መለዩ መልበስ ፣ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ዱላ ማሳረፍ ጀግንነት አይደለም – ግርማ ካሳ

ዶር አብይ አህመድ ለሕዝብ ንግግር አድርጓል። የወታደር ልብስ ለብሶ። በዶክተሩ ንግግር ላይ ችግር የለብኝም። ጥሩ ነገር ነው የተናገረው። ልክ እንደ ሁልጊዜ ዶክተር አብይ የሚናገራቸው ንግግሮች ብዙ ጊዜ ደስ የሚሉ ናቸው።
ሆኖም ግን ትልቁ ነገር የወታደር ልብስ መልበስ አይደለም። ትልቁ ነገር ሕግን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ማስከበር ነው። የተሰጠን ሃላፊነት በትክክል መተግበር ነው። መርህ ይዞ መጓዝ ነው። ከስራችን ያሉ የመንግስት ሃላፊዎችን ሕግ እንዲያከብሩ ማስደረግና ተጠያቂ ማድረግ ነው።
ላለፉት 2 አመታት አገራችንን እያመሱ የነበሩት ወገኖች በዋናንት በዶር አብይ ፓርቲ ውስጥ ያሉ የታችኛውና መክከለኛ አመራር አባላት ናቸው። እነ ጃዋር መሐመድ የኦህዴድ ጽ/ቤት ጽ/ቤታቸው ነበር። የእነ አቶ ለማ መገርሳ፣ እነ አቶ ሺመለስ አብዲሳ እነ ጃዋርም “ጓደኛችን ነው፣ አብረነው እንሰራለን” ንግግሮች የሚሰሩ አይደለም።
በጥቅምት ወር በተለያዩ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች የሩዋንዳ አይነት ከፍተኛ ሰቆቃዎች ተፈጽመዋል። በተለይም በምእራብ አርሲ፣ በባሌና በሃረርጌ።፡ በይፋ 86 ሰዎች ሞቱ ተባለ እንጂ ቁጥሩ ሁለት ሶስት እጥፍ ነበር። ይህ ሲሆን የኦሮሞ ክልል ፖሊሶች ፣ የኦህዴድ ሃላፊዎች (አሁንም በስልጣን ላይ ያሉ) ወይም በቀጥታ ሲተባበሩ ነበር፣ አሊያም ዝም ብለው ይመለከቱ ነበር።
ላለፉት 3 ቀናት በድጋሚ በአርሲ፣ በሃረርጌና በተለያዩ ቦታዎች ብዙ ሰዎች በግፍና በጭካኔ አልቀዋል። ነገሮችን ላለማባበስ በዝርዝር ይፋ ያልሆነ እጅግ በጣም ሰቅጣጭ ተግባራት ነው የተፈጸሙት።
በጥቅምት የሆነውን አሳዛኝ ክስተት እንዳይደገም ፣ ዶር አብይ አህመድ መሰረታዊ ለውጦችን ማድረግ ስላልቻለ፣ ስራዉን ስላልሰራ ፣ ሕግን ስላላስከበረ ነው ሰሞኑን ያየነውን ችግር እንደገና የተደገመው። ዶ/ር አብይ ችግሮችን externalize ማድረግ ሳይሆን ለሆነው ነገር ሃላፊነቱን መውሰድ ያለበት በቀዳሚነት እርሱ ነው።
ሕዝብ መንግስት ሕግ እንዲያስከብር ሲጠይቅ ፣ ወንጀለኞች፣ አሸባሪዎችን አደብ እንዲያስገዛለት እንጂ፣ ሰላማዊ ዜጎችን ሕግን እንደ ዱላ በመጠቀም፣ የበቀል እርምጃዎችን እንዲወስድ አይደለም። አጋጣሚውን ለፖለቲካ አጀንዳ መጠቀምና ሰላማዊ የተፖለቲካ ተቃዋሚዎች ለማጥቃት መነሳት ትንሽነትና ሽንፈት ነው።
የወታደር ልብስ መልበስ የጀግንነት ምልክት አይደለም። መናገር የጀግንነት ምልክት አይደለም። አቅም የሌለውን ሰላማዊን ሰው ላይ መበርታት የጀግንነት ምልክት አይደለም። ጀግና ማለት ወንጀለኞች የሚመክት ግን ሰላማዊ ዜጎችን የሚጠብቅ ነው።
ዶር አብይ ጥሩ መካሪዎች ከጎኑ ቢያደርግ ጥሩ ነው። በአንድ በኩል የሚገነባውን በሌላ በኩል ባያፈርስ ጥሩ ነው።

