የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ግብፅ አቀኑ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ግብፅ ማምራታቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ከፕሬዚዳንቱ ጋርም አብረውም ከፍተኛ ልኡካን የተካተቱ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስማን ሳላህና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረ አብም ይገኙበታል ።

የፕሬዚዳንቱ የካይሮ ጉብኝት በባለፉት ሳምንታት ወደ ኢትዮጵያና ሱዳን ያደረጓቸቸው ጉብኝቶች ጋር ተመሳሳይ እንደሆነም ከሚኒስትሩ ትዊተር ፅሁፉ መረዳት ተችሏል።

ፕሬዚዳንቱ በግብፅ ቆይታቸው በምን አይነት ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ምንም አልተባለም።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከከፍተኛ ሹማምንቶቻቸቸው ጋር ባለፈው ወር ለሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወቃል።

ፕሬዝዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የዓለም አቀፍ ስጋት ስለሆነው ኮቪድ-19 እና የምስራቅ አፍሪካ አገራት ትልቅ ስጋት የሆነው የአንበጣ መንጋ ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለመወያየት እንደሆነም በወቅቱ ተገልጿል።

ፕሬዚዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል የባቱ ዱግዳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት መርቀዋል።

ከሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት በኋላ፤ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የልማት ፕሮጀክቶች ሲመርቁ እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ላይ መታየታቸው፤ በአገራቸው በአደባባይ የልማት ፕሮጀክቶችን ሲያስመርቁ አሊያም ከተመራቂ ተማሪዎች ጋር ሲታደሙ ብዙ ባላስተዋሏቸው ዜጎቻቸው እንዲነቀፉ አድርጓቸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለአለም ስጋት በሆነበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸው ድንገተኛ የተባለ ሲሆን በርካታ ጥያቄዎችንም አስነስቷል።

BBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.