”ህልሜ አማርኛ የአፍሪካ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ነው!” ኒጀራዊቷ የፊልም ባለሙያ ራማቱ ኪየታ

“አማርኛ ብቸኛው የአፍሪካ የስነ ጽሁፍ ቋንቋ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ናት፡፡ ኢትዮጵያ በአማርኛ ትናገራለች፡፡ አፍሪካ ደግሞ አፍሪካን መምሰል አለባት፡፡የአፍሪካን ባህል በማዳበር ወዳጅነት መመስረት አለብን” ትላለች ራማቱ ኪየታ ፡፡
በፊልሙ ዓለም የአፍሪካን ወዳጅነት ለማጠናከር እየሠራች ያለችው የአፍሪካ ፊልም ስራ ባለሙያዎች ማህበር አባል ራማቱ ኪየታ አማርኛ የአፍሪቃ ህብረት የስራ ቋንቋ እስከሚሆን ድረስ ጥረቷን እንደማታቋርጥ ገልፃለች።
እስካሁን በአማርኛ ላይ ምን ሰራሽ ለሚሉኝ ራሴን የአማርኛ ቋንቋ አምባሳደር አድርጌ በመሾም ዓለም አቀፍ ፊልሞች ላይ አማርኛን እስከ ሆሄያቱ እየጨመርኩ ነው የምትለው ነገ ደግሞ ፊልሞቼን በሙሉ ወደ አማርኛ እመልሳለሁ ለዚህ ስኬትም ከፕሮፊሰር ሀይሌ ገሪማ ጋር እየሰራሁ ነው ብላለች ፡፡
1ነጥብ 2 ቢሊየን ህዝብ ባላት አፍሪካ ጥንታዊውን ባለፊደል ቋንቋ የሚናገሩት 100 ሚሊየን አይደርሱም፡፡ የአፍሪካ ህብረት መሪዎችን አነጋግሪያለሁ፡፡ አሁንም አማርኛ ይፋዊ የአፍሪካ የስራ ቋንቋ እስኪሆን ድረስ ጥረቴን እቀጥላለሁ ያለችው ራማቱ ፊልሞቼም በአማርኛ ቋንቋ ይሰራሉ ብላለች፡፡
ፊልሞቿን በጀርመኖቹ ኮሎኝ እና ሀምቡርግ ስታሳይ ዶቼዌሌ አግኝቶ ያነጋገራት የአፍሪካ ፊልም ባለሙያዎች ማህበር አባል ራማቱ ኪየታ ለዶቼዌሊ አማርኛው ክፍለጊዜ እንደገለጸችው ፊልሟን በኒጀር፣ በቡርኪናፋሶ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን እና በሆላንድ ማሳየቷን ትናገራለች፡፡
አማርኛ እ.ኤ.አ. በ1955 ለአፍሪካ የስራ ቋንቋነት ታጭቶ እንደነበር መዛግብት ያሳያሉ፤ ለምን እንደቀረ ግን ምክንያቱ እስካሁን በውል ባይታወቅም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አማርኛ በአንዳንድ የአሜሪካ ግዛቶች የስራ ቋንቋ ሲሆን፣ እስራኤልም የስራ ቋንቋ ለማድረግ ህግ እያዘጋጀች እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የአማርኛ ስርዓተ ፅህፈትን በ1980 ዓ.ም. ከኮምፒውተር ጋር ያስተዋወቁት ዶክተር አበራ ሞላ፣ አጻጻፉ እንዲሻሻል በአንድ ቁልፍ ብቻ የሚሰራ ሶፍትዌር እንዳበለፀጉ ተናግረዋል፡፡አማርኛን ከቴክኖሎጂ ጋር የበለጠ ለማስተዋወቅ እንደ አፕል አይነት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር እየሰራሁ ነውም ብለዋል፡፡ አማርኛ ሆሄያትን ጎግል እና ፌስቡክ ወደ አገልግሎት ማስገባታቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦
dw.com/ለአማርኛ-ቋንቋ-ተቆርቋሪዋ-ኒዤሪያዊት-የፊልም-ባለሞያ

5 COMMENTS

 1. በጣም የሚደገፍ ኃሳብ ነዉ ።የሚገርመዉ አንዳንድ ጽፈኞች አማርኛ ቋንቋ የአማራ ነዉ ብለዉ ያስባሉ ።ነገር ግን አማርኛ የኢትዮጵያ ቋንቋ እንዲሁም አድዋ የመላዉ አፍሪካ የድል ብስራት ስለሆነ አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ቋንቋ ቢሆን ድሉን ይበልጥ አህጊራዊ እንድምታ እንዲሆን ያደርጋል ።

 2. የኢትዮጵያ ባንዲራን የኣፍሪቃና የጥቁር ዘር ሁሉ ነፃነት፣ ኩራትና ክብር ነው በማለት መልኩን ከተከተሉት አብላጫ 95% ግድም የአፍሪካ አገሮች 10 አገራት አረንጓዴ ብጫ ቀይ ፍጹም አንድ አይነት
  ሌሎች 37 አገራት አንድ ወይም ሁለት መልክ የተደባለቀ ከጠቅላላው 54 የአፍሪካ አገራት 47 አገራት የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ የነፃነት ምሳሌና አርአያ በማ ድረግ ወርሰዋል።

 3. Africa
  አፍሪካ
  ።።።።።።።።።።።።።።።፡
  We Don’t need Latin/ Latino Alphabet which belongs To our slaverers And Colonizers. For The Sake of African Unity And Oneness We have FIDEL Ethiopic Which Is FRom Africa And The Only African Indigious Alphabet
  And its key Board was Ready by
  Ethiopian Scientist Doctor Abera Molla .
  And The Called Mr.Mark Powell
  An African American Made by Ethiopic Alphabets for 5 African Languages Such As
  yuriba
  Luba
  Zulu
  Zandena
  Pawini(Siwahil).

 4. Our (Ethiopian) history, is loved by outsiders.
  To mention few of them:-
  – Emperor Haileselasse is loved and adored by the good Jamaicans ;
  -The victory of Adwa is symbol of freedom by all black nations.
  -Abebe Bikila is a Marathon Legend who won an Olympic Gold Medal running barefooted!
  – Amharic language is one of the oldest on earth (5th BC), is the only and African language which posses its own complete Alphabets, called Geez; and it has its own numeral system, our own calandar. So it’s not surprising to implement in the near future Amharic business language for Africa. Soon, it’s necessary to give as compulsory class for African youths. Keep in mind! Absolutely, Nothing to do do with politics.
  God bless Africa.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.