5 COMMENTS

 1. አይ አቶ ግርማ ለምን ግልጽ አታደርገውም? የማ መደብደብ እንዳመመህ ግልጽ ነው። ግን በተለያየ አቅጣጫ ተመልከተው እስቲ

  ፩) ደብዳቢዎቹ የመንግስት ይሁኑ የጁዋር/ሸኔና ወያኔ ሲፓታይዘርስ አለመሆናቸውን ምን መረጃ አለህ? ያውም በዚህ በከፋና አንድነታችንን በምንፈልግበት ጊዜ ያንተው የአቢይን ወታደራዊ አለባበስ ሁሉ አቃቂር ማውጣት ያው ቀሼነትህን ነው ያሳየህው። ለዩኒፎርሙም ከሆነ እነ ሳሞራ ካጠለቁት አለልካቸው ከተሰፋ ድሪቶ የአቢይ ወታደራዊ አይመስልም ብለህ ነው? አስፈላጊ ትችት ነው በዛሬው ቀን?

  ፪) መደብደቡስ እውነት ከሆነ ግፍ ነው። ወንጀልም ነው በድህረ ወያኔ አስተዳደር። ወደ መቶ የሆኑት ያለቁትን ዜጎች ምነው በጨረፍታም አልነካሀቸውም? ከህይወት እልፈት የመደብደቡ ሞር ካመመህ ብዬ ነው

  ፫) አቶ ስማቸው የተባለው የ ቀድሞ 360 አውታር ቤተኛ ስለነ ኤርምያስ ከነወያኔ መሞዳመድ ማውሳቱን ሰምተሀል? እውነት ከሆነ አንድ ኤርምያስ በሸገር የቀባው ተጠሪ ይሆን የተደበደበብህ? እስኪጣራ ልጠብቅ ብዬ እንጅ ብዙ ባልኩኝ ነበር።

  ለመሆኑ ዛሬን ላይ ቆመህ ከትላንት በስትያውን ግድያና ያስነሳውን አቧራ እያየህ፣ መንግስት ስለ ባለፈው ትእግስቱ በአደባባይ እንደቆጨውና ዳግም እንደማይደገም ሁሉ ሹማምንቱ ቃልኪዳን እየገቡ እየሰማህ ለአንድነታችን ነው ወይስ እንድንባላ ነው ያንተው ያለፈውን የመንግስት ሀጢያት መደርደር? ምን የሚሉት ግራ የገባው አጀንዳ ነው ያመጣህው? ሳተናዎች ይህን ካላወጡት ትዝብት ነው። ካሁን በሁዋላ ከወያኔና ከሀዲ ሸኔዎች በቀር ብቻውን መከራ የሚበላውን የአቢይ መንግስት አቃቂር በሚያወጣ ላይ ሰይፌን መዝዣለሁ። የፈለከውን ልትሆን ትችላለህ ። አምላኬን የማመሰግነው የማንም ፓርቲ ሆነ መንግስት ቲፎዞ አይደለሁም። የህሊናዬ ሰው እንጅ ። እዚችው ሚዲያ ላይ ሰንበትን እኮ። ማ ከፋፋይ፣ ማ አስመሳይ እንደሆነ ተገንዝበናል። ይህው ነው። የአንተው እንኳ ግራ የሚያጋባ ስለሆነ መፍረድ ያስቸግራል። የብዙሀን ዝምታ ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ ጠላቶች በግልጽ ተቀምጠዋል። አቢይ አህመድን መጎሸሙ ይብቃ። በዛና ጠነዛ ። በዚህ ግድያም ማግስት አቃቂር? የአባይ ሙሌትና ጠላት እያሰፈሰፈ ከውስጥና ከውጭ እየተቀናጀ አቢይ ላይ አቃቂር ያወጣል እንዴ? ህሊናው ካለህ እራስህን መርምረው ጣትህን ሰውዬው ላይ ከመቀሰር። አበቃሁ።

 2. መለዮ መልበሱ ምን ይጠበስ? ባንድ ወቅት የተማረ ኮሎኔል ነበር:: ሀገር እየፈረሰች ያንተ ቢጤዎች ለሁሉም ነገር የምንቃወምበት ጊዜ ነው? እንደ እስክንድር ና ልደቱ አይነት ታጋዮች ዛሬ ለወያኔ አመቻችና መንገድ ጠራጊ እየሆኑ ነው:: ሀገሩን የሚወድ ከመስከረም በሗላ መንግስት የለም ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ ብሎ አያውጅም

