DOWN – DOWN እግዚአብሄር – DOWN – DOWN መንግሥተ ሠማያት – የጣሞኤል ብልግና ከሚክያስ

እግዚአብሄር አማራ ነው –  ሚካኤል ነፍጠኛ ነው

የሳጥናኤል ድፍረት – የብዔልዜቡል ጩኸት – የኢሩኤልዮም ድንቁርና – የጣሞኤል ብልግና ከሚክያስ

አቢይ ጾም ነው፣ ምዕመናን ያስቀድሳሉ፣ ቀሳውስት ይጸልያሉ፣ ሁሉም ወደ እግዚብሔር አንጋጦ ይጸልያል። አያ እንቶኔ ምን እንደነካቸው አይታወቅም ዛሬ ድክም ብሏቸዋል፣ ረሃቡም ጸንቶባቸዋል። ድንገት ነው አንድ ሃሳብ ወደ ዓዕምሯቸው ዘለቀና ሁለት እንቁላል ይዘው እታች ከምድር ትኩስ ውሃ የሚምቦቀቦቅበት ሠፈር አዘገሙ። እሥፍራው እንደደረሱ አረፍ ካሉ በኋላ ሁለቱን እንቁላል ትኩሱ ውሃ ውስጥ ከተቱት፣ ሃሳባቸው ሰው ሳያያቸው ቀቅለው ለመብላት ነበር። አንድ ባህያ እህል የጫነ ሰው ሲጓዝ አያ እንቶኔ የበሰለውን እንቁላል ልጠው ሊበሉ ሲሉ ያያቸዋል። እሮጥ ብሎ አጠገባቸው ሄደና አያ እንቶኔ – እንዴ ጾም ነው እኮ ምን እያደረጉ ነው” ይላቸዋል። ጉድ ጉድ ሠይጣን አሳስቶኝ ነው፣ ይገርማል ብለው እንቁላሉን ውርውር አደረጉት። አጋጣሚ ሆኖ በርካታ አጋንንት ይህን ያዩ ነበር። አንደኛው አጋንንት ሱሩቃየል የተባለው፣ አያ ይሄን አሰራርማ እኛም ዛሬ ነው የተማርነው፣ በእኛ አታማኽኙ” አላቸው። አንዳኔ ይገርማል፣ ሰውም አጋንንትን አዲስ መላን ሊያስተምር መቻሉ።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ – DOWN – DOWN – ተብሏል። አጋንንት ግን አዲስ የተማሩት – DOWN – DOWN ኢትዮጵያ – DOWN – DOWN አበሻ – ሚኒልክ አማራ ነው – አማራ ነፍጠኛ ነው – ከሚለው አስገራሚ መፈክር ነው። የብዙ ክፉ ሃሳብ ባለቤት የሆነው ሠይጣን ራሱ ይህን ዓይነቱን መፈክር አያውቀውም ነበር። ክልጅነታቸው ጀምሮ ሃሰት ተግተው ያደጉት ሞኞች – አላዋቂነት አስክሯቸው፣ ጨርቃቸውን ጥለው ወጥተው በምዕራብያውያኖቹ አደባባያት ቆመው – DOWN – DOWN ኢትዮጵያ፣ – DOWN – DOWN አበሻ – ሲሉ ነጮች ብቻ አይደሉም ሠይጣናት ራሳቸው ተገርመዋል። ኢዚቃዬል የተባለው ሠይጣን የማትፈርሰዋን ኢትዮጵያ ለምን ይሆን ትፍረስ ትፍረስ እያሉ የሚጮሁት ሲልበአድንቆት ጠይቋል። ሱሩቃየል የተባለው ሌላው አጋንንትምእንዴሚኒልክ ቅኝ ገዥዎችን አሸንፎ መላ አፍሪካን ነጻ አውጥቷል፣ ለምን ይሰድቡታልሲል በአግራሞት ጠየቀ። ይገባዋል እንኳን ሰደቡት” አለ አራዝያል በቁጭት፣ በእመብርሃን ስም ምሎ፣ ጊዮርጊስን አስቀድሞ አይደለም እንዴ እኛንስ ቢሆን ያስፈጀን” አለ፣ ስሜቱ እየተግደራደረው። ጡሩኤልዮም የተባለው አጋንንት ራሳቸው ቅኝ ገዥዎች ያላፈረሷትን ኢትዮጵያ በራሳቸው አደባባይ ላይ ቆመው ትፍረስ ሲሉ ይገርማል” ብሎ ተሳለቀ።

