በገዳ ኮንስትራክሺን ጉዳይ የነ ታከለ ኡማ አስር ቦታ መርገጥ – ግርማ ካሳ

አዲስ ፎርቱን የአዲስ አበባ ፕሮጀክት ለቻይናው ኩባኒያ CCCC እንደተሰጠ ዘግቦ ነበር። ዋናው ኮንራትክተር የቻይናው ኩባኒያ ቢሆንም ከቻይናው ኩባንያ ጋር የሚሰራ ሌላ የአገር ውስጥ ኩባኒያ የፕሮጀክቱን የተወሰኡ ስራዎች እንዲሰራ ፣ ያለ ጨረታ ተመርጦ ስራ ጀምሯል። ይህ ኩባኒያ የገዳ ኮንስትራኪሽን ነው ( የአባይን ግድብ ፕሮጀክት ሳሊኒ ዋናውን ስራ ሲይዘው ሜቴኮም የተወሰነው ይዞ እንደነበረው)

የገዳ ኮንስትራኪሽንን ያለ ጨረታ መመረጡት ተከትሎ ጥያቄዎች በሚነሱበት ጊዜ ፣ እነ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ፣ “ገዳ” የሚለውን ፅሑፍ ፍቀው፡ ፕሮጀክቱ የሚሰራው በቻይና ተቋም ነው የሚል መልስ ሰጡ።

ተቃውሞዎችን መቋቋም ሲያቅታቸው ደግሞ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሹመኞች ጭራሽ “የገዳ ጠቅላላ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” አናውቀውም እስከማለት ደረሱ።

ይሄ ብቻ አይደለም ኢንጂነር ታከለ ፣ ሙሏለም አብርሃ በርሄ የሚባል የአንድ የትግራይ ተወላጅ የአዲስ አበባ ነዋሪ መታወቂያ ለጥፎ ፣ “ገዳ የሚል ፅሁፍ የሸፈነው ይሄ ግለሰብ ነው” በማለት፣ ግለሰቡ ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ እንዲታሰር አድርጓል። “ገዳ ኮንስትራክሽን በሚል የተመዘገበ ድርጅት የለም፤ ባልተመዘገበ ንግድ ፈቃድ የሚንቀሳቀሰው ነው አይታወቅም” የሚል መስተዳደሩ ማስራጨት ጀመረ።

ሆኖም በኦሮሞ ክልል የንግድ ፍቃድ የተሰጠው ገዳ የሚባል ድርጅት እንዳለ በይፋና በሰነድ ተገለጸ። ኢንጂነሩም እስከ አሁን ለሰጠው የተዛባና የዉሸት መረጃ ማብራሪያ አልሰጠም። ሕዝብንና በግፍና ያሰረውን አቶ ሙለዓለምን ይቅርታ አልጠየቀም። ምንም እንኳን ኢንጂነሩ የለጠፈው አስነዋሪ ጦማር ቢያነሳም፣ ፍርድ ገምድል በሆነ መልኩ ግን ያሰራውን ግለሰብ አሁን በወህኒ ቤት ይገኛል።

ይህ የኢንጂነር ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ መስተዳደር እርስ በርሱ የሚቃረን መግለጫ የሚያመላክተው ሰዎች ውስጥ ውስጡን እያጭበረበሩና እየዋሹ መሆናቸውና የሚስሩት ስራ ሲጋለጥባቸው መደናበራቸውን ነው።

የገዳ ኮንስትራክሹን ሕጉን ተከትሎ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ከሌሎች ጋር ተወዳድሮ በአገሪቷ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ የመሳተር መብት አለው። ሆኖም ግን ከሕግ ውጭ፣ የሕዝብን ገንዘብ ለመመዝበር መንቀሳቀስ ግን ወንጀል ነው።፡ኢንጂነር ታከለ ኡማ በግልጽ መጠየቅ አለበት። ከሕግ ውጭ ሊሆን አይችልም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.