 3. ወንድሜ ግርማ – በሻሸመኔ የመኖሪያ ቤቶችን፤ የትምህርት ተቋሞችንና የንግድ ቤቶችን ሲያቃጥሉ የክልሉ ፓሊስ ቆሞ ነው። በዘርና በጫት የሰከረው ይህ ነገር ሁሉ ለኦሮሞ የሚለው የወጣቶች ስብስብ ከጥፋቱ ሊቆም የሚችለው ሲበድልና ሰው ሲገል ሲገደል ብቻ ነው። በመሰረቱ ሃጫሉን የገደሉት ራሳቸው ኦሮሞዎች ናቸው። አዎን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የወያኔ ረዳት እጅ ሊኖርበት ይችላል። ግን ከያኔውን ከዚያ በፊት በስልክ፤ በቴክስት፤ በመከታተል ሲያስጨንቁት የነበሩት የኦሮሞ ተወላጅ ነን የሚሉ የፓለቲካ ትብታቦች ናቸው። ከወራታት በፊት ወደ ሚኒሶታ የተመላለሱት አቦ ለማ ከማን ጋር መከሩ፤ ስለ ምን መከሩ። ለምንስ ከጠ/ሚሩ ጋር ሞት ካልሆነ ምንም የሚለያየን ነገር የለም ያሉትን ረስተው እኔ የመደመር ጉዳይ አይገባኝም አሉ? በዚህ የጭንቅ ጊዜስ ለምን ከመድረክ ጠፉ? ሰው ሊያስተውል ይገባል? በሚኒሶታስ የተጎለተው የሃገሪቱ ካውንስለር ቢሮ ማንን ነው የሚያገለግለው?
  አሁን የኢንቴርኔት አገልግሎት በሃገሪቱ የተዘጋው በኦሮሚያ ክልል ኦሮሞ ባልሆኑ ዜጎች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ በደል ሌላው ዓለም እንዳያውቅ ነው። ውሸት የሆነውና የፈጠራ ወሬ ኢንተርኔት ተዘጋ ተከፈተ መናፈሱን አይተውም። ግን አንድ ነገር ይገርመኛል። ሰው ካለፈው ለምን አይማርም? በዘር እየተፈረጀ በመጥረቢያና በድንጋይ ተደብድቦ መሞቱን እያወቀ ለምን ራሱን ለመከላከል አይደራጅም? ፍራቻ ነው ወይስ እኖራለሁ የሚል ቀቢጸ ተስፋ? አይገባኝም። የሚገድልንና የሚያቃጥልን ለመመከት በህቡዕም ሆነ በይፋ መደራጀት ስህተት አይመስለኝም። ዝም ብሎ ሁሌ ሰሚ የሌለው ኡኡታ ከምንም አያስጥልም። የዘር ግጭት እንዲፈጠር የሚሉት የመንግስት ወሬ ዝም ብሎ ነው። ተፈጥሮ እማ ሰው በዘሩ እየተመረጠ እየተገደለ፤ ሃብቱን እየተዘረፈ አይደል እንዴ? አርሲ ላይ የተቃጠለው ቤት የማን ነው? ማን ነው የተገደለው? ሃረር ላይ እነማን ናቸው ቤ/ክርስቲያን በፍርሃት ተጠልለው ያሉት። አሁን በወያኔ ሙሉ በሙሉ ማሳበብ ልክ አይደለም። ሃገሪቱን ከውጭም ከውስጥም የሚያምሷት የኦሮሞ ልጆች ናቸው። ልክ አቶ ግርማ እንዳለው በጠ/ሚ ዙሪያ ያሉ በተለያየ ስም የሚጠሩ የኦሮምን ህዝብ እንወክላለን የሚሉና በፌዴራል መንግስቱ ሥር የተሰገሰጉ ናቸው። አዎን የገሌን ቲ-ሸርት ለብሳቹሁ ታይታቹሃል፤ ወጣቶች አደራጅታቹሃል፤ በሚዲያ ግጭት እንዲባባስ ቀስቅሳችሁሃል የሚለው የዶ/ር አብይ ፍትህ ኦሮሞዎችንና ሌሎችን በእስር ላይ እንኳን አድሎ የሚያደርግ ነው። ጃዋር የኦሮሞን ህዝብ ሰላምና ጤና አይሻም። ስልጣን እንጂ! ዶ/ር ህዝቅየል ገቢሳ የውሸት ጡርንባ ከሚነፉት ቀንደኛውና የክፋት አቀጣጣይ የሰሜን አሜሪካ የጃዋር ተወካይ ነው። ዘመኑን ሙሉ ፓለቲካ እንደ ቆሎ ሲቆረጥም የኖረው ዶ/ር መራራ በዘሩ እንደ እንስሳ ተሰልፎ ሌላውን አሽቀንጥሮ ለመጣሉ በቀለ ገርባን መጠየቅ ነው።
  ሞት ለዘረኞች። ሞት ሰውን በሰብዕናውና በሰውነቱ መቀበል አቅቷቸው ሰቆቃን በሚያደርሱ ሁሉ ላይ ይሁን። የሃገሪቱ ሰቆቃ ጀመረ እንጂ ገና ብዙ የመከራ ዝናብ ይዘንባል። በክልል የተዋቀረ፤ የእኔ እጣት ከአንተ ጣት ይበልጣል የሚል የዝንጀሮ ፓለቲካ ለሃገርም ሆነ ለግለሰቦች ሰላም አይሰጥም። ችግሩ የ 30 ዓመት ድብቅ ፈንጂ እንጂ አሁን መፈንዳት የጀመረ የጋራ ችግር አይደለም። በቃኝ!