ይህን ከሚሰሙት አጋንንተ መሃከል በጥረኤል አንድ አዲስ ሃሳብ መጣለት። ጓደኞቼ ከነዚህ አላዋቂዎች አንድ አዲስ ነገር ተምረናል። ለምን እኛስ – DOWN – DOWN እግዚአብሄር – DOWN – DOWN መንግሥተ ሠማያት –  እግዚአብሄር አማራ ነው  – ሚካኤል ነፍጠኛ ነው  – እያልን አንጮኸምአላቸው። ሁሉም በሃሳቡ ተስማሙና መፈክሩን ለማሰማት አንድ ትልቅ አደባባይ መርጠው ተቃውሟቸውን ሊያስተጋቡ ፈጥነው ሄዱ። ደፋሩ ሳጥናዔል በከፍተኛ ድምጽ – DOWN – DOWN እግዚአብሄር – አለ፣ ሲያጓራ የሚያስፈራው ብዔልዜቡል – DOWN – DOWN መንግሥተ ሠማያት – አለ፣ ደንቆሮው የኢሩኤልዮም እግዚአብሄር አማራ ነው –  አለ፣ ባለጌው የጣሞኤል – ሚካኤል ነፍጠኛ ነው – አለ። ሌሎቹ አጋንንት እነሱን እየተቀበሉ መፈክሩን አስተጋቡ። ይገርማል አጋንነት እንኳን ከደካሞች፣ ከመሃይማንና ከደናቁርት አዲስ ነገር ያገኛሉ። ሠይጣን ከአያ እንቶኔ እንቁላል በወራጅ ሙቅ ውሃ መጥበስ ተማረ። በዚህ ሲገረም መሃይማን ከንቱ መፈክሮችን ይዘው ብቅ አሉ።

ለነገሩ ጥቂት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያጠል መሃይማን የማትፈርሰዋን እትዮጵያ – DOWN DOWN –  ቢሉ ትዝብት እንጂ አንዳች አይመጣም። ለመሆኑ – አብይ ጎጃሜ ነው፣ አብይ ጎንደሬ ነው – ብሎ መፈክር አለ እንዴክፋት ምን ያህል ቀስፎ ቢይዛቸው ነው እየበሉ እየጠጡ በአደባባይ እንዲህ የሚውገረገሩትትዕቢት ምን ያህል ወኔ ቢሰጣቸው ነው ነጩን በነፍጠኝነት አስፈርጆ የሚያስቀጠቅጣቸውወይ ዘመንስንት አስገራሚ ነገር ብቅ ይላል። እነዚህ ምስኪኖች ምን ያህል ሃሳብ ቢያልቅባቸው ነው – Down – Down ኢትዮጵያ – ማለታቸውይህ ድርጊት ላንዳንዶች ምናልባት የመኖርያ ፈቃድ ማግኛ ቲኬት ወይንም ቢራ መጠጫ ቦኖ ሊሆን ይችላል እንጂ ኢትዮጵያማ አትፈርስም። ኢትዮጵያ የእግዚአብሄርህ የቃል ኪዳን ሃገር ነች። ድብቅ አጀንዳን እውን ለማድረግ ሲባል ግፈኞች በአርሲ፣ ሻሸመኔ፣ ጅማ፣ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ወዘተ፣ ያስፈጸሙት የሕዝብ ሃብት ውድመትና የንጹሃን ዜጎች ዘግናኝ ግድያ እጅግ ያሳዝናል። እግዚአብሄር ግን የምስኪኑን ዋይታ ይሰማል፣ ግፈኞች ያፍራሉ፣ ኢትዮጵያ ኅልውናዋ አይናጋም።

ወገኖቼ ፖለቲካ ሳይንስ ነው። ለአጋንንት ከንቱ ሃስቦችን ማስታጠቁን ትተን እስኪ እውጭ ካለንበት ሃገር ጥሩ ጥሩውን እንደ ንብ እየቀሰምን ጠቃሚ ሃሳቦችን እያፈለላግን ዲሞክራሲን እንገንባ፣ ኢትዮጵያን ከድህነት፣ ሕዝባችንን ከእርዛት እናውጣ።

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፣ አሜን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.