሆነው ግርማዊነታቸው በስልጣን ዘመናቸው በአገሪቱ ሰሜናዊ አስተዳደሮች እኤአ 1958፣1966እና1973 ተከስቶ በነበረው ክፉኛ ድርቅ እና ረሃብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በረሀብ ምክንያት እንደ ቅጠል ሲረግፉ “እርሳቸው ግን የልደት በዓላቸውን ለማክበር ለፌሽታ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን ዶላር አውጥተው በፌሽታ ላይ ነበሩ” ሲሉ ትላንት፣ ዛሬም ይወቅሷቸዋል።

“ፈራጅ ታሪክ ነው” እንደሚባለው በፊውዳል ስርአት ውስጥ ተወልደው ዘመናዊነትን ፣ጸረ ቀኝ አገዛዝን ለህዝባቸው እና ለተቀረው የሶስተኛው አለም ያሰረጹት ፣ብዙ የተባለላቸው፣የተዜመላቸው፣በተቃሪው ደግሞ ለብዙዎች ህይወት መጥፋት፣ለህዝባዊ እምቢተኝነት እና የስርዓት ለውጥ ምክንያት የሆኑት የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉስ ፣ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዛሬም አድናቂዎች እና ተቺዎች ከአሁኖቹ እና የቀደሙት ገዢዎች ጋር በማነጻጸር ላለፉት ሰማኒያ አመታት የኢትዮጵያኖች አመለካከትን ከሁለት ጎራ ከፍለ ውታል።

(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

2 thoughts on “በታሪክ ሚዛን:-ግርማዊነታቸውን እንዴት እንመዝናቸዋለን? – ታምሩ ገዳ

  1. ታምሩ ገዳ ጠንቅቀህ እንደምታዉቀዉ አጼ ሐይለ ስላሴ ምንም የማይወጣላቸዉ አስተዋይ መሪ ነበሩ ስለሳቸዉ ክፉ ነገር የሚያወሩና የሚያስወሩ ጸረ ኢትዮጵዉያን በተለይም ወያኔዎች/ኤርትራዉያን እና እነሱ የፈለፈሏቸዉ ኦነግን የመሰሉ ድርጅቶች ናቸዉ። ዋናዉ አላማቸዉ የማይረሳዉን የህዝብ ፍቅረ ከእሳቸዉ ቀምቶ የራሳቸዉ ለማድረግ የታሰበ ነዉ። አጼ ሐይለ ስላሴ በዘመናቸዉ ተስፈንጣሪ ተራማጂ ተብለዉ በመሳፍንቱ አካባቢ በጥርጣሬ ሲታዩ የነበሩ መሪ ናቸዉ። ብዙ መቶ ሺህ ሰዉ ሞተ ያልከዉ በወቅቱ 30000 ረሀብተኞች ነበሩ ለዚህ ደግሞ አጼ ሐይለ ስላሴ ብቸኛ ተጠያቂ መሆን አልነበረባቸዉም።
    በደርግና በትግሬዎች አገዛዝ በረሀብ ሳይሆን በጥይት የረገፈዉ ቤት ይቁጠረዉ ረሃቡ እንዳለ ሁኖ። ይህን አያይዞ በሁለቱ ትግሬዎች ጥጋብ ምክንያት በሰሜኑ ጦርነት ያለቀዉን ኢትዮጵያዊም አትርሳዉ። አጼ ሐይለ ስላሴ በስደት በነበሩበት ጊዜ የግል ንብረታቸዉን የሸጡ ብቸኛ ንጉስ ነበሩ። ዛሬ አንድ ተራ ትግሬ ምን ያህል ንብረት በዉጭ ሀገር እንዳከማቸ እንደ ጋዜጠኛ ጠንቅቀህ የምታዉቅ መሰለኝ።

    በዳግማዊ ምንሊክ ጊዜ የስልጣኔ ብልጭታና ጅማሮ ቢደረግም የተተገበረዉ በአጼ ሐይለ ስላሴ ጊዜ ነበር። እኝህ ንጉስ በዘመናቸዉ በትልቅ ጥበብ ኢትዮጵያዉያንን ያስተዳደሩ ብዙ ያልተባለላቸዉ ንጉስ ነበሩ። የሚያሳዝነዉ የኢትዮጵያ ተማሪዎች የሻቢያና የአረብ መጠቀሚያ ሁነዉ ነገሩን ባለማስተዋል ምስቅልቅሉን አወጡት ከአጼ ሐይለ ስላሴ ይልቅ ስለነዚህ የህዝብ ጠላቶች በድፍረት መዘገቡ መልካም መሰለኝ።

