አቶ ልደቱና የ”ሻሞ” ፖለቲካ “አሸናፊነት= ዲሞክራሲ + ነጻ አውጭነት” – ጌቱ ለማ ሸዋንግዛው

ጌቱ ለማ ሸዋንግዛው (ከአርባ ምንጭ)—ክፍል ሁለት

ሻሞ ማለት ሰዎች ለሁሉም ሊበቃ የማይችል፣ በአይን የሚታይ ነገር ለሽሚያ የምናቀርቡበት ወይም በሽሚያ የሚገኝበት፣ ባብዛኛው በልጆች የሚከወን መከፋፈያ መንገድ ነው ፡፡ ይህ ደግሞ በውድድር የሚገኝ ሳይሆን መሰረቱ ጉልበት ወይም/እና እድል ነው/ናቸው፡፡ ታዲያ የህዝብን ድምጽ እንዴት ለሽሚያ እንደሚቀርብና እንዴትስ  ዲሞክራሲያዊ ሊሆን እንደሚችል ተንባዩ ተብዬው ብቻ የሚያውቀው ይሆናል፡፡ ሻሞ ካሉት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ስለሚገኝ ድምጽ የሚያወራ ተግባር ሊሆን ፍጹም አይሆንምና ገና ከጅምሩ ትንበያ የተባለው ነገር በስህተት መነሳታቸውን ያመለክታል፡፡

የሳቸውን እንዳለ ወስደን ድምጽ  የሚሻሙት(ባይቻልም) መቶ ምናምን የኛ ፓርቲዎች እንደሆኑ እንገምታለን፡፡ ማነው የሚያሻማው? ህዝቡ? የምርጫ ቦርድ? ወይስ ሌላ፡፡ አቶ ልደቱን እንደ የድምጹ ባለቤትና አሻሚ ናቸው ብለን ብንወስድ 273 ድምጽ የት ደብቀው ነው 274 ብቻ የሚያሻሟቸው? ዛሬም ከወዲሁ ከኮሮጆ ግልበጣ  ጋር ተያይዞ የታሰበ ነገር ይኖር ይሆን? ጠርጥር አለ የቡግና ልጅ!

አቶ ልደቱ የፓርቲ አባል እስከሆኑ ድረስ ፓርቲያቸውም ሆኑ እሳቸው የሚወዳደሩት ለማሸነፍ ነው፡፡ ገና የፓርቲዎችን ፕሮግራሞች በውል ሳናውቀውና ሳናመዛዝን፣ ማንን በእጩነት እንዳቀረቡ ሳይረጋገጥ ለራሳቸው ጭምር ውጤት የሰጡበት አላማው ዝም ብሎ ቅንነት ወይም ስሜት ብቻ ነው ለማለት ይከብዳል፡፡ ሌላው ቢቀር የሳቸው ፓርቲ አባላት በዚህ የሻሞ ፖለቲካ ምን እንደሚሉ መስማት እንሻለን፡፡

ውጤት ተንባዩ ወይም ጠንቋዩ ቀደም ሲል ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለኢትዮጵያ የብሄር አደረጃጀት አይጠቅማትም ሲሉን ነበር የከረሙት፡፡ ዛሬ ደግሞ ጭራሽኑ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ከሆነ በነጻ አውጭነት ያሉ ፓርቲዎች ህዝቡ ይመርጣቸዋል  ይሉናል-በዚህ የሻሞ ፖለቲካ ድርሰታቸው፡፡ በሻሞ ትንበያ መሰረት ነገሮች እውን ቢሆኑ ህዝቡ የብሄር አደረጃጀትን ጠቃሚ ነው ብሎ መርጧል ማለት ነው፡፡ የቀድሞ አቋምዎን ከምርጫ ትንበያዎና ከህዝቡ ፍላጎት ጋር እንዴት እንደተላተመ ቢመለከዩትና ላልገባንም ቢስረዱን ሸጋ ነው፡፡

ለማንኛውም ከአቶ ልደቱ የትንበያ ዋና መነሻ ብለው ካሉት መመዘኛ ተነስቼ ውጤት ለመስጠት የተጠቀሙበት ቀመር ሲጠቃለል የሚከተለውን ይመስለኛል፡

“አሸናፊነት= ዲሞክራሲ + ነጻ አውጭነት”

