በሕወሐትና በማዕከላዊ መንግስት መካከል የተካረረው ውዝግብ እንዴት መፈታት አለበት? ለጉዳዩ ህጋዊና የሀይል አማራጮችን የሚዘረዝሩ ባለሙያዎችን አነጋግረናል

– በህገመንግስት ትርጓሜ ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ላይ ሀሳባችንን እንድናቀርብ አልተጋበዝንም ሲሉ የትግራይ ክልል የጠበቆች ማህበር ቅሬታውን ለዋዜማ ተናግሯል። ከማህበሩ መሪ ጋር አጭር ቆይታ አለን
ሌሎች ዘገባዎችም ተካተዋል

በሕወሐትና በማዕከላዊ መንግስት መካከል የተካረረው ውዝግብ እንዴት መፈታት አለበት?

የዋዜማ ዜና መፅሄት-በሕወሐትና በማዕከላዊ መንግስት መካከል የተካረረው ውዝግብ እንዴት መፈታት አለበት? ለጉዳዩ ህጋዊና የሀይል አማራጮችን የሚዘረዝሩ ባለሙያዎችን አነጋግረናል።- በህገመንግስት ትርጓሜ ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ላይ ሀሳባችንን እንድናቀርብ አልተጋበዝንም ሲሉ የትግራይ ክልል የጠበቆች ማህበር ቅሬታውን ለዋዜማ ተናግሯል። ከማህበሩ መሪ ጋር አጭር ቆይታ አለንሌሎች ዘገባዎችም ተካተዋል

Posted by Wazema Radio ዋዜማ ሬዲዮ on Monday, May 25, 2020

3 COMMENTS

 1. ሃይል አማራጭ አይደለም። ወንድምና እህቶቻችንን ገድለን የምንፎክርበት ጊዜ ወቅት ሽሮታል። የዓለም መሳለቂያ ለመሆን ካለሆነ በስተቀር በሃይል የሚመጣ ለውጥ ሌላ ሃይል ያሽቀነጥረዋል። ይህ ሲባል ወያኔ ተንኮለኛ አይደለም። የአብይ መንግስትም ጽድቅን የተላበሰ ነው ማለት አይደለም። ፓለቲካና ፓለቲከኞች እውነትን ከውሸት ጋር እየቀየጡ ሰው ሲያጫርሱ እንደነበሩና እንዳሉ ያለፈና የአሁን ታሪክ ይመሰክራል። አሁን በዓለም ሰዎች በነጻነት ዙሪያ እኛን ስሙና ምሰሉን የሚሉን ሁሉ እልፍ ሰዎችን የገፈተሩና መከራ ያደረሱ ለመሆኑ የየሃገራቸው የታሪክ ማህደር ይመሰክራል። ዛሬ በሊቢያ/ በሶሪያ/በኢራቅ/በየመንና በሌሎችም ሃገሮች እሳት በመለኮስ የነበሩ መንግስታትን ፍርክርካቸውን በማውጣት ጠበንጃ አንጋችና የእምነት አክራሪዎች የሚንጋጋባት ሰላም ከቤት እስከ ጠረፍ የጠፋባቸው ሃገሮችን እንዲሆኑ ያደረጉት እነዚሁ አጥፊ ሃይሎች ናቸው። የትግራይ ህዝብ በሁለት ሙታን ሃይሎች ገመናውን ያየ ህዝብ ነው። በደርግና በወያኔ። እንደገና ወደ ጦርነት የሚገባበት ያለፈው 45 ዓመታትን ምን አትርፎበት ነው? ንጽህ ውሃ እንኳን ማቅረብ የማይችል ነጻነት እውን ነጻነት ነውን? ታዲያ ዛሬ ወያኔን ከፌዴራል መንግስቱ ጋር እንዲላተም በዚህም በዚያም የፈጠራና የቀጥታ የጦርነት ታንቡር የሚመቱ የውሸት ቱልቱላዎች ረጋ ብለው የህዝባችንን ሰቆቃ መመዘን አለባቸው። ወያኔም መደንፋቱን ያቁም። ጦርነት የመሰልጠን ምልክት አይደለም። ሁልጊዜም እናሸንፋለን እያሉ መደንፋትም ትገቢ አይደለም። የሮምን አወዳደቅ የወደቀው ደርግ ለዚህ ትምህርት ሊሆን ይገባል። ጦር ሰብቆ ኑና ግጠሙን ማለት የፓለቲካ ወስላቶች የስልጣን መሰንበቻ ብልሃት ነው።
  በመሰረቱ ከወደ አስመራም ሆነ ከአዲስ አበባ ወያኔን አጠቃለሁ በሚል ሂሳብ የትግራይን ህዝብ ለሌላ መከራ መዳረግ በዘር ላልተሰለፈ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማይዋጥ የፓለቲካ ስሌት ነው። ስለሆነም ነገሩ እንዲረግብ ወያኔ ረጋ ባለ መልኩ የትግራይን ህዝብ ፍላጎት በማዳመጥ ሥልጣን በቃኝ በማለት የዘረፉትን ይዘው በሃገርም ሆነ ከሃገር ውጭ እንዲኖሩ መንግሥት ነገሮችን ቢያመቻች መልካም ነው። ጦርነት የእብዶች ግብግብ ነው። የትግራይ ህዝብ ጦርነት አይፈልግም። የወያኔን ከጀርባው መውረድ እንጂ! ስለዚህ እናንተ ምሽግ ውስጥ ሆናችሁ የድሃ ልጆችን በግድም ሆነ በፍቃድ ዳግም ለእሳት መዳረግ በሰማይም ሆነ በምድር ከሃላፊነት አያስመልጥም። መገዳደል በቃ። የዓለም መሳለቂያ መሆናችን ያብቃ። እርስ በርሳችን እንድንተላለቅ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ አይዞአቹ የሚሉን ሁሉ በዲሞክራሲ ስምና በአረብ ጸደይ ሰበብ ሃገርን አፈራርሰው ሌላውን ለማፍረስ የሚሮጡ ሃይሎች ናቸው። የሚከፋው አሁን ደግሞ የቻይና በ54 የአፍሪቃ ሃገሮች የቅኝ ግዛት ሰንሰለቷን መዘርጋቷ ተጨማሪ ውጋት ለጥቁር ህዝብ ሆኖአል። የጥቁር ህዝቦች አንድነት ናፈቀኝ። በሃገርም በውጭም እንደ እንስሳ እየታደኑ መገደል ለማቆም፤ በዘርና በጎሳ በቋንቋ ሰበበ እርስ በርሳችን መገዳደልን አቆመን ድንበር ተሻጋሪ ሃሳብ ይዘን ሰውን በሰውነቱ መዝነን መተቃቀፍ ካልቻልን የዛሬው ዜና ነገና ተነገ ወዲያም ተደጋሚ ነው። ሞቱና ተራቡ! በቃኝ!

