ታዋቂው ራፐር ካንዬ ዌስት ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደር አስታወቀ

ታዋቂው ራፐር ካንዬ ዌስት ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደር በትናነትናው ዕለት አስታውቋል።

ይህም ማለቱ ሙዚቀኛው ከሚያደንቃቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይፎካከራል ማለት ነው።

“በአሁኑ ወቅት ለአሜሪካ ቃል የገባነውን አምላክን በማመን የምንፈፅመበት ወቅት ነው። ራዕያችንን በአንድነት እንዲሁም የወደፊቱን የምንገነባበት ወቅት ነው” በማለት በትዊተር ገፁ ላይ ያሰፈረው ራፐሩ “ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ወስኛለሁ” ብሏል

ባለቤቱ ኪም ካርዳሺያንና ቢሊዮነሩ ኤሎን መስክ ለራፐሩ ያላቸውንም ድጋፍ ገልፀዋል።

ነገር ግን ካንዬ በርግጥ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደር ግልፅ አይደለም።

በህዳር ወር ለሚደረገውም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫም ስሙ በፌደራል ምርጫ ኮሚሽንም በተወዳዳሪነት አልተመዘገበም።

ከምርጫ ኮሚሽኑ ቋት በተገኘው መረጃ መሰረት ከካንዬ ጋር የሚመሳሰል ስም ያለው ካንዬ ዲዝ ነትስ ዌስት የሚባል ስም በግሪን ፓርቲ ስም በጎርጎሳውያኑ 2015 በተወዳዳሪነት ተመዝግቦ ነበር።

Skip Twitter post, 1

End of Twitter post, 1

ራፐሩ ለፕሬዚዳንትነት እወዳደራለሁ ሲልም የመጀመሪያው አይደለም።

በጎርጎሳውያኑ 2015 በነበረው የኤምቲቪ የቪዲዮ ሙዚቃ ሽልማትም በ2020 እንደሚወዳደር አሳውቆ ነበር።

ነገር ግን በዚህ አመት ህዳር ወር ላይ የሚወዳደርበትን ጊዜ እንደገፋውና ከአራት አመት በኋላም በውድድሩ እንደሚሳታፍ ገልፆ ነበር።

በወቅቱም ስሙን “ክርስቲያን ጂኒየስ ቢሊዮነር ካንዬ ዌስት” እንደሚለውም ተናግሯል።

Skip Twitter post, 2

End of Twitter post, 2

የአርባ ሶስት አመቱ ራፐር በትናንትናው ዕለት በትዊተር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ ይወዳደር የሚለውን ነገር አላሳፈረም።

ሆኖም ግን አራት ወራት ብቻ በቀሩት ምርጫ ያሉትን ፓርቲዎች ወክሎ መወዳደር የሚታሰብ አይደለም።

ሙዚቀኛው በግል መወዳደር ከፈለገ ደግሞ ፊርማ አሰባስቦ ከቀነ ገደቡ በፊት በአንድ ግዛት መመዝገብ ይኖርበታል። በታላላቅ ግዛቶች በግል ተወዳዳሪነት ለመመዝገብ ያለው ቀነ ገደብ ያለፈ ሲሆን ነገር ግን በትንንሽ ግዛቶች አሁንም መመዝገብ ይችላል።

በቀጣዩ ምርጫ ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት የሚፋለሙት ዶናልድ ትራምፕና የዲሞክራት እጩ የሆኑት ጆ ባይደን ናቸው።

ከሁለት አመታት በፊት ራፐሩ በትራምፕ ደጋፊዎች ዘንድ የሚዘወተረውን “አሜሪካን ታላቅ እናድርግ” የሚል ባርኔጣ አድርጎ በዋይት ሃውስ ከፕሬዚዳንቱ ጋር የተገናኘ ሲሆን፤ ለብዙዎችም ያልገባቸውን ንግግርም አድርጓል።

ትራምፕን በጣም እንደሚወዳቸው ተናግሮ ሊያቅፋቸውም ሲጠጋ ፕሬዚዳንቱም በበኩላቸው “በጣም የሚያስደስት ነው” ብለዋል።

ራፐሩ ከዚህ በተጨማሪ ጥቁር አሜሪካውያን የዲሞክራት ደጋፊ መሆን አለባቸው የሚለውን እሳቤ በመቃወም ተናግሯል።

ባለቤቱ ኪም ካርዳሺያን የካንዬን የፕሬዚዳንትነት መወዳደር ውሳኔ ከአሜሪካ ሰንደቅ አላማ ጋር በማድረግ በትዊተር ገጿ አስፍራለች።

በአሁኑ ሰዓት የፍትህ ስርአቱ እንዲሻሻል ዘመቻ እያደረገች ያለችው ኪም ፕሬዚዳንቱም በርካታ እስረኞችን እንዲለቁ ተፅእኖንም መፍጠር ችላለች።

BBC

Kanye West says he’s running for president

 

https://www.politico.com/news/2020/07/05/kanye-west-says-running-president-2020-348903

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.