ዶርተር አብይ ሆይ ኢትዮጵያ ሳትፈርስ የሕወሃትን ማፍያ ቡድን በነካ እጅህ አፍርስ !! /ከታዛቢው/

**** “ሃጫሉን የገደሉት ነፍጠኞች ናቸው ፤ መላው የኦሮሞ ህዝብ የምኒሊክን ሃውልት አፍርሰህ ወደ ቤተመንግስት ገስግስ” ይህን ያለው የዶክተር አብይ የለውጥ ቡድን እነ ጃዋር መሃመድን በቁጥጥር ስር ከማዋሉ በፊት በሕወሃት የደም ገንዘብ የሚቀለበው ፕሮፌሰር እዝቅኤል ገቢሳ አሜሪካ ቁጭ ብሎ ሕወሃት ባደራጀው ዲጂታል ሚድያ የዘር ዕልቂትን ሲያውጅ ነበር::

**** “በደረሰን መረጃ መሰረት ፤ የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ነፍጠኞ ሳይሆኑ ስልጠናና ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የመጡ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ናቸው ፤ እኔ በደንብ አውቃለሁ እነማን እንደገደሉት ፤ ምን ዓይነት ሚሊተሪ ፐርሶኔል እንደተሳተፈም አውቃለሁ፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን አይደሉም፤ ኤርትራውያን ናቸው” ይህን የተናገረው ደግሞ የኦሮሞ ልሂቅ ነኝ የሚለው መርዘኛው ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ ነው :: ፀጋዬ ሃገር መምራት የማይችል ደካማ ነው ፤ ምንም አያመጣም እያለ በአደባባይ ሲንቀው የነበረው የዶክተር አብይ የለውጥ መንግስት እነ ጃዋርን ጠራርጎ ለፍርድ በማቅረብ ሀገሪቱን ሲያረጋጋና መላው ሕዝብ ከጎኑ መቆሙን ሲያረጋግጥ ነገ ለእኔም አይቀርልኝም በሚል ስጋት ተውጦ ከ 80 በላይ ንፁሃን ዜጎች በጄኖሳይድ የዘር ማጥፋት ዕልቂት ካስጨፈጨፉና የሃገር ንብረት ካወደሙ በኋላ 360 ዲግሪ ተገልብጦ ትላንት በጄኖሳይደሩ የሕወሃት ዲጂታል ሚድያ “ትግራይ ሚድያ ሃውስ” ቀርቦ የተናገረው ሌላ አሳፋሪ ጉድ ነው:: አበው “በአንድ እራስ ሁለት ምላስ” እንዲሉ ፤ይህ የፀጋዬ አራርሳ የመርዝ ንግግር ሕወሃት ለዘመናት ሲጠነስስ የኖረው የአማራ እና የኦሮሞ ግጭት አልሳካ ማለቱን ሲያውቅ ኢትጵያዊው በወንድሙ የኤርትራ ሕዝብ ላይ እንዲነሳ ያቀነባበረው ሌላኛው መሰሪ የሕወሃት ሴራ ዕቅድ መሆኑ ነው:: ንግግሩን ከቪድዮው ላይ ማድመጥ ትችላላችሁ:: https://www.facebook.com/491049821051514/videos/724111555100413/

