የኦሮሚያ ብልጽግና ህይወት ለማራዘም እንደ ጭዳ / Buffer/  የቀረበ የመስውአት ህዝብ – ያሬድ ከፍያለው

በቅርቡ ኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በንጹሃን አማራዎች፣ ጉራጌ እና የሸዋ ኦሮሞዎች ላይ የተፈጸመው ጂኖሳይድ መነሻ የሆነው ዘረኝነት ውሃ እያጠጣና እየኮተኮተ ያሳደገውን አካል ማወቅ የችግሩ መፍትሄ ግማሽ መንገድ  እንደሆነ አምናለሁ።    በእኔ ምልከታ በአሁኑ ወቅት ባለው ሁኔታ የችግሩ ዋነኛ ተጠያቂ  የዶክተር አብይ የተዝረከረከ አመራር ነው። ዶ/ር አብይም ሆነ አመራሩ አሁን በኦሮሚያ የተከሰተውን የግፍ እርድ/ Genocide /  በሙሉ ልብ ሲኮንኑ አልታየም። እሱም ሆነ ግብረአበሮቹ ድርጊቱን ሲጠሩት እንኳን ግጭት ኣያሉ አቃለው ነው።

የሰፈር ጸብ አይነት። ጂኖሳይድን ግጭት ብሎ መጥራት ደግሞ እንዲከሰት እንደማበረታታት ይቆጠራል። አመራሩ ቁጭት የሚባል አልፈጠረበትም። እንደውም የኦሮሞ ወጣት በኦህዴድ ላይ ያለውን ቁጣ  አሌያም በፈጠራ የተነገረውን የሚኒሊክ ጡት ቆረጣ ቂም እንዲወጣበት ሆን ተብሎ በኦህዴድ እንደ ንዴት ማብረጃ የተተወ ህዝብ  ነው:: የኦሮሚያ ብልጽግናን ህይወት ለማራዘም እንደ በፈር / Buffer/  የቀረበ የመስውአት ህዝብ።   እንደምናየውም ወጣቱ ቁጣውን በንጹሃን አማራዎች፣ ጉራጌ እና የሸዋ ኦሮሞዎች  ላይ ተወጥቶ  ጃዋር የሚባል መሪውን ይፈታ የሚለውን ጥያቄውን እንኳን እረስቶ በእርካታ  ወደ ጫት፡ ጠላና ጠጅ ቤቱ ተመልሶአል። መቼም ቤተሰብ የሚመራ ሰው ሰውን በዚህ መልክ ከታትፎ ይገላል ብሎ  የሚከራከር እይኖርም። በቀጣይስ አንድ ባለስልጣን ቢገደል? ዳውድ ኢብሳ፣ ጃዋር፣ አብይ ወይም ሌላ። አብይ እንዳለው በአንድ ለሊት 100 ሺህ ሰው ገብሮ ማልቀስ  ይሻለናል? በመጀመሪያ ዶ/ር አብይ የሁሉም ጠቅላይ ሚኒስትር መሆኑን ማመንና ችግሩ ከተዝረከረከው አመራሩ የመነጨ መሆኑን መቀበል ይኖርበታል። እነዚህን ጨካኝ አራጆች፥ አስተባባሪዎቻቸው እና በዝምታ ያዩትን ባለስልጣናት ለጂኖሳይድ በሚመጥን መልኩ ለተጎጂዎችና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ግልጽ በሆነ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲቀጡ በማድረግ ማሳየት ይጠበቅበታል።

ዶ/ር አብይ እኛ ዝሆን ነን እንሰብራለን፣ እናደቃለን እንዲሁም እኔ ላይ ግድያ ቢፈጸም በአንድ ለሊት 100 ሺህ ህዝብ ይገደላል የሚል ሸር የታከለበት ክፋት ትቶ እንዲስተካከል ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል።  የአብይ አስተዳደር  አንዳች ሸር ያዘለ  መሆኑን የሚያሳይ ሌላው ማሳያ ደግሞ በቡራዩ በጋሞዎች፤ በአዋሳ በንጹሃን ላይ እንዲሁም  ከዛሬ አንድ ዓመት በፊት በጁዋር መሃመድ የፌስ ቡክ ጥሪ በትንሹ 86 ሰዎች ግድያ ሲፈጸም ጉዳዩን የያዘበት መንገድ ነው። በተመሳሳይ እነዚህንም አንገት እስከመቁረጥ ጭካኔ የታየባቸው ጥቃቶች ግጭት እያለ ነበር ሲጠራ የነበረው።

በመጨረሻም ገዳዮቹን ተጠቂዎች በሚታዘቡት ግልጽ ፍርድ ቤት በማቅረብ ከማስቀጣት ይልቅ ጉዳዩን አድበስብሶት አልፎአል። ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ዘርን  መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በሚገባ የተገነዘበውና መንግስትን ሲያስጠነቅቅ የነበረው እስክንድር ነጋ  ላይ የተወሰደው የእስር እርምጃም ሌላው ማሳያ ነው።  የቅርቡ   የጂኖሳይድ ጥቃት የእስክንድር ፍርሃት ነበር። የአብይ መንግስት ግን ለመስማት ፍላጎት አልነበረውም። እስክንድር እንዳለው ይሄ እራሱን ቄሮ ብሎ የሚጠራው ቡድንና አመራሩ በሽብርተኝነት ቢፈረጅ ኖሮ ይህን ጥቃት መከላከል በተቻለ ነበር። ታዲያ እስክንድር እንደመሰማት መታሰሩ ምን ተብሎ ይጠራ?  አውቀን ካልተኛን በቀር ደግሞ ከነዚህ ማስረጃዎች በላይ የአብይ አስተዳደር በተኩላዎች የተሞላ ለመሆኑ ማስረጃ የለም። አውቆ መተኛት ደግሞ ለወደፊት  ገዳዮቹን በመቶ ሺዎች እንዲገሉ እንደማበረታታት ይቆጠራል።

1 COMMENT

  1. በአደባባይ ነፍጠኛን ሰብረነዋል እያሉ ቅስቀሳ የሚያደርጉ ሰወች ናቸው ኦሮሚያ ተብሎ የተከለለውን አካባቢ የሚመሩት። ሁሉ ኬኛ : ግደለው :ቂረጠው : የሚሉ ፖለቲከኞች ናቸው የመንግስትን መዋቅር የሚቆጣጠሩት። ንፁሀን ዜጎች በፅንፈኞች ሲታረዱ ሲጨፈጨፉ ከላይ ሆነው የዘር ማፅዳት ግድያውን ሲመሩ ሲያቀናብሩ የነበሩት እነዚህ አመራሮች ናቸው። አሁንም ፍትህ እንሻለን። አቢይ አህመድ በጉያው ሸጉጦ የያዛቸውን እነዚህን ግለሰቦች ለፍርድ ማቅረብ አለበት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.