ቃላቸውን ባለመጠበቃቸው ዜጎችን ለሰው አውሬዎች አሳልፈው ሰጡ – ግርማ ካሳ

ለማስታወስ ያህል እነዚህ የቀድሞ ብአዴን፣ አዴፓ የአሁን የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች ናቸው።
በነዚህ አመራሮች አማከኝነት ፣ በነርሱ ትከሻ ላይ ነው፣ ኦህዴድ ፌዴራል መንግስቱንና የአዲስ አበባ መስተዳድረን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠረው።
እነዚህ አመራሮች አዴፓን ሲመሰርቱ አንደኛ ሕግ መንግስት እንዲሻሻል እናደርጋለን፣ ሁለተኛ አከላለሉን እናስቀይራለን፣ ሶስተኛ በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ አማራዎች ጉዳይ ትልቁ ቱኩረታችን ይሆናል። አራተኛ አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናት ብለው ነበር። ከሁለት አመታት በፊት። አማራ ሁሉም ኢትዮጵያ አገሩ ነው፤ በሁሉም ቦታ በሰላም ሰርቶ በነጻነት መኖር አለበት የሚለው ደጋግመው የተናገሩት ነው።
ሰሞኑን ትልቅ ሰቆቃ እያየንባቸው ካሉ አካባቢዎች መካከል አንዱ የአርሲ ዞን ነው። በአርሲ ዞን ቢያንስ 20% የሚሆነው ነዋሪ ራሱን አማራ ብሎ የሚጠራ ነው። የአማራና የኦሮሞ ድብልቁ የሆነ ግን ኦሮሞ ነኝ የሚለውን ከወሰድን ደግሞ ወደ 40% ይሆናሉ። በዚያ የሚኖሩ የሸዋ ኦሮሞዎች በዚያ ባሉ በአርሲ ኦሮሞዎች እንደ “አማራ” የሚቆጠሩ ናቸው። “አማራ” የሚባሉት የሸዋ ኦሮሞዎች ስንጨምር አብላጫ ቁጥር ነው የሚኖራቸው።
ይሄንን እንኳን ከግምት በማስገባት እነዚህ የቀድሞ አዴፓ አመራሮች በዚያ የሚኖረው የአርሲ ኦሮሞ ያልሆነው ሌላው ማሀብረሰብ (ከሸዋ የመጡ ኦሮምዎችን ጨምሮ) ደህንነቱ እንዲጠበቅለት፣ መብቱ እንዲከበርለት፣ ውክልና በዞኑ እንዲያገኝ ማድረግ አልቻሉም። በመሆኑም ይሄ ማሀረሰብ በአገሩ እንደ ጠላትና እንደ መጢ በጽንፈኛ እየታየ በአርሲ ጽንፈኛ ኦሮሞዎች እየታደነ ነው።
አሰላም ከተማን ውሰዱ። የአሰላ ከተማ ሕዝብ አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ ሆኖ፣ የከተማዋ ከንቲባ ግን ከአሰላ ውጭ የመጣች ጽንፈኛ የቀድሞ ኦህዴድ አሁን የብልጽግና አመራር ናት። የጃዋር መሐመድ ወዳጅና ደጋፊ። ብአዴን አዴፓዎች ይሄንን እንኳን እንዲሻሻል ማስደረግ አልቻሉም።
በአዲስ አበባ ከአርሲና ከባሌ የመጡ ጽንፈኞችን እነ አቶ ለማ መገርሳና፣ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስፍረው፣ አደራጅተው የአዲስ አበባን በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ማሀረሰባት ሲያሸብሩ እነዚህ አመራሮች ምንም ነገር ማድረግ አልቻሉም።
ደፍሬ ይሄን እላለሁ። እንደ አርሲ ባሉ ቦታዎች የአርሲ ኦሮሞ ባልሆኑት ላይ እየደረሰ ላለው ሰቆቃ ፣ ብአዴኖች/አዴፓዎች ሃላፊነት መውሰድ አለባቸው። ሰዉን ያስጨረሱት በተዘዋዋሪ መንገድ እነርሱ ናቸው። ምንም ነገር ባለማድረጋቸውና የኦሮሞ ጽንፈኝነት መረን ሲለቅ አደጋዉን ማየት ባለመቻላቸው፤ ወይንም ማየት ባለመፈለጋቸው።