  2. ሰው የሚመዘነው በኖረበት ዘመን ነው። ዛሬ ላይ ቆመው የአጼውን መንግሥት ጭቃ የሚቀቡ ሁሉ የደንቆሮ ጥርቅሞች ናቸው። ኢትዪጵያ በታሪኳ ታፍራ፤ ተከብራና በዓለም ላይ እኩል መሆኗ የተረጋገጠው በጃንሆይ ዘመን ነው። ዛሬ ሰው ገድሎ ወይም ሰርቆ የሚሮጠው በጥይት ተኩስ እንኳን አይቆምም። ነበረ ያኔ “ወድቃ በተነሳቸው ባንዲራ” በሃይለስላሴ ስም ቁም ሲባል ገዳይና ሰራቂው ሁሉ የጊዜው ደብተራ እንደ ደገመበት ባለበት ቀጥ ይል ነበር። እንዲህ ሲባል ስህተት አልነበረም ማለት ግን አይደለም። ያኔም ግፍ ነበር አሁንም ግፍ አለ፤ ወደፊትም ይኖራል። ይሁን እንጂ ሻቢያና ወያኔ እንዲሁም ደርግ ካደረስቱ ግፍ ጋር የዘውድ አገዛዝ ያደረሰው መከራ ሲነጻጸር ፊውዳል፤ ጨቋኝ አድሃሪ ይባል የነበረው የቀ.ኃ.ሥ መንግሥት መልዕአክ ነበር ማለት ይቻላል። እያፈረስን ስንሰራ፤ እየሰራን ስናፈርስ፤ እየገደልን ስንገዳደል የኖርን ህዝቦች ነን። የዛሬውም የትናንትናውን የሚመስል መልክ አለው። ባጭሩ ፓለቲካና ፓለቲከኞች እስከመቃብር ነጻ እናወጣሃለን የሚሉትን ህዝብ ነጻ ሳያወጡ ለራሳቸውና ለዘሞዶቻቸው ዘርፈው አዛርፈው በድሎት የሚኖሩ ድውያኖች ናቸው። የህዝብ ስም መሸሸጊያ፤ የነጻነት ትግል የባርነት እንደሆነ አይናችን እያየ ነው። ይባስ ተብሎ አሁን ደገሞ ክልልህ አይደለም ውጣልኝ በማለት አንገቱን የሚቀላበት የእብዶች ሃገር ነው። የሰው መለኪያው ሰው መሆኑ ቀርቶ በዘሩና በቋንቋው የሚመዘንበት የሙታን ፓለቲካ። ቋንቋ መግባቢያ ነው። የግድ ግን ቋንቋየን ካላወቃችሁ ጨውና በርበሬ አትገዙም የተባለበት ሃገር በሃበሻው ምድር ብቻ ነው። መረጃ ካስፈለገ አቶ በቀለ ገርባን መጠየቅ ነው። በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የቋንቋው መምህር አሁን ደግሞ ወያኔ እኔን አልደበደበኝም በማለት ለወያኔ ወገቡን ይዞ ሲታገል ማየት እጅግ ያንገፈግፋል። ስንቶቹ የኦሮሞ ልጆች ናቸው የተገደሉት። ስዬ አብርሃ ከሥር ተፈትቶ እስር ቤት እንዴት ነው ሲባል ” እስር ቤቱ ሁሉ ኦሮምኛ ይናገራል” ያለውን አቶ በቀለና ወያኔ ይሻላል የሚሉን የውሻ ፓለቲከኞች አልሰሙት ይሆን? ግን የፓለቲካ አውቆ አበዶችን ምንም አይነት መድሃኒት ፈውስ አይሰጣቸውም።
    ከንጉሱ በህዋላ ኢትዮጵያ እውቅ ልጆቿን ያጣችበት፤ ሰው እንደ ቅጠል የረገፈበት። 17 ዓመት የመከራ ዶፍ ሲያዝንብ ቆይቶ አንዲት ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀር ብሎ እንዳላፏከረ እግሬ አውጪኝ በማለት ሃራሬ የገባው መንግሥቱ የዘርና የጎሳ ፓለቲከኞችን ወያኔና ሻቢያን በምትኩ ተክቶ ነው። ከዚያ በህዋላ የሃገሪቱ እድል ፈንታ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ እንጂ የመከራ አውድማ ናት። ስለሆነም ንጉስንና መንግሥታቸውን የሚያጣጥሉ ሰዎች ቆም ብለው ማየት የሚኖርባቸው የጊዜውን የዓለም የፓለቲካ አሰላለፍ፤ የሰውን ንቃተ ህሊና፤ የባላባታዊ ስርዓት የሚያመነጨውን የፓለቲካ ጫና በማገናዘብ ሊሆን ይገባል። ንጉሱ ሰርቁ፤ የህዝብ ገንዘብ ዘረፉ የሚባለው ወሬ ነው። ወያኔ በ 27 ዓመት የዘረፈው በአንድ ጥናት እንዳየሁት 75-150 ቢሊዪን ዶላር ነው። ምንጭን ከወራጅ ወንዝ ጋር ማወዳደር አይቻልም። ሃገሪቱ በቁማ የተበላቸው በወያኔ ዘመን ነው። አንድ ነገር ልበልና ላቁም
    ጊዜው ወያኔ አዲስ አበባ የገባበትና ግርግር የበዛበት በዚህም በዚያም ነገሮች እየተዘረፉ የሚወሰድበት ጊዜ ነበር። በዚህ መካከል የአንበሳ አውቶብሶች ይጠፋሉ። ከዚያ ከወራታት በህዋላ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ አንድ አውቶብስ ሰው ጭኖ ይመጣል። አዲስ አበባ ደርሶ ሰውን ካራገፈ በህዋላ ችግር ይገጥመዋልና ወደ አንበሳ አውቶቡስ ጋራጅ ለጥገና ይገባል። ጠጋኙ መካኒክ የመኪናውን የሞተር መለያ ቁጥርና ሌሎችንም ነገሮች ሲያመሳክር ከጠፉት አውቶብሶች አንድ መሆኑ ያውቃል። ግን ቀለም ተቀብቶ መቀሌ ታርጋ ተለጥፎበታል። አፉን ዘግቶ ጠግኖ ይሰጣል። ያለዚያ ሞት ይመጣልና። ያልተሰራ ግፍ የለም። ግን ፓለቲካውም ሰውም የደነዘዘ በመሆኑ ለመኖር እንጂ ሌላ ሃሳብ የለውም። የንጉሱ ዘመን ከደርግ ከወያኔና ሻቢያ ዘመን በሚሊዪን ጊዜ ይሻላል። ንጉሱ መልካም ሰው ነበሩ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.