አዲስ አበቤ ኦሮሞ ለምን ገዛን ቢል ኖሮ ደሙን ለኦሮሞ አያፈስም ነበር – ግርማ ካሳ

ሰኔ 16 ቀን ነበር፣ ከሁለት አመት በፊት። መንግስት የጠራው ዝግጅት አልነበረም። ግን የተወሰኑ አክቲቪስቶች ያስተባበሩት፣ የለውጥ ኃይል ለሚባለው ለነ ዶር አብይ የተደረገ ድጋፍ።
እነ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ልብ ይበሉ።፡ይህ የአዲስ አበባ ሕዝብ “ኦሮሞ ለምን ይገዛናል?” ብሎ ለተቃወሞ የወጣ አይደለም። ለመለስ ዜናዊ፣ ለኃይለማሪያም ደሳለኝ ያላሳየዉን ፍቅርና ድጋፍ ፣ ለኦሮሞ መሬዎች የገለጸበት ነው።
ከነዚህ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ፣ ወንድም ስንታየሁ ቸኮል ነበር። አሁን የባልደራስ ከፍተኛ አመራር ነው። እነ ወ/ሮ አዳነች ” ኦሮሞ ለምን ገዛን” ብላቹሃል ብለው ክስ ከመሰረቱባቸው የባልደራስ እስረኞች መካከል አንዱ።
እነ ዶር አብይ የኦህዴድ አመራሮች ነበሩ። ኦሮሞዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆነ የአዲስ አበባ ሕዝብ፣ እነ ስንታየሁና ባልደራሶችም፣ ኦሮሞ ለምን ገዛን የሚል አስተሳሰብ ኖሯቸው አያውቅም። “ኦሮሞ ለምን ገዛን ?” የሚል አመለካከት ቢኖር ኖሮ፣ እነ ዶር አብይ አራት ኪሎን ሲቆጣጠሩ ይሄ ሁሉ ድጋፍ ይሰጣቸው ነበር ? በስኔ 16 ቀን እንደታየው በነቂስ የአዲስ አበባ ሕዝብ በወጥቶ፣ ያዉም በራሱ ተነሳሽነት፣ ለኦሮሞ መሪዎች ድጋፍ ይሰጥ ነበር?
የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥያቄዎች ፣ “የሚያስተዳድረን ማን ነው ? ከየትኛው ጎሳ ነው ? ” የሚለው ሳይሆን “አስተዳዳሪው ብቃት አለው ወይ ? የከተማዋን ሕዝብ ጥቅም ያስቀደመ ነው ወይ ? ሁሉንም ነዋሪዎች በእኩልነት የሚያይ ነው ወይ ?..” የሚሉት ናቸው።
በርካታ የከተማ ነዋሪዎችና ባልደራሶች አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን፣ በሕዝብ ያልተመረጡ የከተማ አስተዳዳሪዎችን፣ እነ ታከለ ኡማ እየተቃወመ ያሉት፣ መሪዎቹ ኦሮሞ ስለሆኑ፣ ወይንም ኦሮሞ ለምን አስተዳደረን ከሚል አይደለም። እነ ታከለ በሚሰሩት አፓርታይዳዊና ዘረኛ የተረኝነት አሰራራቸው ነው። የአንድን ጎሳ የበላይነትና ልዩ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገውን ሴራን እንቅስቃሴ ነው። አራት ነጥብ።
ትንሹ ጃዋር የሆነው ብርሃነ መስቀል አበበ፣ በይፋ የአዲስ አበባ ከንቲባ መሆኑ ያለበት ኦሮሞ ብቻ ነው ሲል ነበር። ብዙ የኦሮሞ ብሄረተኞች አዲስ አበባ የኦሮሞ ንብረት ስለሆነች አዲስ አበባ ከኦሮሞ ውጭ ሌላ ሰው ማስተዳደር የለበትም፣ ከንቲባ መሆን የለበትም የሚል እምነት አላቸው።
ኦሮሞ ብቻ ካልገዛን የሚለውን ዘረኛ አባባል መቃወም ኦሮሞ አይግዛን ማለት አይደለም። ኦሮሞ ልዩ ጥቅም ያግኝ የሚባለው አፓርታይዳዊ አመለካከት መቃወም፣ ኦሮሞ አይጠቀም ማለት አይደለም።
ከ13 አመታት በፊት በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ 20% የአዲስ አበባ ነዋሪ ኦሮሞ ነው። 10% ደግሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋው ኦሮምኛ የሆነ። የአዲስ አበበ ነዋሪ የሆነ ኦሮሞ ፣ ሕዝብ ከመረጠው፣ አዲስ አበባን ማስተዳደር ይችላል። ከወሊሶና ጉሊሶ፣ ከአምቦና ሻምቦ የመጣ ኦሮሞ፣ ነዋሪነቱን አዲስ አበባ አድርጎ፣ የአዲስ አበባ ነውሪ ሆኖ፣ ሕዝብ ከመረጠው የአዲስ አበባ አስተዳዳሪ መሆን ይችላል። ኦሮሞ ማስተዳደር ይችላል። እንኳን አዲስ አበባን መቀሌን ኦሮሞ በሕዝብ ከተመረጠ የማስተዳደር መብቱ መከበር አለበት።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖር ኦሮሞ፣ ኦሮሞ ስለሆነ ሳይሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ስከሆነ፣ በነዋሪነቱ በከተማዋ ያሉ አገልግሎቶች እኩል ተጠቃሚ ይሆናል። መሆንም አለበት።
እነ ወ/ሮ አዳነኝ አበቤ ግን፣ “በሕዝብ ያልተመረጡና የአዲስ አበባን ሕዝብ ጥቅም የማያስጠብቁ ነው” በሚል እነ ታከለ ኡማ ላይ ተቃዉሞ መነሳቱን፣ “ኦሮሞውም የከተማ ነዋሪ እስከሆነ ድረስ እኩል ተጠቃሚ እጂ ልዩ ተጠቃሚ መሆን የለበትም” መባሉን ነው፣ አመጽ ቀስቃሽነት፣ “ኦሮሞ አይገዛንም ” ማለት እንደሆነ አድርገው ነው የፈረጁት።
የአዲስ አበበ ሕዝብ መለስ ዜናዊን ሲቃወም የነበረው፣ ትግሬ ለምን ገዛን ብሎ አልነበረም። ሕዝብ በፍትህ፣ በ እኩልነት፣ በሰላም የዘርና የኃይማኖት ልይነት ሳያደረግ አገርን የሚያስተዳደር፣ ኢትዮጵያውን ከልቡ የሚወድ መሪ መቼም ያከብራል። ይልቅ ሁሉም ነገር የኦሮሞ የሚባለው የኬኛ ፖለቲካ ነው፣ ትግሬ ጠቅላይ ሚኒስተር ነበር፣ አሁን ተራው የኦሮሞ ነው ብለው፣ ኦሮሞ ካልገዛ ደም መፋሰስ ነው የሚመጣው ብለው ሲዝቱ የነበሩት። ከዚህ ጎሳ ያለው ሰው ለን ገዛን ብለውን ደም የሚቆጥሩት የአዲስ አበባ ልጆች አይደሉም። ይሄንን እነ ወሮ አዳነች ጠንቀው ያውቁታል።
በሰኔ 16 ቱ ስልፍ ራሳቸው ኦሮምዎች ነበሩ እነ ዶ/ር አብይ ለመግደል ቦምብ ያፈነዱት። የአዲስ አበባ ወጣት ለኦሮሞው መሪ በመስቀል አደባባይ ደሙን አፍሷል።
2 አስተያየቶች

