‹‹መቶ አሥር የማይሞሉ ግለሰቦች መቶ አሥር ሚሊዬን ሕዝብን እንዲበጠብጡ ልንፈቅድላቸው አይገባም› አቶ ታዬ ቦጋለ የታሪክ መምህርና ደራሲ

አቶ ታዬ ቦጋለ የታሪክ መምህርና ደራሲ

አዲስ አበባ፡- መቶ አሥር የማይሞሉ ግለሰቦች መቶ አሥር ሚሊዬን ሕዝብን እንዲበጠብጡ ልንፈቅድላቸው አይገባም ሲሉ የታሪክ መምህርና ደራሲ አቶ ታዬ ቦጋለ አሳሰቡ። አገር እንዳትፈርስና የሕዝቦች መስተጋብር እንዳይበጠበጥ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመሆን ለሕግ መከበር የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ጥሪ አቀረቡ።

የታሪክ መምህሩ አቶ ታዬ ቦጋለ ትናንት በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታውቁት፣ ኦነግ ሸኔና ሥልጣን ናፋቂው ህወሓት አገር ከተረጋጋች የሠሩት ወንጀል ስለሚጋለጥ አገር እንዳትረጋጋ ሌት ተቀን እየሠሩ ነው። ከተጠያቂነት ለማምለጥ ህዝቡን በጭንቀትና በሽብር ውስጥ አድርጎ መኖር አላማቸው በመሆኑ ህዝቡ ሊታገላቸውና መንግሥትም በሕግ ሥር ሊያደርጋቸው ይገባል።
ኢትዮጵያ በተጎዳች ቁጥር ቅድሚያ ተጠቂው የኦሮሞ ህዝብ ነው የሚሉት የታሪክ መምህሩ፣ ሽፍታንና አሸባሪን መደበቅም ሆነ መርዳት የኦሮሞ ህዝብ ባህል ባለመሆኑ ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠቱ ሂደት ላይ ግንባር ቀደም መሆን አለበት ብለዋል። ሕግን የማስከበሩ ሂደት ደግሞ የህዝብና የመንግሥት የጋራ ሃላፊነት መሆኑንም አመልክተዋል።
አቶ ታዬ እንዳሉት ህዝቡ በሁሉም ቦታ እየተጎዳ ነው። በርካታ ባንኮች ተዘርፈዋል። በአሸባሪው ቡድን ሴቶች ተደፍረዋል። ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ፅንፈኛ ሃይል ከህወሓት ጋር በመሆን ከግብጽ የሚሰጠውን ተልዕኮ እውን በማድረግ ሀገራችንን ከህዳሴው ጉዞ ለማደናቀፍ ያለ እንቅልፍ እየሠራ ነው። ህዝብ ወንጀለኞችን ከመሸሸግና መንግሥትን ከመተቸት ተቆጥቦ አሸባሪዎችን ማጋለጥና የሰላም አየርን መተንፈስ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
እንደ ሻሸመኔ ያሉ ከተማዎች ከ75 በመቶ በላይ ያፈራረሰ ጠላትን፣ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማደናቀፍ የሚሞክር ሃይልን፣ ንፁሐንን በቤታቸው የገደለና ተልዕኮ በመቀበል ሀገርን ለውጭ ጠላት አመቻችቶ ለመስጠት የሚደራደር ሽፍታ ላይ የተወሰደው እርምጃ በጣም አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው፣ መንግሥት መተቸት ካለበት እየወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም ተብሎ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል። ሁሉም ሰው ከሕግ በታች ሆኖ ሊዳኝ ይገባዋል።
መንግሥት እንዲጠነክር ህዝብ ሌት ተቀን ከጥፋት ሃይሎች ጋር ሳይሆን ከመንግሥት ሃይሎች ጋር መሥራት አለበት። ሁከት የሚፈጥሩ ሃይሎች በቁጥር የሚቆጠሩ በመሆናቸው በቀላሉ በቁጥጥር ሥር አውሎ ሀገርን ወደ መገንባት መሸጋገር ይገባል ብለዋል።
የፈሰሰው የንፁሃንና የህፃናት ደም ሳይደርቅ ወንጀለኞች ታሠሩ ብሎ ለመጮህ ርህራሄው ከየት መጣ ብለው የሚጠይቁት የታሪክ መምህሩ፣ ማህበራዊ ግንኙነቶችን አሻክረው፣ የእምነት ቦታዎችን አቃጥለው፣ የደሀ ንብረት ሲወድም ቁመው የተመለከቱ የጥፋት ሃይሎች የመንግሥትን አገር የማረጋጋት እና ሕግ የማስከበር ሥራን ለማደናቀፍ በጅምላ እያሴሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ይሄ አሳፋሪ ድርጊት ነው ያሉት አቶ ታዬ፣ አገር ለሚያተራምሱ ወንጀለኞች ጥብቅና ለመቆም የሚሞክር ከሴራዎች በስተጀርባ እጁ ያለበት አካል ነው። ‹‹ከእኔ ጀምሮ ማንኛውም አገር ወዳድ የኦሮሞ ህዝብ መንግሥት እርምጃ ወሰደ ብሎ አይከፋም። በጥቂት ሃይሎች አገር በዚህ ደረጃ መውደሟ አሳዛኝ ነው›› ብለዋል።
‹‹ሰላም ያሰፍናል ተብሎ እምነት የተጣለበት የፀጥታ ሃይል የወንጀሉ ተባባሪ ባይሆን ይህ ሁሉ ውድመት አይመጣም። መንግሥት ለሀገር ይሠራል ብሎ ከፌዴራል እስከ ዞንና ወረዳ ድረስ ያስቀመጠው ባለሥልጣን የጥፋት ተባባሪ ባይሆን ኑሮ በዚህ ደረጃ ችግር አይደርስም ›› ያሉት አቶ ታዬ፣ በቅድሚያ በዝረፊያና በግድያ የተሰማሩ አካላትንና ተባባሪዎችን መንጥሮ ማውጣት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
ሕዝብም ሳይታለል ከመንግሥት ጎን ቁሞ የጥፋት ሃይሎችን በሕግ ጥላ ሥራ ማድረግ አለበት። በርካታ ሥራ አጥ ባለበት አገር ወንድሙ የሚሠራበትን ሆቴል ማቃጠል፣ የሚዝናናበትንና ገቢ የሚያገኝበትን ከተማ ማውደም የጥፋቶች ቁንጮ ነው። በዚህ ጊዜ ሕዝብ ከመንግሥት ጋር በመሰለፍ አገርን የማስቀጠል ታሪካዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንደሚኖርበት አመልክተዋል።
በሞገስ ፀጋዬ
ፎቶ ሀዱሽ አብርሃ
(አዲስ ዘመን ሐምሌ 5 2012 ዓ.ም)
Image may contain: 1 person, standing
Meles Bisrat, Brook Zenebe and 161 others
74 Comments
28 Shares
Like
Comment

