የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ባንክ ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቀረበ

ዋዜማ ራዲዮ- የአለም ባንክ ኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሚል ቀርጻ እተገብረዋለሁ ላለችው መርሀ ግብር እሰጠዋለሁ ብሎ ቃል የገባው ሁለት ቢሊየን ዶላር ያህል ብድርና ድጎማ መስተጓጐል ከገጠመው በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት ከባንኩ ጋር ለመወያየት ጥያቄ ማቅረቡን ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበው ጥሪ በጥቅሉ በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አተገባበር ዙርያ ለመነጋገር እንደሆነም ተገልጿል። የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እተገብረዋለሁ ያለችውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ በፍጥነት አልተገበረችም በሚል ስበብ ሀገሪቱ ቃል የተገባላትን ገንዘብ በወቅቱ እንዳታገኝ አድርጓል። እርምጃው ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በያዘችው አቋም ሳቢያ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን የሚናገሩ አሉ።

ባንኩ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ቃል የገባውን ብድርና ድጋፍ ማጠፉን አስመልክቶ ዋዜማ ራዲዮ ላወጣችው ዘገባ የዓለም ባንክ ከቀናት በፊት ምላሽ ሰጥቷል። ሆኖም የባንኩ አጭር የፅሁፍ መግለጫ መረጃዎችን ያስተባበለ ሳይሆን በደፈናው ባንኩ የኢትዮጵያን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በቅርበት መደገፍ ይቀጥላል የሚል ነው።

የዓለም ባንክ ለስብዓዊ ዕርዳታ በተለይም የኮሮና ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያቀርበው ድጋፍ ባለፉት ወራት ከዓለም ባንክ እንደተለቀቀ የባንኩ መረጃዎች ያሳያሉ። ይሁንና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን ለመደገፍ ቃል የተገባው ብድር ድጋፉን ለሚያፀድቀው የባንኩ ቦርድ እንዳይቀርብ መስተጓጎሉን ዋሽንግተን ካለው የባንኩ ዋና መስሪያቤት ምንጮች ስምተናል።

የኢትዮጵያ መንግስት አደርገዋለሁ ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሙሉ በሙሉ ለመተግበር በሀገር ቤት ካለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ባሻገር በተደረጉ የተለያዩ ምክክሮች የማሻሻያ ዕቅዶቹ የሚያስከትሉት ተፅዕኖ በባለሙያዎች ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። መንግስትም የባለሙያዎችን አስተያየት ተከትሎ ዕቅዱን የመከለስና የማዘግየት እርምጃዎችን መውሰድ ጀምሯል።

አንድ የባንኩ የግምገማ ሪፖርት ሰነድ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመውታል ብሎ ያምናል። ባንኩ ባለው ግምገማ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ አደርገዋለሁ ያለውን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዛወር ዕቅድ በአግባቡ ተግባራዊ እየሆነ አይደለም።

የፋይናንስ ዘርፉን ለገበያ ክፍት የማድረግና የመንግስትን ቁጥጥር በማላላት በኩልም ያለው እንቅስቃሴ ከጅምር ያለፈ አይደለም። ይልቁንም የማሻሻያ እርምጃውን ተግባራዊ ያለማድረግ አዝማሚያ ታይቶበታል። በሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ የሆኑት የመንግስት ባንኮች ድርሻ በሂደት በግል ባንኮች እንዲተካ የማድረጉ ሂደት ገና አልተጀመረም። መንግስት የግል ባንኮች ላይ የውጪ ኢንቨስተሮች እንዲሳተፉበት የሚያስችል ማሻሻያ አላደረገም። [ዋዜማ ራዲዮ]

2 COMMENTS

  1. USA is a land of immigrants. Most of the money the world bank loans to Ethiopia is gotten from investors whose ancestors immigrated to USA . Trump’s time is best for the homeless new arrival vulnerable Ethiopian refugee migrants in USA,in Trump’s time the infrastructures are being used to help the vulnerable segments within USA which is relieving the burden of helping the new arrivals from us the ones who stayed in USA longer which is just another simple proof that Trump is siding with the ordinary Ethiopian people not with the hypocrite elites in Ethiopia . Trump is willing to let the money reach directly to those who need it without the brokers in the middle . Trump’s plan to withdraw the giving of the lump sum funds to the EPRDF PP is appropriate since instead he is willing to give it directly to the needies without the ethnic middlemen EPRDF squandering the money.

    For the first time in a very long time the new arrival migrants basic needs such as housing , clothing , nutritious food , medical attention.. are being covered by the USA government . Trump’s actions so far indicate when not if Trump gets reelected he is determined to make America Great Again , by making America a land of opportunity for all. The federal law enforcement agencies had already identified cities within USA and already completed the identifying process of the identities of the habitual violent criminals within the cities, especially cities who need to be helped by sending in the federal law enforcement agencies to do the work, these identified parts of the country finally got the chance to be free from the infestation of crimes in their cities which is costing lives by the Americans loosing generations to crime. The president got the responsibility to identify the failed local law enforcement agencies and try to help enforce the law by sending in federal law enforcement agencies to do the job. Something similar to what Abiy Ahmed did when he sent his federal law enforcement agencies to arrest the terrorist Eskinder Nega and similar to when the federal law enforcement agencies arrested Lidetu Ayalew in the Oromia State.Trump is a visionary leader who is willing to make America a land of opportunity again.

  2. These aid monies are used to punish some and benefit others. Tools of coercion get the lions share of such funding and the rest of the beneficiarys are those that are closer to the regime and of no Ethiopian sentiments. Wether the world bank gives the money it is inconsquential to the Ethiopian people.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.