የህዝቡ ዝምታ ያስፈራው ወያኔ ወጣቶችን እየለቀመ በማሰር ላይ ነው፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከምርጫ ጋር በተየያዘ በርካታ ሰዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ ከከተማዋ የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 11 ለም ተብሎ በሚጠራው ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በሃሰት እየተውነጀሉ በስርዓቱ ታጣቂዎች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ከትምህርት ቤቱ ከታሰሩት ተማሪዎች ውስጥ ተማሪ ሲራክ ለማ የተባለ የ9ኛ ክፍል ተማሪ፤ ያሬድ ፋሲል እና አላምረው ይደግ የተባሉት ደግሞ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችና ሌሎችም አምስት ተማሪዎች የሚገኙባቸው እንደሆኑ ሊታወቅ ተችሏል።

እነዚህ ተማሪዎች እናንተ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ስለሆናችሁ ለሌሎች ተማሪዎች ዓመፅ እንዲያስነሱና የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና አንፈተንም በሉ እያላችሁ ታነሳሳላችሁ ተብለው ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ከለም ትምህርት ቤት በፖሊሶች ተይዘው እንደተወሰዱ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገልፀዋል።

እንደዚህ አይነት ህጋዊ ያልሆነ ተግባር በለም ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን እየታየ ያለው በሁሉም የሃገራችን ሃይስኩል ትምህርት ቤቶች እየተፈፀመ ያለ እኩይ የስርዓቱ መገለጫ ባህሪው እንደሆነ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ አክሎ አስረድቷል።

አሰግድ ታመነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.