በሰልፉ ላይ የተሳፉት የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላቱ ቀላልና ከባድ የጦር መሳርያዎችን ታጥቀው መታየታቸውን የቢበሲ ዘጋቢ ከመቀለ ገልጿል

ዛሬ ረፋድ ላይ በክልሉ ዋና ከተማ በመቀለ ጎዳናዎች ላይ በሰልፍ ሲጓዙ የታዩት ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱት የልዩ ኃይሉ አባላትና ሚሊሻዎች በከተማው ወደሚገኘው ስታድየም በመጓዝ ተሰብስበው ታይተዋል። በመቀለ ከተደረገው ከዚህ ወታደራዊ የሰልፍ ትዕይንት ባሻገር በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ጭምር መደረጉ ለማወቅ ተችሏል።

ቢሆንም ይህ ዛሬ የተካሄደው ወታደራዊ ሰልፍ ዓላማው ምን እንደሆነ የትግራይ ክልል መንግሥት የገለጸው ነገር የለም። ነገር ግን የትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ፌስቡክ ገጹ ላይ “ለሰላም ሲባል ለሚከፈል ዋጋ ሁሌም ዝግጁ ነን” የሚል መልዕክት አስፍሯል።

ቢሮው አክሎም “የአንድ ሕዝብ የሰላሙ ዋስትና ውስጣዊ አቅሙ እንጂ የማንም የውጭ ኃይል ድጋፍና ጥበቃ ሆኖ አያውቅም” ሲል ገልጿል። የእዚህ ወታደራዊ ትዕይንት ዓላማ ባይገለጽም የትግራይ ክልል መንግሥት ከፌደራሉ መንግሥት በኩል ይደርስብኛል የሚለውን ጫና ለመመከት እየሰራ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።

የቀድሞው ገዢ ፓርቲ ኢህአዴግ ከከሰመና የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከአዲሱ የብልጽግና ፓርቲ እራሱን ካገለለ በኋላ በፌደራሉ መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ መጥቷል።

ወታደሮች
ይህም ሁኔታ በሁለቱ ወገኖች መካከል የኃይል ግጭት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ከአንዳንድ ወገኖች በኩል ሲነሳ ቆይቷል።

ባለፈው ሳምንት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር ምንም አይነት ፍጥጫ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ተናግረዋል።

በዚህም “ማን ነው ማንን የሚወጋው? ለምንድነው የፌደራል መንግሥት ትግራይን የሚወጋው? ይህ የእብደት ንግግር ነው። የፌደራሉ መንግሥት የራሱን ሕዝብ የመውጋት ሃሳብና ፍላጎት ፍጹም የለውም” ብለው ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ነግ ግን የትግራይ ክልል መንግሥት ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት እውነታውን አያንጸባርቅም ሲል አጣጥሎታል።

የትግራይ ክልል መንግሥት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫም “ስልጣን ላይ ያለው አሃዳዊ አምባገነን ቡድን የትግራይ ሕዝብና መንግሥት ምርጫ አካሂዳለሁ በማለቱ ብቻ ‘ተዘጋጅቻለሁ፣ እናቶች ያለቅሳሉ፣ የወጣቶች ደም ይፈስሳል፣ መሰረተ ልማት ይወድማል’ ሲል በአደባባይ ፎክሯል” ሲል የፌደራል መንግሥቱን ከሷል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ለነሐሴ ወር የተያዘው አጠቃላይ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወርሽኝ ሰበብ መራዘሙን ተከትሎ ነው።

የምርጫውን መራዘም የትግራይ ክልል የተቃወመው ሲሆን ከሌሎቹ የአገሪቱ ክልሎች ተለይቶ በተናጠል ምርጫውን ለማካሄድ ወስኖ አስፈላጊ የተባሉትን ሥራዎች እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም ሳቢያ ባለፈው ሳምንትም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲያቆም የሚጠይቅ ደብዳቤ ፅፏል።

በደብዳቤው ላይ ክልሉ በዚህ ውሳኔው የሚገፋ ከሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት “በሕገ መንግሥቱና ሌሎች ሕጎች የተሰጠውን ስልጣን ለመተግበር እንደሚገደድ” ማስጠንቀቁ ይታወሳል።

ወታደሮችBBC Amharic

3 COMMENTS

  1. The Tigraian forces under their vanguard party, the TPLF have decisively defeated the then largest army in Africa. In warfare, what matters most is not number but determination,self confidence, discipline and mission. The stories of the Tigraian and Israeli armies is similar in this case because both have defeated their numerically much superior enemies. The Tigraians are peace loving people but prepared to defend their country Tigray and freedom.

  2. Kidanu
    No, Tigre’s never defeat anyone let alone the biggest army. Have you ever heard of delusions of grandeur? That is what you tigrians have, nothing more. You think you are a warrior, we saw that during badame war. You were toasted by Eritrea small army until the old derg army came and rescue you. Don’t make me laugh when you compare yourself to Israelis. If anyone who have distant relation with Israelis are only Amaras. Because they themselves are relatives of Israelis (where do you think the lion of Judah came from). Abiy shouldn’t have move a finger on you, all he has to do is let the gonderes and woloyes do the job. It won’t take them a full day to bury all of you. What country do you have to defend? Isn’t the place you occupy axumite Amara land? If I were you I learn fast how to swim. Because your next destination is your old barren country called Yemen. If You think you can defeat anyone because you stole a lot of Ethiopian treasure and weapon, you are wrong. We know warriors who can take your weapon from you with a mere stick. Just start some thing and you will have thunderstorms in front of your rag tag so called army. That will finalize the term six hours to mekele. The only way out for your kind is put your tails under your leg, carry a big rock and ask for forgiveness before it is too late. You were and are very bad people, no Ethiopian can forget what sadist you are.
    Dream on woyane, dream on.

  3. እድሜያቸው ለመብልና ለትምህርት እንጅ ለጦርነት ያለደረሱ ሕጻናት ለውትድርና መመልመል በደቡብ ሲዳንና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ባሉ የአሸናሪነት ባህርይ ባላቸው ቡድን ጫፍ የነካ ተግባርና በአለም ላይ በሰብአዊ መብት የሚስጠይቅ እንደሆነ ተምልክተናል፡፡ የምንጸየፈውን በህውሀት ታጋይነት ማየት እንደ ትልቅ ውርደት ይሰማኛል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.