 2. >>> ሃይል አማራጭ አይደለም።

  Wrong !

  If your opponent leaves you no other alternative, you have to use force !

  Ethiopians could remove TPLF from power 2 years ago only by using force, because TPLF didn’t allow peaceful struggle. TPLF killed,arrested, silenced and forced into exile those who struggled peacefully.

  >>> ይህ ሲባል ወያኔ ተንኮለኛ አይደለም። የአብይ መንግስትም ጽድቅን የተላበሰ ነው ማለት አይደለም።

  TPLF was far worse than ተንኮለኛ

  The Abiy government isn’t much different from TPLF.

  >>> በዘር ላልተሰለፈ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማይዋጥ የፓለቲካ ስሌት ነው።

  TPLF was tribalist, the Abiy government is also tribalist. Both TPLF & the Abiy government ARE NOT እውነተኛ ኢትዮጵያዊ. If you want እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መንግስት, you must join others, Tigrians and other Ethiopians, to remove the Abiy government from power, including by using violent means.

 3. በግልጽ እንነጋር ከተባለ በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው ድርጅታዊና ክልላዊ መግለጫዎች ወያኔ ጸብ ጫሪ ቃላትን፣ ና ከፈለክ ግጠመኝ የሚል ጉልበተኛ ድምጾችን ሲያስተላልፍ እንሰማለን፡፡ እራሱንና ደጋፊዎችን ጀግኖች፣ የተቀረውን ተሸናፊና ተንበርካኪ አድርጎ ከመሳል አልፈው በ1983 የመጣውን ለውጥ ብቻውን ያስገኘው እንደሆነ በአዛውንት የቀድሞ ድርጅቱ አባላት በ2012 በተከበረው የህውሃት ሙት አመት ላይ ሲያላዝኑ ነበር፡፡ በጣም የሚያሳዝኑትና ዝምታን የመረጡት አብረው ተዋድቀናል የሚሉት የኦፒዲኦ፣ ብአዴንና ደህዴን አዛውንት አባላት የነበሩና የአሁን ጡረተኛ አባላቱ ናቸው፡፡ ያሸነፍነው እኛ ብቻ፣ ህገመንግስቱን ያረቀቅነው ወያኔ (ስዩም መስፍን በ2012 በተከበረው የህውሃት በኣል ወቅት የተናገረው፣)፣ በጦርነት ያሸነፍናቸው የትምክህት ሃይሎች (ደጺ በስታዲየም) እና የመሳሰሉት፡፡
  አሁንም በየአጋጣሚው ፌዴራል መንግስቱን ለማሳሳትና ስሜታቸው ከጋለ ብሄረተኞች ድጋፍ ለማግኘት የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ የሚገኘው ህውሃት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ፌዴራል መንግስቱን ሲናገር የምንሰማው ህግ የማስከበር ሃላፊነት ስለመወጣት እንጂ የጦርነት አዋጅ ሲደልቅ አይደለም፡፡ ይህን እንደውም ፌዴራል መንግስቱን መወቀስ ካለበት በስልጣኑ ልክ ይህን ህግ የማስከበር ስራ ባለመወጠቱ፡፡ ለዚህም ነው ህውሃት ኑ ግጠሙኝ፣ መመከት፣ በምድር አንድም ሃይል አይመልሰንም የሚሉን፡፡ እረ ይበቃል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.