አስተያየቶች

ወ/ሮ አዳነኝ በንግግሯ ፋዉል ሰርታለች ፣ እርማት ብታደርግ ጥሩ ነው #ግርማካሳ
Tona Ethio

የሚከተለውን ጦምሯል

———————————…

ተጨማሪ ይመልከቱ

4 COMMENTS

 1. አሁን ያንተም አራጋቢነት አማራውንና ኦሮሞን ከማጋጨት ውጪ ምን ሌላ የሚጨምረው ነገር አለ? ከታከለ ኡማ የተሻለ በአዲስ አበባ የሰራ ከንቲባ ነበረ? ህሊና ላለው ሰው:: እኔ ደግሞ ለህሊናዬ የምገዛ የአማራ ልጅ ነኝ:: ታከለ ምኔም ሊሆን አይችልም:: በነዋሪነትም ቢሆን ታከለ 25 አመታት አዲስ እበባ ኖሯል:: እሱ አዲስ አበቤ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል:: ለአዲስ አበቤነት ከቴዎድሮስ ፀጋይ ልዩ ፈቃድ ያስፈልገዋል ማለት ነው:: ዛሬ ወቅቱና ጎራው ለይቷል:: ኢትዮጵያውያን ከዐቢይ ጋር ይቆማሉ: ሌሎች ተቃዋሚ ነን ባዮች የወያኔ መንገድ ጠራጊዎች ሆነው ይቀራሉ:: ያንተ ቢጤዎችም አቀጣጣዮች ከባንዳው ወያኔ ተላላኪ ፅንፈኞች ህዝብን ለመከፋፈል የተቀረፅ አጀንዳ ምንም አትለዩም:: የተለየው ካምፑ ብቻ ነው:: እናንተ በዚህ እነሱ በዚያ::

 2. ግርማ ተሳስተሀል ። መዋሸት ምን ያደርጋል ? የባልደራስ አመራሮች እነእስክንድር አቢይን ሳይሆን ታከለን አዲስ አበባ አልተወለደም ; ላዲሳበቤ አይመጥንም አማርኛ አይችልም ስልጣን ያስረክብ ሲሉ አልነበረም ወይ? መች በስራው ለኩት?

