በሐጫሉ ሞት የተቀሰቀሰው ቀውስ ወዴት እያመራ ነው?

ከድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የተከሰተው ቀውስ ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ “የርስ በርስ ጦርነት የመቀስቀስ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ለረዥም ጊዜ ሲታቀድ፤ ሲታሰብ የቆየ” ውጥን ነው ብለዋል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ወታደራዊ መለዮ ለብሰው ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ባደረጉት ውይይት “በመሳሪያ፣ በሚዲያ እና በገንዘብ” የተቀናጀ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በአሜሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ እና አውሮፓ አገሮች ባለፉት ተከታታይ ቀናት የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድን መንግሥት የሚተቹ ተቃውሞዎች እየተደረጉ ነው። በማኅበራዊ ድረ ገፆች መቃቃሩ መበርታቱን የሚጠቁሙ መልዕክቶች ይታያሉ። በጉዳዩ ላይ የሚደረጉ የሐሳብ ልውውጦች ልዩነቱ መክረሩን ይጠቁማሉ።


የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥል አስታውቋል። ለመሆኑ በሐጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተቀሰቀሰው ቀውስ ወዴት እያመራ ነው? የሕገ-መንግሥታዊ ዴሞክራሲ እና የአስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ እና የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አደም ካሴ ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ አካፍለዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.