በዚህ ፎርሙላዎና የአክራሪ ብሄረተኞች አሸናፊነትን ትንበያዎ ተነስተው ወደፊት በነዚህ ኃይሎች ለኢትዮጵያ ምን አይነት ስርዓት እንደሚዘረጉና እንዴትስ ህዝቡን እንደሚመሩት በነካ እጅዎ ሌላ ጥንቆላ የሚመስል ቅዠት እንደሚያቀርቡልን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ዘዴዎች ፕሮግራማቸውን በሰፊው ለህዝብ ባላስተዋወቁበት፣ ቅስቀሳ ባልተደረገበት ህዝቡ በደመነፍስ እከሌን ይመርጣል ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ መረጃና ማስረጃ በሌለበት ዜጋን ወደማጎሪያ እንደመውሰድ ይቆጠራል፡፡ ያ ብቻ አይደለም ዜጋውን በሌለው መረጃ፣ በደመነፍሳዊ ውሳኔ እከሌን ይመርጣል፣ ያኛውን ይጥላል ማለት ህዝቡን ምን ያህል እንደናቁት ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ ልብ በሉ ሲነሱ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ከሆነ ማን ያሸንፋል በሚል ነው መልስ አግኝቻለሁ ያሉን፡፡ ለምሳሌ አብሮነት የተባለው የርሳቸው ፓርቲ የትና መቼ ነው ከህዝቡ ጋር የተገናኛችሁት፡፡ ሳናውቅዎ እንዴት አዲስ አበባ ላይ መረጥንዎ፡፡ ትንበያ ህዝብን መጠየቅ አቅርቦ ነው የሚሰራው፣ ህዝቡ ደግሞ እገሌን እመርጣለሁ ብሎ ምላሽ የሚሰጠው ፓርቲዎችን ዝም ብሎ በስማቸው ሳይሆን ባለቸው ፕሮግራም ነው፡፡ ከፈረሱ ጋሪውን አስቀድሞ እንዲህ መሸምጠጥ ይቻል ይሆን፡፡ ሲበዛ ይገርማል!

በመጨረሻም ህጋዊና ምክንያታዊ የነበረውን ቅቡል መንገድ ስቶ በዚህ ዐይነት ኢ-ሳይንሳዊ ቀመር አስተዛዛቢ ድምዳሜ ላይ መድረስ ከትርፉ ኪሳራው ያመዝናል፡፡ ያሳፍራልም፡፡  የጥናት ሥራ መሰረታዊ መርህንና አካሄድ(ፕሮሴጀር) የጣሰ፣ ኢትዮጵያን የሚያህል ሰፊ አገር በአጭር ጊዜ  በግል አጥንቶ ማጠናቀቅ “የቻለ” ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ብቸኛው ሰው ስለሆኑ የሚመለከተው የምርምር ተቋም “ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት” መንገድ ቢያመቻችላቸው ብዬ ብናገር እርስዎም ጭምር እንደሚስቁብኝ በመገመት ያቀረቡት ትንበያ ኢሳይንሳዊ የሆነና እኛንም  ወደ ሻሞ ፖለቲካ ሊያሻግሩን የወጠኑት ማደናገሪያ አጀንዳ ነው ብዬ ሃሳቤን  እቋጭቻለሁ፡፡

ሰላም እንሁን

 

3 COMMENTS

 1. When it comes to
  -forming a transitional government.
  – finding abducted students.
  -resettlling the internally displaced Addis Ababa , Merkan GURAGE , GEDEO…. people back to their homes.
  – granting Sidama the Statehood status.
  – Badme Ethio-Eritrea , Sudan-Ethiopia , Somalia-Ethiopia and other border issues the “dynamite” PP chairman , Masters in Business Administration holder Dr. Abiy got no time to act due to the Covid-19 emergency , but when it comes to selling Ethiopian national interests without the approval of Ethiopians, the MBA holder Abiy finds ample times to do so despite the pandemic because his signature “telecom privatization” attempts will be profitable to his personal finances , while Lidetu Ayalew the member of the Privatisation Advisory Council opposing this plan got labeled as traitor , with Abiy who is selling the Ethiopian telecom to foreigners is treated as a hero.
  ever since MBA holder Dr. Abiy got to power he got his eyes on selling The Ethio-Telecom , Ethiopian Airlines , Ethiopian shipping lines and alike now Abiy is ready to sell the Ethio-Telecom before September comes so he makes his personal financial status prosper by making this shady deal of selling Ethio telecom during this times of State of emergency.

  Ethiopia Moves to Open Phone Industry to Investors

  AllAfrica.com › stories
  Web results
  Ethiopia: Government Privatisation Advisory Council Forms and Meets …

 2. The women diasporas donated the majority of the money to Abiy’s trust fund without their husbands approval , now the women diaspora who have given money to PP trust fund are spying conspiring with many of the Ethiopian embassies against their own husbands and family members because the women are blaming their husbands and brothers for the failure of the trust fund with the money being looted used to buy bullets to kill poor Ethiopians.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.