የአሥራት ጋዜጠኞች ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደረጉ

አሥራት:_ጳጉሜ 3/2012 ዓ/ም
የአሥራት ጋዜጠኞች ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን (3ኛ) እስር ቤት ከተፈቱ በኋላ 7 ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች “ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ” በሚል ወደ እስር ቤት እንደመለሷቸው ለማወቅ ተችሏል።
በትናንትናው ዕለት የአራዳ መጀመርያ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት የጠበቀላቸው ሲሆን ፖሊስ ከእስር እንዳይፈቱ አድርጎ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው ይታወቃል። ይሁንና የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ ወንጀል ችሎት የፖሊስን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ የዋስትና መብታቸው መከበሩ ትክክል መሆኑ ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሥራት ጋዜጠኞች በእያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ በተጠየቀው መሰረት አሥራትን በሕዳር ወር 2012 ዓ/ም የለቀቀው ዮናታን ሙሉጌታ ተፈትቷል። ይሁንና በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ከእስር ቤት ሲወጡ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች በር ላይ ጠብቀው ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ አድርገዋል።

3 COMMENTS

  1. Balderas political party needs to be classified as an international terrorist organization with international active terror networks while its headquarters is based in the capital city of Ethiopia , Addis Ababa .
    The former chief federal prosecutor and the now Mayor of Addis Ababa, Adanech Abebe got the ability to win the terrorist charge case filed in court yesterday against Balderas political party’s leaders and their national and international financial supporters which Included Asrat Media.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.