የሓየሎም አገዳደል እጅግ የተጠና እና በተቀናጀ መልክ በህወሓት የተፈጸመ ነው

የቐዳማይ ወያነ መስራች የብለታ ሃይለማርያም ልጅ ሊላይ ሃይለማርያም ረዳ ዛሬም ስለ ህወሓት ድብቅ የግድያ ታሪኮችና ስለ ሓየሎም አርአያ አገዳደል ተጨማሪ መረጃዎችን ሰጥተውናል
 የሓየሎም አገዳደል እጅግ የተጠና እና በተቀናጀ መልክ በህወሓት የተፈጸመ ነው፤
 ከሓየሎም ጋር በጣም ቀረቤታ ስለነበረን አገዳደሉን አውቃለሁ፤
 ሓየሎም ከመገደሉ ሳምንት በፊት አንድ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ከሓየሎም ገዳይ ጋር አብረው ሂልተን ሆቴል ምሳ በልተዋል፤ እንደገና ሓየሎም ከመገደሉ ሶስት ቀናት አስቀድሞ ይህ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ከሓየሎም ገዳይ ጋር አብሮ ምሳ በልቷል፤
 ሓየሎም የተገደለ ቀን ሁለት የህወሓት ባለስልጣናት ከሚመሩት ቢሮ ወደ ሓየሎም ቢሮ ተደውሎ “ሓየሎም አለ፤ የለም” ብለው ጠይቀዋል፤ ከሰአት ደግሞ ሁለት ደህንነቶች ወደ ቢሮው መጥተው “ሓየሎም የት አለ?” ብለው ጠይቀው የለም ተብለዋል፤
 ሓየሎም በተገደለበት እለት እስከ 12፡30 አከባቢ ሂልተን አብረን ነበርን፤ ከአንድ ውይንም ከሁለት ሰአት በሁዋላ ተገደለ፤
 ሓየሎምን ሻዕብያ አስገደለው የሚባለው ውሸት ነው፤ በእርግጥ ገዳዩ ኤርትራዊ ነው፤ ነገር ግን ከስብሓት ነጋ የቅርብ ወዳጅ እና ከህወሓት ባለስልጣናት ጋር ቢዝነስ ይሰራ ነበር፤ ስለዚህ የሓየሎም ግድያ በህወሓት የተቀነባበረና የተጠና መሆኑ መታወቅ አለበት፤
 በህወሓት ቤት ከእነሱ ሀሳብ የተለየ ሃሳብ ያለውን ሰው ገድሎ ሀውልት ማሰራት በጣም የተለመደ ነው፤
 መስፍን ኢንጅነሪግን የገደሉት ራሳቸው ህወሓቶች ናቸው፤ ገድለው ሲያበቁ ደግሞ መስፍን ኢንጅነሪንግ ብለው በስሙ ትልቅ ካምፓኒ ሰየሙለት፣
 ዶክተር ኣታኽልቲ ቐጸላንም የገደለው ህወሓት ነው፤