እንደ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ በኢትዮጵያ ታላላቅ ብሄረሰቦች አማራ እና ኦሮሞ መካከል የዘር ዕልቂትን በማቀነባበር ሀገሪቷን ለማፍረስ የታሪካዊ ጠላታችንን ግብፅ ምኞትና ፍላጎት ለማሳካት ከሊቀ ሰይጣኑ የትህነግ/ሕወሃት የማፊያ ቡድን ጋር በጥምረት ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ኃይሎች ላይ ከሰሞኑ የዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር ቆፍጠን ያለ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ እጅግ የሚያስመሰግነው ነው:: ሃገሪቱን በቋንቋ እና በብሄር ከፋፍሎ የውሸት የጭቆና ትርክትንና የለበጣ እኩልነትን እየሰበከ ፤ በአባይ ወንዝ ላይ ያላቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ተገንጣይ ቡድን አድርገው ጠፍጥፈው በመሰረቱት ግብፅ እና የአረብ ሃገራት የገንዘብና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ትናንሽ ግዛቶችን በመፍጠር ኢትዮጵያን ለመበታተን የአንድነቱን ኃይል “ነፍጠኛ ትምክህተኛ እና ጨቋኝ ” ወዘተ የሚሉ ስሞችን በመለጠፍ ፤በዕለት ጉርስ እጦትና በእርዛት የሚንገላታውን ሀገር ወዳድ የአማራው ህዝብ ጥንታው ርስተ መሬቱን የዘር ማፅዳት ዕልቂት በመፈፀም የቻለውን ያህል ቆርሶ ወደራሱ በማካለል ግዛቱን ከ 60 በመቶ በላይ ያሰፋው ሕወሃት ከጅምሩ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ለመሆኑ ዋናው ምስክር “ስልጣን ከእጃችን ከወጣ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” እያለ በድፍረትና በንቀት ያሰማው የነበረው ቀረርቶ የአደባባይ ምስጢር ነው:: በሱዳን ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የስልጣን ተቀናቃኝ ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት ሲል ብቻ፤ የኢትዮጵያን ለም መሬት ሳይቀር ከ 12 ሺህ ሄክታር በላይ ቆርሶ ለሱዳን ገፀበረከት አድርጎ የሰጠው ሕወሃት ኢትዮጵያዊነት በደሙ ውስጥ አለ ለማለት ፈፅሞ ይከብዳል:: ይህ ግፈኛ የማፍያ ቡድን ከሁለት ዓመታት በፊት በሕዝባዊ አመፅ ተገፍቶ ወደ መቀሌ ሲሸኝ “መግደል ሽንፈት ነው:: ይቅርታ ማድረግና መቻቻል ብልህነት ነው” ሲሉ ተደጋጋሚ የአደባባይ ዲስኩር ሲያሰሙ ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እባክዎ! ሕወሃት የለየለት አምባገነን እና ሙሰኛ ቡድን አይደለም፤ ስልጣን ዳግም ወደ እጁ ካልገባ ኢትዮጵያን ከማፍረስ ወደኋላ ስለማይል ይህን ቡድን ትጥቅ ማስፈታቱ ይበጃል” ሲሉ አያሌ ኢትዮጵያውያን ተማፅነዋቸው ነበር:: ሆኖም ሰሚ ጆሮ ባለመኖሩ ለ 28 ዓመታት በዘረፉት የሀገሪቱ ሃብት በመላው ሀገሪቱ በብሄሮች መካከል ግጭትን እያቀናበሩ ፤የአያሌ ንፁሃን ደሃ ዜጎች ደም ዛሬም ድረስ እንዲፈስ ፤አብያተ ክርስቲያናትና መስጂዶች እንዲቃጠሉ ብሎም የግለሰቦችና የመንግስት የልማት ተቋማት እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል:: ዛሬም በአቋራጭ ስልጣን ለመቆናጠጥና የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ፤ከጠላት በሚሰፈርላቸው ረብጣ ዳረጎት የግብፅን ምኞት ለማሳካት ጭምር በኦሮሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ ጎራ ስም ተደራጅተው ለዕኩይ ዓላማቸው መሳካት ከእነሱ ጋር መንግስትን ለመገልበጥና ሃገሪቱን ለመበታተን ከበሮ የሚደልቁ ግለሰቦችን “የኦሮሞ ሕዝብ ጠላቶች ” ሲል በጠንካራ የሰላ ሂስና ትችት በአደባባይ በተደጋጋሚ ሲወቅሳቸው የኖረውን ታዋቂውን ወጣት የነጻነት ታጋይና ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ፤በኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ እና በትራይ ሚድያ ሃውስ “ነፍጠኛው ነው የገደለው:: ምን ትጠብቃለህ ? የምኒልክን ሃውልት አፍርሰህ ነፍጠኛውን አጥፍተህ ቤተመንግስቱን ተቆጣጠር” ሲሉ እንደ ፕሮፌስር እዝቅኤል ገቢሳ፣ ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ፣ ጃዋር መሃመድና ሌሎችም የግብፅ እና ሕወሃት አጋፋሪ ደላሎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች በግልፅ እንደ ሩዋንዳው የዘር ፍጅትን እና ዕልቂትን በግልፅ አውጀው እንደለመዱት ለበርካታ ንፁሃን ሞትና ለንብረት ውድመት መንስኤ ሆነዋል::

