ህወሀት ከኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት አባልነት ተሰረዘ ተባለ

ህዝባዊ ወያነ ኀርነት ትግራይ ከዓባልነት የተሰረዘው የጥምረቱን መተዳደሪያ ደንብን ባለመክበሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት አስታውቋል። ህወሃት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተጠራው ስብሰባ ላይ አልተገኘም ሲልም ጥምረቱ አያይዞ ገልጿል።
ይህ ውሳኔ ያስተላለፈው በ4ኛው መደበኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባዔው ላይ ሲሆን በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ሀገራዊ ምርጫ እንዳይካሄድ መወሰኑን ተገቢ መሆኑንም ጉባኤው መክሯል፡፡
የጥምረቱ ጉባኤ በሀገሪቱ ሰላምና ጸጥታ ሊሰፍን በሚችልባቸው ሀሳቦችም ላይ ውይይት ማደረጉን የሀገር ውስጥ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የጥምረቱን ሊቀመንበር አቶ ደረጀ በቀለን ጠቅሰው ዘግበዋል። ህወሀት ጨምሮ ከሃያ በላይ ፓርቲዎች አባል የሆኑበት ኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት በአንድ የምርጫ ምልክት እንደሚወዳደሩ ሲገልፁ መቆየታቸው ይታወሳል።

DW

2 COMMENTS

  1. እማን ላይ ቆመሽ ማንን ታሚያለሽ ?
    ተራ ድራማ !!ማን ፈጠራችሁና ???

  2. ተሰረዘ ተባለ እንዲህ አይነት ያልጠራ ነገር ለእይታ ማቅረብ ጥሩ ነዉ? ህወአት ግፉን ቆጥሮለት መስጊድ እንደ ገባች ዉሻ በየቦታዉ ይዋከብ ይዟል። እነዛን ሰይጣናት አምኖ የተከተለ መጨረሻዉ ይኸዉ ነዉ። አሁን የት ሊሄዱ ነዉ አረጋዉያኑ የቦጨቁትን ይዘዉ ባህር ማዶ ይነጉዳሉ እንደዉም መገንጠሉን የፈለጉት ለራሳቸዉ ፓስፖርት አስበዉ ይሆን?፡እባካችሁ ለትግራይ ህዝብ እዘኑለት በሏቸዉ።
    እኔ ግን እንደሚገባኝ ለሰራነዉ በደል እራሳችንን አለት ድንጋይ ላይ ፈጥፍጠን እንሞታለን እንዳይሉን ነዉ ጨክነዉ ባደረጉት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.