3 COMMENTS

  1. አሁን ማን ይሙት ይህ አዲስ ወሬ ሆኖ ይወራል። ግልጽና የታወቀ ነገር ነው። ገና በበርሃ እያሉ ከህዋላ በገዳይ የወያኔና የሻቢያ ስኳዶች ተገለው አፈር የተመለሰባቸው ስንቶች ናቸው? ቤቱ ይቁጠረው ወይም የኤርትራ በረሃና የትግራይ ምድር ይቁጠረው። ወያኔ በከተማም ሆነ በገጠር ያስገደላቸው እልፍ ናቸው። ለምሳሌ የስለላ መረቡን ሃላፊ አቶ ክንፈን የገደሉት ራሳቸው ናቸው። ይህንም ለማስረዳት በቤቱ ከሞተ በህዋላ ብርበራ ያደረገው ራሱ መለስ ነበር። ግን ግድያው በሌላ ሰው ጠብ እንደ ተፈጸመ ተደርጎ ነበር ሁሉም ተሸፋፍኖ የቀረው። በሱዳን ዘምቶ የነበረውን ኮሌኔል ማን ገደለው? ለምንስ እናቱ አዲስ አበባ ድረስ ተንከራተው አስከሬኑን በዚያ አገኙት? የሃሎም ግድያ በወያኔ የተቀነባበረና ገዳዪን ገዳይ የገደለበት ጉዳይ እንደ ነበረ ይታወቃል። በአዲስ አበባ ሌላውን ኮሌኔል እና ሚስቱን የገደለው ማን ነው? ወያኔና ግድያ ተለያይተው አያውቁም። ኢያሱ በርሄን ማን ገደለው? ለምን ተገደለ? ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ሻቢያና ወያኔ የሚመሳሰሉበትን አንድ ነገር ልጥቀስና አሁን በመቀሌና በሌሎች ከተሞች ስለ ነበረው ወታደራዊ ትርኢት ሃሳብ አካፍዬ አበቃለሁ።
    በኤርትራ ኢብራሂም አፋ አካዳሚ – ሻቢያ ከገደለው በህዋላ ያቆመለት ሃውልት ነው። የሆለታ ገነት ጦር ት/ቤት በሃያሎም ስም መጠራቱም የሁለቱን ሃይሎች ገጽታ ግልጽ አርጎ ያሳያል። ዶ/ር ኣታኽልቲ ቐጸላ የተገደለው ኢትዮጵያዊነትን በማራመድ ነው። የሃያሎምም ግድያ ኢትዮጵያዊነትን መውደድ እና የኤርትራን መገንጠልና መልሶ መመዝበር በመቃወሙ ነው። ወያኔ የማፊያ ድርጅት ነው የምንለውም ለዚሁ ነው።
    አሁን ያለ የሌለ መሳሪያ አስታቅፎ ወጣቱን ትግራይ ልትወረር ነው አማራ መጣብህ። ሻቢያ ሊያጠቃህ ነው። የአብይ መንግስት ሊመታህ ነው እያለ ዘጥ ዘጥ የሚያረጋቸው ለጋ የሃገሪቱ ልጆች እጅግ ያሳዝኑኛል። የትግራይ ህዝብን በማታለል እድሜ ልኩን የተካነው ወያኔ የፈጠራና የማወናበጃ ስራው ዛሬም በእርጅናው አላቆመም። የሚገርመው ግን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ተቀምጦ ልክ እንደ ወንበዴነቱ ሰውን አሰልፎ እዩን ጀግንነታችን ኑና ግጠሙን ማለቱ ለራሱ መሰንበት አስቦ እንጂ ለትግራይ ህዝብ ደንታ እንደማይሰጠው የበረሃና የከተማ ታሪኩ ይመሰክራል። ገበሬን ከግብርናው ላይ በግድ ለጦር ያሰለፈ ሃይል ህዝቤ ተራበ ብሎ ቢጮህ ማን ይደርስለታል? በትግራይ ህዝብ ስምና ደም መነገድ መቼ ነው የሚያቆመው? የእነርሱ ልጆች ቻይና፤ አሜሪካ፤ አውሮፓና በሌሎችም ከተሞች ቤት ተገዝቶላቸው፤ የንግድ ሥራ ተሰቶአቸው እየተንደላቀቁ የገበሬ ልጆችን ለቅሞ ልዪ ሃይል በሚል ስም ለሞት ማሰናዳት እብደት እንጂ የጤና አይደለም። እኔ ለትግራይ ልጆች ጥሪ አለኝ የታጠቃችሁትን መሳሪያ የታፈነውን የትግራይ ህዝብ ከወያኔ ነጻ ለማድረግ ተጠቀሙበት። ትግራይን ማንም ሃይል የውጭም ሆነ የውስጥ የሚነካ የለም። የትግራይን ህዝብ ሊያጠቃ የሚነሳ ማንም ሃይል የኢትዮጵያ ጠላት እንጂ የትግራይ ህዝብ ጠላት ብቻ አይሆንም። የምንኖረውም አብረን የምንሞተው አብረን ነው። የወያኔን የውሸት ፕሮፓጋንዳ አትስሙ። ንቁ! በቃኝ!

  2. ማነህ አባቴ ትግሬ ጥቅሙን የሚያውቀው እራሱ ነው ሉመጥፕ የሚዥለውን ገምተህ ካልደነገትክ ተዋቸው። ቢያንስ አቦይ ስብሀትና ጌቸው ረዳ ሰክረው ሲወላገዱ ማየት እነሱ ጠግበው እንደበሉና እንደጠጡ ስለሚታሰባቸው ደስታ በደስታ ይሆናሉ። ከሚገባው በላይ መከርን የነሱ ልጆች አሞሪካና አውሮፓ ቻይና ነው የሚማሩት አልን ይሄ ካላነቃቸው ጥይት ያንቃቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.