Share

1 COMMENT

 1. Underestimating the dire situation or “ADBESBISO MALEF” is what got us to this disasterous stage in the first place. We talk about developmental economy developmental construction-monument but when it comes to the development of children’s minds very little had been talked about in the last three decades which directly resulted in the disaster we are in.
  We should not sugar-coat it but we should open up, recognize , identify and admit the seriousness of the problem . In my understanding “Limat” means development. Limatawi EPRDF or developmental EPRDF had been talking about limat for decades. Now the question is what kind of development are we talking about? Most of the Oromo society including the PM himself while in bed thinks development means or translates to having as much babies as possible. Whoever is giving birth the most amount of children is considered as the most developed by most Oromos or by almost all other ethnic groups of Ethiopia.

  Then when we step into the house of federation the EPRDF PP takes measures for development by counting double digits economic growth , dollars borrowed from China IMF.. or number of high rise buildings it built or the majority considers development as the number of children got born .We currently do not even know for sure whether there are one hundred and ten million people or eighty million people or one hundred forty million Ethiopians because census count had been routinely postponed as if it is a thing to do.The way it is going census count is not getting the priority it deserves anytime during this lifetime.

  The society gets married, with some muslims each husband marrying ten wives at the same time and having babies non stop because that is what development translates to the people eventhough raising children is becoming extremely difficult for parents because both parents work many hours to feed their children, the children are left to grow up without proper role model guiding them as they grow up.

  When children go to schools colleges you find Professors such as Merira Gudina or Bekele Gerba teaching the children or until two decades ago people were being thought in schools by shabiya agents teaching students to Down Down Ethiopia formally in Ethiopian schools ,back then when children complain about their “down down Ethiopia” Shabiya teachers then the children get expelled from school by the shabiya teachers , with the students geting kicked out put out of school for resisting down down Ethiopia teachings and most of the time end up disowned by their family wrongly accusung their children of being a lazy backward undeveloped student because at the time no parent believed there are teachers intentionally teaching their students to down down Ethiopia in Ethiopian schools , most parents thought they have a liar child who defames the teachers. Until 1998 Shabiya thought in schools within Ethiopia for the students to act savagely against each other, shabiya tried to convince students that down downing each other in a society means building hard working competitive society, means development or means competitive capitalism , those students who let down down Ethiopia teachings to marinate in their brains believing that is what competitive capitalism development is all about graduated from schools with distinctions then went to become leaders and became teachers themselves holding key positions in EPRDF. Those who opposed such teachings are labeled lazy damn and had been ridiculed by the limatawi EPRDF most ended up in jails or in exiles with no contact from their parents or from their family members for being lazy backward damn who no Ethiopian wants to listen to what they got to say.

  Building high rise buildings and borrowing billions of dollars from the west should not have been the only measure of development or having as many kids should not have been the measure of development, what development translates to is being able to understand, communicate, build thrust amongst each other within a family or within a society which is a measure Ethiopia is least developed with this measure of development.

  Just having gangs of kids, with each year new baby being born only for some parents not even remembering their own children names is what is bringing the disaster we are experiencing.Even those who know their children names don’t know anything about the child they brought into this world meaning there is a majority of the population which is a loose cannon society of 40 years or younger which tries to go on as a country without knowing what is in the minds of each other.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.