ኦቦ ሽመልስ አብዲሣ ዛሬ የሃጫሉ ቀብር ሥነስርአት አምቦ እየተካሄደ ባለበት ወቅት በOBN ያደረገው ንግግር ትርጉም ፣

ሃጫሉን በኖረበት በእዚሁ ከተማ እንድንቀብረው ዝግጅት ነበረን። ቤተሰቦቹ በትውልድ መንደሩ እንቅበረው ስላሉ የነርሱ ፈቃድ ማከበር ነበረብን፣
ሃጫሉ አንድ ቀን ይገድሉኛል እንዳለ አለፈ፣
ሃጫሉን አንድ ግዜ ብቻ አይደለም የገደሉት ፣
አስከሬኑ ወደቤተሰቦቹ እየተሸኘ ሳለ መሣሪያ የታጠቁ አስከሬኑን ነጥቀው ወደ አዲስ አበባ መለሱት ፣ ህዝብ በተኩስ ለውጥ እንዳይጎዳ ብለን ዝም አልናቸው ፣ ይህም አንሶ የብልፅግና ፅ/ቤት ድረስ ዘልቀው ሥራ ላይ የነበረውን ሰው በመግደል ግጭት ለመቀስቀስ ሞከሩ፣ ያንንም በትዕግሥት አለፍነው ፣ በትናንትናው እለት ደግሞ ኦነግ ሸኔና የወያኔ ታጣቂዎች በቅንጅት ወላጆቹ ቤት ድረስ ዘምተው አጎቱን በጭካኔ ገደሉት፣ ይህ ለሃጫሉ 3ኛ ሞት ነው ።
ለሃጫሉ ግድያ ተጠየቂዎቹ ኦነግ ሸኔ ወያኔና በህዝብ ትግል ገብተው እዚህ አዲስ አበባ ቁጭ ብለው ህዝብ የሚያምሱ ናቸው ፣ ሃጫሉን ለእርድ ያዘጋጁት የግዲያው ተባባሪዎች ከሳምንት በፊት ሚዲያቸው ላይ አቅርበውት ምን እንደጠየቁት ማንም ሰው የሚያውቀው ነው፣ ያ ቃለመጠይቅ የተዘጋጀው ለሴራቸው ስኬት ህዝብን ከህዝብ ለማባላት በማሰብ እንደነበር ግልጽ ሆኖአል።
ከጥያቄያቸው አንዱ ትግራይ ሂዶ ከወያኔ ጋር መነጋገር እንዴት ወንጀል ነው ትላለህ ? ድሮ ድሮ ኦሮሞ ኦሮሞ ትል ነበር አሁን ቋንቋህን ቀይረሃልም ነበር ያሉት ።
ሃጫሉ እነርሱ የግል ህይወታቸውን ሲያደላድሉ ከጠላት ጋር ግንባሩን ሰጥቶ ስተናነቅ የኖረና ጨቋኝ ሥርአት ለማንኮታኮት መስዋእት የከፈለ ጀግና ነው ፣ በነፃነት ወደ አገራቸው ሲመለሱ አክብረን የተቀበልናቸው ግን ለህልፈቱ ተባባሪ ሆኑ ።
ከአሁን ቦሃላ ትዕግሥታችን ተሟጦአል። ያሳየነው ትእግሥትና ፍቅር ከፍርሃት የመነጨ አይደለም። ወያኔ፣ ኦነግ ሸኔና አዲስ አበባ ሆኖ ውጥረት የሚያመርተው ቡድንና ከግብፅ ጋር ተባብረው አገራችንን እንዲያተራምሱ የሚፈልጉ ሃይሎች አላማቸው አይሳካላቸውም ፣ ክልላችን ሰላም እየነሱ ያሉ እነዚህን ሃይሎች የገቡበት ገብተን ከክልላችንን እናጠራቸዋለን።
ከበሰበሰው ሥልጣን ጠራርገን ያባረርነው ወንጀለኞች እርስ በርስ አባልተውን ዳግም ወደሥልጣን ሊመለስ አይችልም ። ኦሮሞ ግንድ ነው፣ አባት ነው ፣ታላቅ ነው በኖረው ባህልህ ከሁሉም ህዝብ ጋር በፍቅር መኖርህን ቀጥልበት። እርስ በርስ በመባላት ለጠላቶቻችን ሴራ እንዳንመች አደራ እላለሁ ……”
ሳሙአል

