ኢትዮጵያኖች እና ግብጾች የመረጃ መረብ ጦርነት ከፍተዋል – ታምሩ ገዳ

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የህዳሴ ግድብ ግስጋሴ ያልተዋጠላቸው ግብጻዊያኖች እና የኢትዮጵያ ወንዙን የመጠቅም ፍትሀዊ፣ ተፈጥሮአዊ እና ህጋዊ የውሃው ተጠቀሚነት መብቷን የሚደግፉ ኢትዮጵያኖች መካከል የሚካሄደው የማህበራዊ መረጃ መረቦች ፍልሚያ ተፏፉሟል።
ገልፍ ኒውስ እንደ ዘገበው ኢትዮጵያዊያን እና ግብጻዊያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በአመዛኙ በትዊተር አማካኝነት የህዳሴው ግድብን በተመለከት በተለያዩ ጽሁፎች ፣ተንቀሳቃሽ ምስሎች የተደገፉ፣ኢትዮጵያ ግድቡን በውሀ የመሙላት መብቷን የሚገልጹ ዘመቻዎችን ሲያካሄዱ ተስተውለዋል።በኢትዮጵያኖች በኩል ከተንጸባረቁ ቅስቀሳዎች መካከል ግድቡ የእኔ ነው(ኢት ኢዝ ማይ ዳም)፣ግድቡ ይሞላል(ፊል ዘ ዳም)እና የህዳሴው ግድብ (በአረብኛ ዳም አናሀዳ)…ወዘተ የሚሉ መንፈሶችን አንጸባርቀዋል፣ በተቃራኒው “የአባይ ውሃ ለግብጽ ብቻ መሆን አለበት” ብለው የተንቀሳቀሱ ግብጻዊያኖች”ኢትዮጵያ ግድቡን መገደብ እንደሌለባት” ካልሆነም ደግሞ” ጥቃት እንዲወስድ “የሚቀሰቅሱ ዘመቻዎች ተስተውለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ በሶስቱ አገራት(በኢትዮጵያ ፣በግብፅ እና በሱዳን) መካከል ተዳክሞ የነበረው የህዳሴው ግድብ ድር ድር በትላንትናው እለት በኢንተርኔት ኔት(ቨርቱዋል) አማካኝነት መካሄዱን ዘገባዎች በስፋት ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደምታካሄድ መግለጿ በእጅጉ ያስቆጣት እና ያስደነገጣት ግብጽ ምንም እንኳን የህዳሴው ግንባታን እንደምትደግፍ በይፋ ብትገልጽም በኢትዮጵያ ውስጥ አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት እንዳይፈጠር የማድረግ ውጥኖች እንዳሏት እና ሁለቱም አገራት ከዲፕሎማሲያዊው ዘመቻ ባሻገር ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ወታደራዊ ጡንቻቸውን እንደሚያፍታቱ ቀደም ያሉ መረጃዎች ይገልጻሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.