ለሻሸመኔው እልቂት ተጠያቂው ሸኔ ሳይሆን ብልጽግና ውስጥ ያሉ ጽንፈኞች ናቸው – ግርማ ካሳ

ከአንድ አመት ተኩል በፊት ፣ “ሻሽመኔ በአክራሪ ኦህዴዶች እስከተዳደረች ድረስ የሚለወጥ ነገር አይኖርም” በሚል ርእስ ስር፣ በሻሸመኔ ጽንፈኞች አንድ ሽማግሌ የሙስሊም አባትን መሬት ላይ ጥለው ፣ ሲወግሩና ሲደበድቡ የሚያሳይት ቪዲዮን አያይዤ ለጥፌ ነበር፡፡
ይኸው በድጋሚ ሻሸመኔ ሌላ በጣም የከፋ ሰቆቃ አስተናግዳለች፡፡ ሻሸምኔ እንዳለ በጽንፈኞች ወድማለች፡፡ አሌፖ ሲሪያ ሆናለች፡፡
መንግስት ኦነግ ሸኔ ያደራጃቸው ናቸው ይሄን ያደረጉት ይላል፡፡ ለሁሉም ነገር ሸኔ ጥፋተኛ እየተደረገ ነው፡፡ ቀላሉ እርሱ ስለሆነ፡፡ ሆኖም ይሄ የመንግስት ጣት ቀሰራ አልተዋጠልኝም፡፡
ሸኔ በአገራችን ችግር ፈጣሪ እንደሆነ የሚካድ አይደለም፡፡ በወለጋ የተማሪዎች መታገት፣ ወለጋና ጉጂ የጦርነት ቀጠና እንዲሆኑ በማድረግ በአካባቢው ህዝብ ላይ ትልቅ ችግርን እየፈጠረ ያለ፣ መሸነፍና መደምሰስ ያለበት ቡድን ነው፡፡
ሸኔ ማለት የዳዎድ ኢብሳ ኦነግ የዉትድርና ዊንግ የነበረ ማለት ነው፡፡ ብዙዎች ላያወቅቱ ይችሉ ይሆናል፤ ሸኔዎች ሆነ እነ ዳዎድ ኢብሳ ከነጃዋር መሐመድ ጋር ችግር ያለባችው ሰዎች ናቸው፡፡ በተለይም ሸኔዎች እንኳን ለነጃዋር ክብር ሊኖራቸው፣ በማንኛውም ጊዜ እርምጃ ሊወስዱባቸው እንደሚችሉ የታወቀ ነው፡፡
የጃዋር ኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ (OMN) ወለጋ ስላለው እንቅስቃሴና ስለ ሸኔ ብዙ አይዘግብም ነበር፡፡ አቶ ዳዎድ ኢብሳ በOMN የቀረቡበት ጊዜ ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ OMNን በመቃወም፣ በዋናነት ወለጋዎች ያሉበት የኦሮሞ ኔትዎሮክ ኒዩስ (ONN) የሚል ሜዲያም ተቋቁሟል፡፡ የዳዎድ ኢብሳ ኦነግ፣ ከኦብነግና ሌሎች ድርጅቶች ጋር “ትብብር” የሚባል ጥምረት ሲመሰርት፣ OMN ን ሳይሆን ONN ነበር የዘገበው፡፡ OMN ለነ አቶ ዳዎድ ኢብሳ ኦነግ ሽፋን መስጠት ብዙም አይፈልግም፡፡ እንግዲህ ይሄ በራሱ አንድ የሚያሳየን ነገር አለ፡፡
ሸኔ የሚንቀሳቀሰው በዋናነት በወለጋና በጉጂ ነው፡፡ በአርሲ፣ ሃረርጌ፣ ባሌ፣ ከሚሴ በመሳሰሉት ሸኔ የለም፡፡ ያ እንደሆነ በታወቀበት ሁኔታ በነዚህ ቦታዎች ግፍ የፈጸመው ሸኔ ነው ማለት እውነትን ከሕዝብ መደበቅ ነው፡፡ ወለጋና ጉጂ ስላሚሆነው ሸኔን መክሰስ ያስኬዳል፡፡ አርሲና ባሌ፣ ሃረርጌና ከሚሴ ስለሚሆነው ግን ሸኔን መክሰስ አዋጭ አይደለም፡፡ (በነገራችን ላይ ላይ ከዚህ በፊት በአጣዬ ለተፍጠረው እልቂት ፣ ኦነግ እንደሆነ ተገልጾ ነበር፡፡ አዎን ኦነግ ነበር፡፡ ብዙ ኦነጎች ናቸው ያሉት፡፡ በዳዎድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ሳይሆን አርሲና ባሌ ካሉ እስላማዊ ኦነጎች ጋር ግንኙነት ያለው ኦነግ ነው)
ገዢው ፓርቲ ነገሮችን ከማድበስበስ ይልቅ የችግሩ ዋና ምንጭ ላይ ማተኮር ያለበት ይመስለኛል፡፡