3 COMMENTS

 1. I am happy with your statement . Keep consistency and firmness !!

  ነገርን ነገር ያመጣዋል እንዲሉ፣
  ኣዲስ ኣበባ የኢትዮጵያ እና የኣፍሪካ ዋና ከትማ ከመሆኑዋም ባሻገር የብዙ ኣለም ኣቀፋዊ ድርጅቶች ዋና መስሪያ ቤቶች መገኛ ቦታ ናት።የሚኖርባትም ኣመለካከቱ የሰፋ ፣ የዘር እና የጎጥ ዝንባሌ የሌለው ፣ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ውሁድ የሆነ የራሱ ልዩ መለያ ያለው ህዝብ ነው።
  ኣዲስ ኣበባ እጅዋን ዘርግታ ማንንም ፣ ከየትም ጎሳ ይምጣ ተቀብላ የምታስተናግድ የሁሉ እናት ናት።
  ነገር የመጣው በ 97 ህዝባዊ ምርጫ ቅንጅት ባሸነፈበት ወቅት ስራዬ ተብሎ፣ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ሲባል ኣዳማ የነበረውን የኦሮሚያ ዋና ከተማ ወደ ኣዲስ ኣበባ ክልጠፋ ቦታ እንዲመጣ ተደረገ።የታሰበውም ኣልቀረ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የመረጠው ኣስተዳደር እንዳልሆነ ሆኖ ቀረ።
  ወንድሜ ኣቶ ሽመልስ ኣዲስ ኣባባን እንደቀድሞዋ ሙሉ ነጻነቱዋን ፣መልሱላት ሁለት ኣስተዳደር፣( Federal /State / ሁለት Town planning፣ ሁለት ከንቲባ፣ ሁለት ራእይ ፣ ሁለት ኣይነት ህግ ኣስከባሪ፣.. ሁለት ፣ ሁለት………..dual administrations, policies, visions , goals ,objectives …sometimes mutually exclusive / ሆና ኣት ዘልቀውም ፣ ሰላምዋም ተናግቶኣል።
  ስለዚህ እባክ ዎ ለነዋሪው ሰላምና መረጋጋት፣ ለሁሉም የጋራ ከተማ ባለቤትነት ስሜት ፣ የኣፍሪካ መዲናነቱዋን ለማስከበር ፣ የወደፊት እድገቱዋን ለማሳለጥ ሲባል የኦሮሚያን ዋና ከተማ ከኣዲስ ኣበባ ኣስወጡት። በዙ ሪያዋ ያሉ ገበሬዎች ለኑዋሪው ኣካሉ; ወገኑ ናቸው፣
  መስተጋብሩ በህግ እና በገበያ ህግ ይወሰናል።ከባህርዳር፣ መቀሌ፣ ኣዋሳ…………etc መስፋፋት ባልተለየ ሁኔታ።
  ኣዲስ ከተማ መቆርቆር ኣሁን ኣብጦ የፈነዳውን ስራ ኣጥ ወጣት ሰፊ የሆነ የስራ መስክ ይከፍተለታል።ኣዲስ ኣባባ የፌዴራሉ መቀመጫ ብት ሆን፣ ኣዲሱ የኦሮሚያ ዋና ከተማ የፋይናስ ትቁዋሞች መቀመጫ እንዲሆን ኣርጎ ማመቻቸት ይቻላል፣ የታሪኩን ዳራ ትተን ፣ ህዝብ በተግባር እንዴት ይጠቀማልን ማሰብ ኣስተዋይነት ነው ።ሌላ ኣጀንዳ እስከሌለ።
  እግዛብሄር ለ መሪዎቻችን ማስተዋልን ይስጥልን !!

 2. ለራሱ ህይወት አሰጊ መስሎ ስለታየው ነው ይህን አይነት ዲስኩር የሚናገረው። ውሸታም። ኦነግ ሼኔ የኛ ኘው ሲል አልነበረም? የዘመኑ የኦሮሞ ፖለቲከኞቾ ሰብአዊ መርህ የላቸውም። ጎሳ ነው ለሁሉ ነገር መለኪያቸው

 3. @Bosna
  በኣብይ ዘመን የወያኔ ነፍጠኛ / Woyane’s signature / የሚለው የጥላቻ መቀስቀሻ ቃልን ከ ለውጡ ሃይል ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመ ባለ ስልጣን ቢኖር ሸመልስ ነው ። ይቅርታም የጠየቀበት ኣይመስለኝም ።
  Let us put that at the back of our mind and be generous to give him the benefit of the doubt at this juncture of our current history .
  ሆድ ከሁዳድ ይሰፋል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.