 3. Abiy is not carrying out how his duty as a PM ever since he got to power. Abiy Ahmed and Worqneh Gebeyehu done so much wrong with the GERD negotiation finally he put Amara on the spotlight as a FM, just so the Amara FM takes the blame.Same as Abiy put Health Minister An Amara when CoronaVirus came out.

  Worqneh Gebeyehu was Abiy’s favourite who was put as a FM but he was unable to perform the duty with Abiy doing his work for him but Abiy was not successful either.
  Deputy PM Demeke got no power also he is just a symbol , I personally can not think of one decision he made or one difference he made as a deputy PM under Abiy Ahmed.

  Shimles Abdissa , Lemma Megerssa. Takele Uma …. got the power not Gedu or Demeke.

  Abiy Ahmed had no other choice but to become a Prime Minister to survive, some of the many reasons why he became a PM , I list below.

  1. His wife was living in exile with his children, he knew he can gather his wife and children to live with him by becoming a Prime Minister. He just builds peacocks , he plants flowers , he go around clowning across the globe so he impresses his wife and kids, his failure as a Prime Minister is ridiculous but he thinks he succeeded because he got his wife and children living with him.

  2. He was in neck deep committing crimes with EPRDF, as an INSA spy snitching at first to Lemma Megerssa against Oromos Amaras then next he even passed Lemma and started snitching directly to Getachew Assefa while working for TPLF as a spy, Abiy even was the only spy who caused a little friction between Meles and Getachew because of the clumsy spy work Abiy performed , even Meles and Getachew were for the first time arguing because of Abiy , that’s when Abiy for the first time felt threatened because until then he thought he was Getachew’s and Meles’s right handman. After that clumsy work Abiy did get scared sent his wife to exile right away and Abiy became a psychopath a man of no substance just to survive , his wife was active in the propoganda media against TPLF almost as big as Jawar was with the anti TPLF propoganda at the time. She even became involved with ESAT.

  3. Then when TPLF decided to go to Tigrai because they didn’t want to look like Derg who killed fifty thousand during the red terror when they killed five thousand querro fano…. When TPLF admitted for their record that was too much numbers bad enough for TPLF because they found themselves same as DERG with the rates they were killing each day ,then Abiy was afraid without TPLF in power he would get killed or imprisoned so he resorted to become a Prime Minister by cutting a deal with TPLF just for his safety and for TPLF’s safety. (ABIY DOES NOT MIND IF SAFETY OF ETHIOPIANS IS JEOPARDIZED HERE AND THERE AS LONG AS HE DOESNOT LOOK AS BAD AS TPLF OR AS BAD AS DERG) . He doesn’t order his security apparatus to shoot Ethiopians if he sees Ethiopians getting mutilated, He wants to not be held responsible by amnesty , human rights watch… because he wants to keep his record better than the red terror or the TPLF’s. Balderas and Amara National Movement are threats for him by reporting what is going on, to the international powers so he wants to silence them.

  Abiy Ahmed would give up his job as a Prime Minister to whoever if only he doesn’t get prosecuted for his crimes working for TPLF. He doesn’t care how good of a job or how bad of a job he is doing as a Prime Minister because his reason for being a Prime Minister is not about that . To make matters worse recently after the Hachalu protest/rampage he presented himself as the main target , close to three hundred people lost their lives and he wants to say to the world he was the main victim and he foiled civil war by just three hundred casuallities. There was no civil war attempt or coup attempt , all there was is a Prime Minister holding the government apparatus hostage to save his own skin, repeatedly failing to keep peace and order at the expense of poor vulnerable unsuspecting innocent Ethiopians lives.

 4. Addis abeba belongs to all Ethiopians. it is a city of many international institutions. it is the centre of economic ,social and political activities in our country. Addis Abeba should be governed by its own council elected by the residents of the city. FULL STOP.
  Ethiopia without Addis Abeba is unthinkable. Addis Abeba is what Ethiopia is . It is home for Every ethnic group in our country. it is an international city.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.