4 COMMENTS

  1. ከፋፋይ አጀንዳ የወያኔ ፕላን ነው

    እውነት ለእነዚያ አማሮች የምትቆረቆር ከሆነ ጊዜው የወቀሳ ጊዜም አይደለም:: ከመግስት ጎን ሆኖ ህዝብ የማዳን ወቅት ላይነን;; ፖለቲካ የሚቆመርበት ወቅትም አይደለም::የሀገር ማፈራረስ ጦርነት ተጀምሯል:: ኢትዮጵያውያን ሰብሰብ ብለው ከዐቢይ ጎን ከመቆም ውጪ ሌላ አማራጭ የለም:: የአማራና ኦሮሞ መሪዎችን ለያይተህ የምታወግዘው ግቡ ወያኔን ከመመለስ ውጪ ሌላ ምንም እርባና የለውም:: እነሱ የአንድ የብልፅግና ፓርቲ አባል ነን: ኢትዮጵያውያን ነን ብለው ተነስተዋል:: የእናንተ ጠብ ጫሪ አጀንዳዎች ናቸው ለፅንፈኞቹ እሳትና ነዳጅ የሆኑት:: 27 አመታት ወያኔ የከፋፈላትና ዘርፎ ባዶ ያስቀራትን ሀገር መምራት እጅግ ብዙ ትእግስትና ድካም ይጠይቃል:: ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ናት:: ከሩቅ ሆኖ መተቸትና ማብጠልጠል ቀላል ሊሆን ይችላል:: በዚህ ወቅት ከመደገፍ ውጪ አሳዶ ለጠላት መስጠትና ውጤቱ ኢትዮጵያን ማዳከምና መበታተን ነው::ሀገር እየተቃጠለች ወገኖች እየተገደሉ የወያኔ ሴራ ጉዳይ አስፈፃሚ ነህ:: መልካም ኢትዮጵያዊ ትመስለኝ ነበር::

  2. እውነቱ እንዴት ነው ጉዳዩ ? ግርማ ካሳን ነው በዚህ መልክ የምታስተናግደው? እንግዲያው የአቻምየለህም አሳብ ይኸው ነው እሱንስ ምን ልትለው ነው? አብይን መደገፍ መብትህ ነው ነገር ግን ግርማ ካሳ ያለእረፍት ለሚታረደው ረዳት ላጣ ወገን የቆመውን ዜጋ ቢያንስ እውቅና ስጠው። አንተንም አይሀለሁ የሀገርህ ጉዳይ እረፍት ከነሱህ መሀል አንዱ ነህና። ተከቧበሩ ተናበቡ

  3. ኦሮሞ በሚባለው ክልል ውስጥ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው ዜጋ በፅንፈኞች መብቱ ተረግጦ ነው ያለው። ይህን መብት ለፅኖፈኞች የሰጣቸው ወያኔና ኦነግ የሸረቡት ህገ መንግሰት ነው። ህገመንግስቱ ለዜጎች ሳይሆን ብሄር ለሚሉት የተፃፈ ነው

  4. ወንድሜ ሰመረ

    ላንተ እክብሮት ስላለኝ ነው መልስ የምሰጥህ:: ባሁኑ የጦርነት ወቅት ለተራ የፖለቲካ ሂሳብ ማወራረጃ ጊዜ አይደለም:: አማራው አልተደራጀም :አልታጠቀም:: እራሱን መጠበቅ አይችልም:: የሚጠብቀው ወደንንም ጠላንም መንግስት ነው:: መንግስት ያለ ህዝብ ድጋፍ የጠላት ሰለባ ይሆናል::ሀገር ስትፈረስ እንደ በግ የሚታረደው በመላው ኢትዮጵያ ተበትኖ የሚኖረው አማራ ነው:: በዚህች ወቅት ዐቢይ ተወደደ አልተወደደ ኢትዮጵያዊው በሙሉ ሀገር ለማዳን ከዐቢይ ጋር መቆም አለበት:: በኢሬቻ በዐል ንግግሩ ሺመልስ አብዲሳን ጠልቼው ነበር:: ሆኖም ዛሬ በወያኔ ላይ በሚያደርገው ዘመቻ እንደ ኢትዮጵያዊ አብሬው እቆማለሁ::ዛሬ የሺመልስ አቋሙ ከ አብን ጋር አንድ ነው::ሀገር ከኮንዶሚኒየም ታከለ ኡማና እስክንድር ነጋ ና ግርማ ካሳ በላይ ናት::ግርማ ካሳ የፈለገውን ይፃፍ ሆኖም በዚህ ወቅት መንግስትን መገዝገዝ ጥቅሙ ለአማራ ጠላት ህውሀት መሆኑ ነው::ዛሬ እሱን የመሳሰሉ በርቧሪዎችን ወያኔ በእጅጉ ይፈልጋል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.