አቶ በቀለ ገርባ እና ጀዋር መሐመድ 3ኛ ፖሊስ ጣብያ ናቸዉ

የአቶ በቀለ ገርባ ባለቤት ወ/ሮ ሃና ባለቤታቸዉ በሦስተኛ ፖሊስ ጣብያ መታሰራቸዉን ከፖሊስ በደረሳቸዉ የስልክ ጥሪ ማረጋገጣቸዉን ተናገሩ። ፖሊስ ወደ ወ/ሮ ሃና የደወለዉ፤ «ለአቶ በቀለ ገርባ የደም ግፊት መድሐኒታቸዉን እንዲያመጡላቸዉ ለመጠየቅ ነዉ፤» ብለዋል። ወይዘሮ ሃና የባለቤታቸዉ «የደም ብዛት ሕመም እንደተነሳባቸዉ» ተናግረዋል።
« ባለቤታቸዉ በሚገኙበት ሦስተኛ ፖሊስ ጣብያ መድሐኒቱን ካደረሱ በኋላም ለአቶ በቀለ ገርባ ምግብና ልብስም እንዲያመጡላቸዉ ተደርጎ እንደወሰዱላቸዉ » ወ/ሮ ሃና ተናግረዋል። የአቶ በቀለ ባለቤት ወ/ሮ ሃና ምግቡን ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣብያ ሲያደርሱ፤ ባለቤታቸዉን አቶ በቀለ ገርባን እና አቶ ጀዋር መሐመድን ከሩቅ ጎን ለጎን ቆመዉ እንዳይዋቸዉ ተናግረዋል።
ይሁንና ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር የታሰሩ ልጆቻቸዉ ይት እንዳሉ እንደማያዉቁ ወይም እንዳላይዋቸዉ ወ/ሮ ሃና ተናግረዋል። የአቶ በቀለ ገርባ ልጆች ቦንቱ እና ሳሙኤል በቀለ እንዲሁም የአቶ በቀለ ገርባ የእህት ልጅ ኪያ በላቸዉ ከአቶ በቀለ ጋር የሟቹን አርቲስት አስክሬን ወደ አዲስ አበባ በመመለሱ ሂደት ላይ ተገኝተዉ ተይዘዋል»ተብሎአል። «ቤተሰቡ በአንድ መኪና በእህታቸዉ ልጅ በኪያ በላቸዉ አሽከርካሪነት በኦሮምያ የብልጽግና ቢሮ አስክሬኑን በመመለስ ጉዳይ ላይ ተሳትፈዋል» ተብሎአል።
DW ዶቼ ቬለ ፈጣን መረጃን ያደርሳል፤ ገፃችንን ላልደረሳቸዉ በማካፈል ተባበሩ!
DW

2 COMMENTS

  1. የዶ/ር ኣብይ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ ኣቅርቦኣል።ህዝቡም ምላሹን ሀገር ኣቀጥቅጥ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ መግለጽ ይጠበቅበታል።የሚቀጥለው እርምጃ ክተት ኣውጆ ለሀገራችን መበጥበጥ መቀሌ ቁጭ ብሎ እዝ የሚያስተላልፈውን ኣካል ከኣልሻባብ ባልተለየ ሁኔታ በኣሸባሪነት ፈርጆ፣ ጥሉ ከወያኔ እንጂ ከትግራይ እንድልሆነ ኣስፈላጊው ገለጻ ተሰጥቶ፣ በቁጥጥር ስር ማረግ ነው ።
    ወያኔዎች ይህን ሁሉ ግፍ ሲፈጽሙ ፣ ለእኩይ ተግባራቸው ገንዘብ የሚሰሩ ድርጅቶቻቸው በነጻነት ይቀሳቀሳሉ፣በየኮንቴነሩ የታጨቀው ብር ብሄራዊ ባንክ በማያውቀው ሁኔታ በሀገር ውስጥ እየተቀሳቀሰ ደሀውን በ excessive inflation ይቀጣል፣ በውጩ ኣለም የገንዘብ ማዘዋወሪያ ከፍተው ሃገሪቱ ውስጥ ሊገባ የሚችለውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ከዘረፉት ብር በሀገር ውስጥ በጥቁር ገበያ ሂሳብ ለተላከለት ሰው በብር ባንክ ኣካውንት ያስገባሉ።ሌሎችንም ወንጀሎች እስከመቼ እንታገስ ??
    ማፈሪያ ምደኞቻቸውን በተጀመረው መንገድ ከየጉሮኖው እየለቀሙ ለተፋጠነ ፍርድ ማቅረብ ነው ።ከዚህ ያነሰ እርምጃ መውሰድ ራስን ለጥቃት ኣጋልጦ መስጠት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.