አርሲ ዞን ወደ መረጋጋት ተመልሳለች

በኦሮምያ ክልል አርሲ ዞን በተለይም ዝዋይ ዱዳ ወረዳ የሚኖሩ ወደ ሠላሳ የሚሆኑ አባወራዎች በወረዳዉ ፖሊስ ጣብያ ተጠልለዉ እንደሚገኙ አሳወቁ። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደሉ ከተሰማ በኋላ ሃዘናቸዉን ለመግለጽ ወጡ የተባሉ ወጣቶች መሃል የነበሩ ሰዎች ግድያ መፈጸማቸውና ንብረትም ማውደማቸው ተነግሮአል።

በኦሮምያ ክልል አርሲ ዞን በተለይም ዝዋይ ዱዳ ወረዳ የሚኖሩ ወደ ሠላሳ የሚሆኑ አባወራዎች በወረዳዉ ፖሊስ ጣብያ ተጠልለዉ እንደሚገኙ አሳወቁ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የወረዳዉ ነዋሪዎች ፤ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደሉ ከተሰማ በኋላ ሃዘናቸዉን ለመግለጽ ወጡ የተባሉ ወጣቶች መሃል የነበሩ ሰዎች ግድያ መፈጸማቸውና ንብረትም ማውደማቸውን ተናግረዋል። የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አልዩ በዞኑ ከ 30 በላይ ሰዎች መገደላቸዉን እና ንብረት መዉደሙን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ይሁንና በአሁኑ ወቅት በዞኑ ሰላም ሰፍኖአል ፤ ተፈናቃዮችም እየተመለሱ ነዉ ብለዋል።

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.