እንደነ አርሲ ባሉ ቦታዎች የሚንቀሳቀሰው ሸኔ ሳይሆን ሌላ፣ እነጃዋር የሚመሩት የተደራጀ የጽንፈኛ ቡድን አለ፡፡ ይሄ ቡድን ከዳዎድ ኢብሳ ኦነግ የተለዩ በአብዛኛው የነጃራ ተከታይ እስላማዊ ኦነጎች ፣ በኦፌኮ ውስጥ ያሉ አክራሪዎች እንዲሁም በትልቁ ሊሰመርበት የሚገባ በኦህዴድ አሁን ደግሞ የኦሮሞ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አባላትንና የተወሰኑ አመራሮችን ያቀፈ ቡድን ነው፡፡ አዎን እዚህ ቡድን ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ አለበት፡፡ ያ እንዳይታወቅም ነው፣ ችግሩን externalize በማድረግ ከችግሩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን ሸኔ ተጠያቂ በማድረግ በሻሸመኔና በዝዋይ፣ በከሚሴና በሃረርጌ ለሆነው ነገር ጣት እየቀሰሩ ያሉት፡፡
የኦነግ ሸኔ ጉዳይ እልባት እያገኘ ነው፡፡ መከላከያ እየወሰደ ባለው እርምጃ በወለጋና በጉጂ አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ ነው፡፡ እነ ጃል መሮም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወይ እጅ ይሰጣሉ አሊያም ይደመሰሳሉ፡፡ ሆኖም ግን ትልቁና አሳሳቢ የሆነው እነ ጃል መሮ ከፈጸሙት የባሰ ግፍና ሰቆቃ እየፈጸመ ያለው፣ አብዛኞቹ አባሎቻቸው የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የተሰገሰጉ፣ የጽንፈኛው ቡድን ነው፡፡
ስለብልጽግና ይሄን ስናገር አንዳንድ የዶር አብይ ደጋፊዎች ሊከፉ ይችላሉ፡፡ ግን የምንጽፈዉና የምንናገረው ዶር አብይ አህመድ የርሱን ድርጅት እንዲያጸዳ ነው፡፡ በብልጽግና ውስጥ አመራሮች ጋር ሳይቀር ሰርጎገቦች፣ ላይ ላዩን ኢትዮጵያ እያሉ ውስጡን ውስጡ የዘረኝነት አጀንዳ የሚያራመዱ፣ በአቶ ለማ መገርሳ የተሾሙ ብዙ አሉ፡፡
እስቲ አስቡት ሻሸመኔ ስትወድም፣ የፖሊስና የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይሎች ለምንድን ነው ከተማዋናን ሕዝቡን መታደግ ያልቻሉት ? መመሪያ አልተሰጠንም ይላሉ፤ ባይሰጣቸውስ ዝም ማለት ነበረባቸው ወይ ? ደግሞ መመሪያ ለምን ከአመራሮች አልተሰጣቸውም ? የኦሮሞ ክልል ፖሊሶችንና ልዩ ኃይላትን የሚመሩት፣ የሚያሰማሩት፣ መመሪያ የሚሰጡት እነ ማን ናቸው ? የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች አይደሉም ? በተፈጠረው የዘር ማጽዳት ወንጀሎችና ሰቆቃዎች ሰዎችን የብልጽግና ፓርቲ ላይ ጣታቸውን ቢቀስሩ ትክክል አይደሉም ?
ከአንድ አመት በፊት እንዳልኩት አሁን ደግሜ እላለሁ፡፡ በተመለከተ ችግሩ ያለው ኦህዴድ ጋር ነው፡፡ ወይም የኦሮሞ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው የኦሮሞ ክልል መስተዳደር ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው በኦሮሞ ክልልያሉ የዞንና የወረዳ መስተዳድሮች ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጋር ነው፡፡ ችግሩ ያለው እነዚህ መስተዳደሮች የሚመሩበት የዘር ፖለቲካው ጋር ነው፡፡