የሃገር ጠላቶች ያሰቡት አልተሳካም:: ስልጣን ናፋቂዎችም አፍረዋል:: የግብፅ ከፋፋይ መሰሪ ፕሮፓጋንዳ ከሽፏል:: እኩይ ምኞታቸው በኢትዮጵያውያን አንድነትና በዶክተር አብይ የለውጥ ኃይሉ አመራር ቆራጥ እርምጃ መክኗል:: “እኛ ከተነካን ኢትዮጵያ ትፈርሳልች ፣ የዓለም ፍፃሜ ይሆናል” አትንኩን የሹም ዶሮ ነን ሲሉን የከረሙት የአረብ ደላሎች እነ ከበቡሽ ጃዋር ዛሬ ከህግ በላይ አለመሆናቸውን መንግስት በአደባባይ አሳይቷቸዋል:: ትላንት ሰው አስገድለው ንፁሃንን ያለ ሃጢአታቸው እያሳሰሩ ሲሳለቁ የነበሩት እኩያን ዛሬ የእጃቸውን አግኝተዋል:: ደካማ ነው ሲሉ የተሳለቁነት አመራር አሁን ላይ ጥርስ አውጥቶ እንደ አንበሳ እያነቀ ከጥልቅ ጎሬያቸው አንድ ላይ ሰብስቦ የፍርድ ችሎት አቁሟቸዋል:: ያሰቡት ሳይሆን እኩይ ድርጊታቸው የገባው የአማራ እና የኦሮሞ በአጠቃላይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከዶክተር አብይ አመራር ጎን ተሰልፎ ሃገር በማዳኑ ተግባር ላይ እየተረባረበ ይገኛል :: በውጭ ሃገር ተቀምጠው በሚከፈላቸው የደም ገንዘብ ህሊናቸውን ሸጠው በደሃው ወገናችን ላይ የዘር ዕልቂት ሲደግሱ የኖሩትን እነ ፕሮፌሰር እዝቅኤል ገቢሳ ዶክተር ፀጋዬ አራርሳ ዶክተር ብርሃነመስቀል አበበ አሉላ ሰለሞን ዳንኤል ብርሃኔ እና ሌሎችንም በአፋጣኝ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው እንዲሰጡ አልያም በዓለማቀፍ ችሎት ለፍርድ እንዲቀርቡ በማድረጉ ረገድም በጎ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን አይተናል እሰየው የሚያስብል ነው :: የዶክተር አብይ መንግስትም የኢትዮጵያንም ሆነ የራሱን ህልውና ለማስጠበቅ ይህ የመጨረሻ ዕድሉ ይሆናል:: ይህን በእጁ የገባ እና በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ሁነት ጊዜ ሳይሰጥ በህግ አግባብ ተግባራዊ ለማድረግ ህዝቡን አስተባብሮ መነሳት ይኖርበታል:: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የሚሰፍነው ግን እንደ አሁን ቀደሙ በመግለጫ ጋጋታ አልያም “ሽብር እና ዕልቂት የሚደግሱልን የምናውቃቸው ስልጣን ያጡ ኃይሎች ናቸው ” እያሉ በመቆዘምና በመልመጥመጥ ሳይሆን እንደ አሁኑ ቆፍጠን ብሎ ሕወሃትን በማያዳግም እርምጃ ድባቅ መምታት ሲቻል ብቻ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል:: የሀገሪቱን ዜጎች በነጻነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ፍፁም በሚጻረር መልኩ ትንሽ ኮሽ ባለ ቁጥር በባህል ስም ዱላና ገጀራ አልያም የጦር መሳሪያ ይዞ አደባባይ ለተቃውሞ የመውጣት ድርጊትም ሆነ በየሰፈሩ ኢ-መደበኛ መንግስት ሆኖ “ከመሬቴ ለቀህ ሂድ ንብረትህን አምጣ” ወዘተ የሚሉ ግፎችና በህዝቦች መካከል ግጭትን የሚጋብዙ የወንጀል ትንኮሳዎችም ከጎረቤት ሶማሊያው አልሽባብ አልያም ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራምና ከእስላማዊው አሸባሪ መንግሥት አይ.ኤስ አልያም ከአልቃይዳ ተግባር ቢከፋ እንጂ የሚተናነስ ባለመሆኑ መንግስት በአፅንዖት ልዩ ትኩረት ሊሰጠውና በአፋጣኝ በህግ ሊያስቆመው ይገባል ስንል ምክራችንን እንለግሳለን:: ወጣቱ ሃገር አልሚና ስራ ፈጣሪ እንጂ በስሙ ገንዘብ የሚነግዱ የፖለቲካ ቁማርተኞችና ደላሎች መጠቀሚያ እንዳይሆንም በኢትዮጵያውያን ሙያተኞችና ባለሃብቶች እንዲሁም በመንግሥትም ዘንድ ብዙ መስራት ተገቢ ነው:: በአጠቃላይ የዶክተር አብይ የለውጥ ቡድን ሆይ! ሕዝባዊ አመኔታን ለማግኘትና እማማ ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ ሳትፈራርስ በሰላም እና በብልፅግና የልጅ ልጆቻችን መኖሪያ እንድትሆን በጀመራችሁት ቆራጥ እርምጃ የሀገሪቱን አስከፊ ቀንጀኛ ጠላት ወያኔ በማጥፋት አንፀባራቂ ታሪክ ሰርታችሁ ስማችሁን በደማቅ የወርቅ መዝገብ ላይ እንድታሰፍሩ እንማፀናችኋለን :: አዎ ተደጋጋሚ ጥሪያችን ” ዶርተር አብይ ሆይ! ኢትዮጵያ ሳትፈርስ የሕወሃትን ማፍያ ቡድን በነካ እጅህ አፍርስ !!” የሚል ነው ልብ ያለው ልብ ይበል !

ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑር !!

/ከታዛቢው/

1 COMMENT

  1. Can you wait a little to see results before bestowing apreciation of such magnitude. Be patient so you are not disappointed.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.