በኢትዮጵያ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11 ደረሰ . እስካሁን ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 1172 ደርሷል

በኢትዮጵያ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 11 መድረሱን የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 1172 ማሻቀቡን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ባለፉት 24 ሰዓታት ሶስት 3 ኢትዮጵያዊያን በወረርሽኙ ሳቢያ ህይወታቸው በማለፉ ሳቢያ የሟቾች ቁጥር 11 ደርሷል። ህይወታቸቸው ያለፈው ሶስቱ ኢትዮጵያዊያን አንደኛዋ 29 ዓመት ሴት የትግራይ ክልል የሰቲት ሁመራ ነዋሪ ሁለተኛ የ75 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ ሁለቱም በሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ሲሆን፤ ሶስተኛዋ የ55 ዓመት የደቡብ ክልል የከፋ ዞን ነዋሪ (በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የመጣ) ሲሆኑ ህይወታቸው ካለፈ ብኋላ በተደረገ የአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ተብሏል።

ሚኒስትሯ እንዳሉት የወረርሽኙ ስርጭት በፍጥነት እየተስፋፋ በመሆኑ ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄዎችን መተግበር አለበት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.