5 COMMENTS

 1. እግዜር ይስጥህ የተሟላ መረጃ ነው በርግጥም ሻሸመኔ ውስጥ እነዛን ከወደቁ በሀዋላ የእዛውንት እስላሞችን ጭንቅላት እንደ ኲዋስ ይጠልዙ የነበሩ እርኩስ ቄሮዎችን ለእይታ ማብቃትህ ምስጋና ይገባሀል። ለዛ ክስተት አህመዲን ጀበል የሰጠውን ወራዳ ምላሽ በጊዜው የጻፈውን ጎግሎ መመልከት ነው።

 2. Ban ethnic parties ! Dismantle kililization based on ethnicity as it is now !
  The genesis of ethnic hate and strife originated mainly, by order of intensity, from Tigray and Oromia . So the regionalization of the two states must be re -engineered for the sake of survival of Ethiopia once and for all. Regions should not have ethnic identity nor ethnic belongingness. Period. What do you think fellow Ethiopians ?

 3. Zega

  Amara is so involved in politics . Most people from other ethnicities are not so political savy as Amaras.

  Without the constitution or without the current regional demarcations or without ethnic federalism for sure we Ethiopians will go back to the aristocrats rule of one ethnic Amara taking over with other ethnic cities being colon zed by Amaras , we will not let that happen.

 4. Ayte Daniel,
  How long can we afford to live by chopping each other in the most barbaric manner as we witness the acts now ? Can you suggest a solution ? a frame work under which mutual respect and co-existence could occur among brotherly peoples ? Your problem seems to be more of psychopathic than political , in which case you and your likes need appropriate psychological therapy.
  The Ghost of Menelik is hovering over you.
  Sane mind would not think of aristocracy at the 21 Century. !!ምስኪኖች !!

 5. እስከአሁን ለ3 ዓመት ያየነው ጭፍጨፋ ከኦነግ እራስ አይወርድም፡፡ የማደናገሪያ ሥም እየተስጠ ከተጠያቂነት ባንሸፋፍናቸው ጥሩ ነው፡፡ ኦነግ ታሪካዊ ዘረኘነትና አረመናዊ ጭፍጨፋቸው ኢትyoጵያዊነት ጥላቻቸው ወረቀት ላይ በማስረጃ ማህደር ውስጥ መኖሩን ክማንም ጋር የሚያከራክር አይደለም፡፡ ኦነግ ሽኔ እያላችሁ አትቀባጥሩ፡፡ እነሱ መቺም የሚሰለጥኑ መቼም በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ አይደሉም፡፡ በፓለቲካ እርቅ ሰበብ አገር እያጠፉ ነው፡፡ በፓለቲካ ይቅርታ ሲገቡ እውነት የተለወጡ መስሎኝ ለኦሮሞ ህዝብ የፕለቲካ ተሳታፊነት እድል ያመጣሉ በማለት ተሰፋ ነበረኝ፡፡ ውለው ሳያድሩ ኦሮሞ መጀመሪያ ኢትዮጵያንማ ስሟንም መጥራት አይፈልጉም፡፡ ለእነዚህ መሞኘት አይስፈልግም፡፡
  የአቢይ መንግሥት የማያዳግም ማሰጠንቀቂያ መስጠት አለበት ጭራቅነታውችውን መተው ካልፈለጉ ግ ን እዛው በረሃቸው እየተሰደዱ ሽብራቸውን ይቀጥሉ፡፡ ወያኔ ሸሆናቸውን ቆርጦ ነው በረሃ ያስገባቸው፡፡ አሁንም ያለው አማራጭ ይሄው ነው፡፡ ጋኔን የተጠናወተው ድርጅት ነው፡፡ አሁን ደግሞ ስማቸውን ማስክ አልብሰው ሸኔ ፤ ቄሮ እያሉ ያወናብዳሉ፡፡ አብይ ብልጥ ከሆነ ለአገር ደህንነት ሲባል እነሱን ነው አንድ በአንድ መልቀም ያለበት፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.