 4. ወቅቱ የጠ/ሚኒስትሩን አለባበስ አቃቂር ማውጫ ሰዓት አይደለም እሱም አጣብቂኝ ውስጥ ነው ያለው፡፡ አገራችን በወታደራዊ መንግሥት አትደዳደርም እና የሚሊተሪ ልብስ አስፈላጊነቱ ትንሽ ግር ብሎኛል፡፡ ወይስ በሚሊተሪ አስተዳደር ነው አገራችን ያለችው? ምን አልባት ያመለጠኝ ለውጥ ካለ ይቅርታ፡፡
  ሆኖም በዚህ ሰዓት አብይን ማሳነስ ትተን የሚረዳበትን መንገድ መፈለግ የግድ ነው፡፡ በተለይ በተለይ በዚህ በወጣቱ ዙሪያ የሚታየውን አላዋቂነት ዱላቸውን የሚያስጥል ህግም ይሁን ሃይል ተጠቅሞ መላ መፈልግ አለበት፡፡ በመንጋ ግንባር እየፈጠሩ ህዝብን ማሸበር መግደል ከምንም በላይ ትኩረት ተሰጥቶበት መፍትሄ ግድ ነው፡፡ ወላጆቻቸውን ቢሆን ሃላፊነት እንዲወስዱ በማስጠንቀቅ መንግሥት ጠንከር ያለ እርምጃ የግድ ነው፡፡ የመንግሥቱ ሐይለማሪያምን ማህደር ውስጥ ያሉ ጠንክር ያለ እርምJአውን ከመዝገብ ውስጥ መፈልጉ አይከፋም፡፡ (የመንግሥቱን አረመኔ መንግሥት ናፍቄ አይደለም) ነገር ግ ን ዱርዬውን ሰብሰብ ብሎ የሚቆምረውን በጥሩ ይቆጣጠረው ነበር፡፡ በእርግጥ የጀዋር ቡችላዎች ከስላም ፈላጊ ፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ስለተሰገሰጉ እነዚህ የአገር እንቅፋቶችን የማጽዳቱ ሥራ ቀላል አይሆንም፡፡ Let’s hope the best!

 5. አባ ዊርቱ የማንም ፓርቲ ደጋፊ ይደለሁም ማለት ምን ማለት ነው? የመንግስት መሪ ተብዬው ሲገርመን የካድሬዎቹ ነጭ ውሸት ይዘገንናል፡፡ የአቢይ ደጋፊ ለመሆን ስንት አማራ መግደል አለብህ? ከዚህ በላይ ምን ልትሆን ነው? ከደጋፊም ዕውር ካድሬ ማለት አንተ ነህ፡፡ የምትሞጫጭራቸውን ድሪቶዎች ላነበበ ያንተ ማንነት ግልጽ ነው፡፡ ይልቅስ አርፈህ ተደመር፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.