“ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጣም ፈሪ ናቸው ! ” – ዳዊት

“የፌዴራል መንግስት ጠንከር ያለ መግለጫ በማውጣት ሀገሪቱ አንድ መንግስት ብቻ እንዳለ በተግባር ምርጫውን በመከልከል ያሳያሉ ተብሎ ሲጠበቅ ሀገሪቱን ከመበታተን ይታደጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ ህውሀት ትግራይን ለመገንጠል የሚያስችለውን ጉዞ ያለምንም ማንገራገር ፈቅደዋል ::

በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ጠ/ ሚ አብይ በመሪ ደረጃ ጠንካራ አቋም ያሌለው እጅግ በጣም ፈሪ ባንኩንም ታንኩንም ይዘው የሚለማመጡ ሀገር ላይ እጅግ ብዙ ጉዳት ከደረሰ በኃላ ከረፈደ እርምጃ ለመውሰድ የሚጣጣሩ ጠ/ ሚ ሆነው ክልሎች እንደፈለጉ የማይታዘዟቸው ከጠ/ ሚ ሀያለማሪያም እንኳ ያነሰ ልብ ያላቸው እጅግ በጣም ፈሪ መሪ ናቸው ::

ህውሀት እንዲገነጠል ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፈቅደዋል ! ነገር ግን በጉልበት የወሰዳቸውን የአማራ መሬቶች ሳይመልስ ጉዳዩ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተይዞ እያለ ምርጫ እንዲያደርጉ መፈቀዱ መሬቶቹንም ለህውሀት መወሰናቸውን በተዘዋዋሪ ያሳዩበት መንገድ ነው ::

ትግራይ ከዚህ በኃላ ራሷን ችላ ሌላ ሀገር ነች ! የሀገሪቱን የፌዴራል መንግስት በየትኛውም መንገድ ትእዛዝ የማትቀበል ራሷ በመረጠችው መሪ የምትተዳደር በየትኛውም ግዜ በማንኛውም አካል ላይ ጦርነት መክፈት የምትችል ሉአላዊ ሀገር አድርገዋታል ጠ/ ሚ አብይ አህመድ ::

ጠ/ ሚ ጉልበታቸው የፈረደበት የአማራ ህዝብ ላይ ነው ክልሉ ላይ ባስቀመጧቸው ምስለኔዎች አማካኝነት የፈለጉትን እያደረጉ ህዝቡን ጥያቄውን እንዳያሰማ መሬቶቹን እንዳያስመልስ ሳንካ በመሆን የህውሀት የተግባር ልጅ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል ::

ጠ/ ሚሩ ምንም አይነት የኢትዮጵያዊ ቆራጥ መሪ ስብእና በፍፁም በፍፁም የላቸውም ! ከመሪነታቸው ይልቅ የፓስተር ስብእናቸው ተቆጣጥሯቸዋል

ይህ ፌሎ ሽፒ ሀይደልም በስብከት ብቻ ሰውን ማሳመን የሚቻለው ሀገር ነው ! ኮስተር ኮፍጠን ማለትን ይጠይቃል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን አሁንም ይህን ለማስተባበል ሌላ ስብከት ይዘው ብቅ ይላሉ ::

የአማራ ህዝብ እና መንግስት ግን አማራጩን በራሱ መንገድ ሊፈታ ይገባል ! ፋኖ የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴ ትግል መጀመር አለባቸው ! በጉልበት የተወሰዱበትን እርስቶቹን መንግስት እንዳሌለ አውቆ የራሱን አማራጭ መውሰድ አለበት ::

የዶ/ር ኣብይ ድፍረቱ ኮንዶምኒየም ስርቆት ላይ እና እንደ እስክንድር ባሉ ንፁሀን ብቻ ላይ ነው!”

ተፃፈ በዳዊት ፣

1 COMMENT

  1. You said the truth thank you. He is just like the chicken in front of his house. Does not deserve to be called a man, another name comes to mind.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.