ተስፋ የቆረጡ የቦሊቪያ ዜጎች አስከሬኖችን በየጎዳናው እያስቀመጡ ነው

 በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ባለባት የቦሊቪያዋ ትልቋ ከተማ ኮቻባምባ በርካታ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመቅበር ቀናት መጠበቅ ግዴታ ሆኖባቸዋል አንዳንዶቹም በቤታቸው ውስጥ አስከሬኖችን ለቀናት ማስቀመጣቸው ለበለጠ ጭንቀት ዳርጓቸዋል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ አንዳንዶች ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ተገደዋል። በባለፈው ሳምንት እሁድ የሞተው የ62 አመቱ ግለሰብ ዘመዶች አስከሬኑን በጎዳናው ላይ ለሰዓታትም አስቀምጠዋል።

በማዕከላዊ ከተማዋ 600 ሺህ የሚጠጉ ነዋሪዎች ያሉ ሲሆን ባለስልጣናቱም አስራ ሰባት አስከሬኖችን በቀን እየሰበሰቡ እንደሆነም አስታውቀዋል።

በከተማዋ ዋና መካነ መቃብርም መጨናነቅ ተፈጥሯል ተብሏል። የከንቲባው ፅህፈት ቤት በርካታ የመቃብር ስፍራዎችን እየቆፈረ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን ይህ ግን ባለው ተቃውሞ እንደተፈለገው ሊሳለጥ አልቻለም።

የተቃውሞው መነሻም አስከሬን ያስቀመጡ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንጠቃለን በሚል ስጋት ነው።

መቃብር ቆፋሪዎች በበኩላቸው በኮሮናቫይረስ ለሚሞቱ ሰዎች የተለየ መካነ መቃብር እንዲዘጋጅ መንግሥትን ጠይቀዋል።

BBC Amharic

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.