በአዲስ አበባ እነ አቶ ለማ መገርሳ፣ ታከለ ኡማ የፊንፊኔ ፕሮጀክት – ግርማ ካሳ

በአዲስ አበባ እነ አቶ ለማ መገርሳ፣ ታከለ ኡማ የፊንፊኔ ፕሮጀክት በሚል ያደራጇቸውን ወጣቶች በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ ዙሪያ በብዛት አስፍረዋል፡፡ ይህ ቡድን በቀድሞ ኦህዴድ አሁን የኦሮሞ ክልል የብልጽግና ቅርንጫፍ ድጋፍ፣ ትብብር፣ የሕግ ከለላ የሚደረግለት ቡድን ነው፡፡
እነዚህ ወጣቶች ሰርተው የሚበሉ ሳይሆን ለዘረፋና ለአመጽ ተግባር በጽንፈኛው ቡድን መሪዎች የሚሰማሩ ናቸው፡፡
እነዚህ ወታቶች በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ወይንም በአዲስ አበባ ዳር ዳር ባሉ አካባቢዎች ያሉ የኦሮሞ ገበሬ ልጆች አይደሉም፡፡ ከአርሲ፣ ባሌ ከመሳሰሉ ቦታዎች ፣ የመጡ ናቸው፡፡ ችግር ባለበት አካባቢ በአያሱዙ እየተጫኑ ይሰማራሉ፡፡
የአዲስ አበባ ነዋሪ ይሄን በግልጽ መረዳት አለባት፡፡ መታለል የለበትም፡፡አዲስ አበን ችግር ውስጥ እየከተቱ ያሉት በአቶ ለማ መገርሳ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ ሃላፊዎች፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ይሉ መሪዎችና የኦሮሞ ክልል መስተዳደር ራሱ ነው፡፡
ዶር አብይ አህመድ አቶ ለማ መገርሳ የሰራውን ስራ ካልቀለበሰና ከአዲስ አበባ ውጭ መጥተው አዲስ አበባን የሚያሸብሩ አሸባሪዎች ካላስቆመ በአዲስ አበባ ነገሮች የበለጠ የከፋ ነው የሚሆኑት፡፡ ሄኖክ መሰረት የሚከለተውን በአዲስ አበባ ስለሆነው ነገር ጽፏል፡፡
፟_________________
በአዲስ አበባ ብቻ ከ ሁለት መቶ በላይ የቤት መኪና ተቃጥሏል።
የልደታ እና ሰሃሊተ ምህረት ቤተክርስቲያናትን ለማቃጠል የመጡት አሸባሪዎች በህዝቡ ትብብር ተመልሰዋል።
በሃያት መኖሪያ ቤቶች አካባቢ አደጋ ለማድረስ ሄደው አሁንም በህዝቡ ትብብር ተመልሰዋል።
በሰበታ የሴራሚክ መነገጃ፣ የሮቶ ፕላስቲክ እና መሰል የሱቅ መደብሮችን አውድመዋል።
ህዝቡ ራሱን ሲከላከል እንደነበር ለመረዳት ችለናል።
አሸባሪዎቹ በአይሱዙ እየተጫኑ ነበር የሚመጡት። መንግስት ከተጫኑበት መኪና ላይ ወርደው አደጋ ከማድረሳቸው በፊት ሊያስቆማቸው ፈቃደኛ አልነበረም።
መንግስት እስክንድር ላይ ያቀረበው ክስ፣ የአዲስ አበባን ወጣቶች “መጡባችሁ” “ራስችሁን ተከላከሉ” በማለቱ ነው ብለዋል።
አዎ አሸባሪዎች መጥተዋል፥ ጥቃት አድርሰዋል።
እና በየት ሀገር ነው ራስን እና ንብረትን መከላከል #ወንጀል የሆነው?
ወይንስ እንደሻሸመኔ እና አሳሳ ዝም ብላችሁ ተጨፍጨፉ ነው?
መንግስት ለምን በግልፅ ጎራውን አይለይም?
የመረጃው ምንጭ Henoke Meserte

4 COMMENTS

 1. መንግስትማ ጎራውን ለይቷል:: ሀገር አፍራሽ ባንዳው ወያኔና ተላላኪው ኦነግ ሸኔ ነው ብሏል::ጦርኑቱን ለመመከት ተነስቷል:: የእናንተ ቢጤዎች ስራ የፖለቲካ ቁማር መቆመር ነው:: “የዶ/ር አብይ አገሪቱን ለማረጋጋት እየተሰራ ያልውን ስራ ይማይደግፍ ካለ አገሪቱ እንዳትርጋጋ የሚፈልግ ብቻ ነው::”
  ባልደራስ የኢዜማ ፓርቲ ባለበት ሀገር ለምንስ ያስፈልጋል? ሌላ የቀኝ ክንፍ የጎበዝ አለቃ መሆኑ ነው:: የአዲስ አበባ ህዝብ እራሱን ለመጠበቅ ባልደራስ አያስፈልገውም::
  እንዳንተም ያሉ ፀሀፍት እሳት ለኳሽና አቀጣጣዮች ወያኔ ለጀመረው ኢትዮጵያን የማጥፋት አጀንዳ you are another facilitator. ህዝብ እያለቀ ከተማ እየተቃጠለ ነው:: እናንተ ስለታከለ ኡማ ታላዝናላችሁ::
  ኢትዮጵያን የሚፈልግ በሙሉ በዚህ ወቅት ከዐቢይ ጋር ይታገላል!

 2. ስለ ባልደራስ አላስፈላጊነትና ስለ ኢዜማ አስፈላጊነት አንተ ሳትሆን የአዲስ አበባ ነዋሪ ነው የሚወስነው!! ኢዜማ/ግንቦት7 ለሞተለትና ከሚገባው በላይ ይደግፈው የነበረው የአዲስ አበባ ነዋሪ ባለፉት ሁለት ዓመታት በባለጊዜ የኦሮሞ ዘረኞች ሲታስር ሲፈናቀልና ተወልዶ ባደገበት ከተማ እንደመጤ ሲቆጠር ቢከራከርለትና ከጎኑ ቢቆምለት ኖሮ ባልደራስ ባልተመስረት ነበር:: ባልደራስን መንግስት የሚይስቃየውና አመራሩን የሚያስረው በእውነት ለአዲስ አበባ ህዝብ ስለቆመና የባለጊዜ ዘረኞችን ከተማዋን የመቀራመት ሩጫ ስለሚያጋልጥበት ነው:: በነገራችን ላይ ወያኔ ኢትዮጵያን ማጥፋት የጀመረውና እያጠፋ ያለው ዛሬ ሳይሆን ከአሁኖቹ ተረኞች ጋር ሆኖ ከዛሬ 30 ዓመት ጀምሮ ነው!!

 3. ሁሉ ኬኛ እያሉ በአይናቸው ያዩትን ሁሉ ለመጨበጥ መቋመጥ አያዋጣም። ተከባብሮ መኖር ለሁሉም ያዋጣል።

 4. እውነቱ አሁንስ የእውቀት ክፍተት እየታዘብኩ ነው። የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶር አብይ ነው ማንኛውም ወንጀል እሱ ምን ያድርግ የሚባልበት ነገር የለም የተሰጠውን ስልጣን ተጠቅሞ ከህግ ስር ማዋል ይገባዋል።
  ለራሱ አላማ አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው አማራ ክልል ፈጽሞታልና። ሌላው የሚያስቀው ኢዜማ እያለ ባልደራስ ለምን አስፈለገ ያልከው ነው ይህንን ስቆ ከማለፍ ውጭ መልስ አይሰጥበትም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.