ታግተው የደረሱበት ያልታወቁት የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የአማራ ተማሪዎች ጉዳይ ምላሽ ሳያገኝ ስድስት ወር ሞላቸው

አሚማ
ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተነስተው ወደ መኖሪያ ቀያቸው በማምራት ላይ የነበሩ ተማሪዎች ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች( አንዳንዶች ቄሮና ኦነግ ይሏቸዋል) መታገታቸው ከተነገረና ያሉበት ሳይታወቅ እነሆ ዛሬ ግንቦት 24 ስድስተኛ ወር ሆኗቸዋል።

ይህንን ተከትሎ የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ በአማራ በርካታ ከተሞች ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል፤ አብን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በጉዳዩ ላይ መግለጫ አውጥተዋል፤ ሰብአዊ የመብት ተሟጋቾችም በቂ ባይባልም ድምጻቸውን አስተጋብተዋል፤ ይሁንና ጉዳዩ ያለ መፍትሄ 6 ወራትን ተሻግሯል።

መንግስት አንዴ ጉዳዩ እንዳልተፈጸመና የውሸት ዜና እንደሆነ፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ጉዳዩን እንደሚያውቀውና ከዚህ እልፍ ብሎም 21 ተማሪዎችን ከእገታ በማስለቀቅ ወደ ዩኑቨርሲቲው እንደመለሳቸው ቢገልጽም፤ ሀቁ በተቃራኒው መሆኑንና ዩኒቨርሲቲዎች ሲዘጉም ልጆቹ ወደቤተሰቦቻቸው እንዳልሄዱ ታውቃል። ያኔ መንግስት የሚመልሰው ቢያጣ ከህዝብ ለሚጠየቀው ሁል እየሰማ ዝም ማለትን መርጦ ቆይቷል።

ቢቢሲ የደረሱበት ሳይታወቅ የተወሰኑ የተማሪዎቹ ቤተሰቦችን አነጋግሪያለሁ ባለው መሰረት አሁንም በሀዘንና ሀሳብ ተቆራምዳው ለተለያዩ በሽታዎች መዳረጋቸውንና ስራቸውን ተረጋግተው መከወን እንዳልቻሉ ነግረውኛል ብሏል። አሁንም ታስፋ ሳይቆርጡ መንግስት ልጆቻቸውን በህይወት እንዲያመጣላቸውም እየጠበቁ ነው።

የታገቱት የተማሪ ቤተሰቦች ሰቀቀንና የየዕለት ሀዘን፣ የመንግሥት ዝምታ እና የታጋቾች አሁናዊ ሁኔታ እስከመቼ ይቀጥላል የሚለው ጥያቄ እስካሁን ያልተፈታ መልስ ያላገኘ ጉዳይ ሆኗል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.