ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 የብር ኖቶች የሚተኩ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችና አዲሱን የ200 ብር ኖት ይፋ አደረገች

አሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል።
ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል።
ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል።
በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል።

2 COMMENTS

  1. This is not a good news for the TPLF. The TPLF leaders have run too their safe haven Makelle with containers filled with looted money. They have using this money to destabilize the government and derail its reformist programs. The Oromo activists such as Ezkiel Gabissa and Tsegaye Ararsa are among the Oromos who are on the TPLF payroll. Some in the Oromo political community say that Ezkiel and Tsegaye are mainly preoccupied with getting part of the money the TPLF has looted from Oromia

  2. ኢትዮጵያ በቀደመው ታሪኳ እንዲህ ያለ ብልህና ቅን መሪ አልነበራትም። ያው ግን ለህዝባቸው መልካምን ነገር የሚያስቡና ተራማጅ ሃሳቦችን ይዘው የተነሱ አልነበሩም ማለት ግን አይደለም። ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ከልቡ የሚተጋ መሪ ነው። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያደረገውን ለውጥ አይቶ መመዘን በቂ ነው። የሰው መለኪያ ተግባሩ እንጂ ዘሩና ቋንቋው ወይም ሃይማኖቱ ሊሆን አይገባም። ለምሳሌ ኮ/መንግሥቱ ሃይለማሪያም አንድ ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀር በማለት ፈክረውና አፋከረው እግሬ አውጪ በማለት ሃገሪቷን ወንበዴና ሃገር ቆራሽ ለሚሏቸው አስረክበው ነው የሸመጠጡት። አጼ ቴዎድሮስ የተለሙትን ዳግማዊ ሚኒሊክ ተቀብለው የሚችሉትን ሁሉ ከቅኝ ግዛት ሃይሎች ጋር በመፋለም አሳልፈው ለቀ. ኃ. ሥ አስረክበው እሳቸውም የሚችሉትን ለወገንና ለሃገር ሰርተዋል። ያው ታህሳስ 5 1953 የተሞከረው የመንግሥት ግልበጣ ብዙዎችን ገደለ። የግልበጣው መሪ ጄ/መንግሥቱ ንዋይም ዝናብ በሚያካፋበት በዚያች ጨፍጋጋ ቀን ተሰቅለው አለፉ። ጄ/ መንግስቱ ንዋይ “እኔን እንጂ ሃሳቤን መግደል አትችሉም” ባሉት መሰረት ሌላው መንግስቱ የንጉሱን ዙፋን በግፍ ወደ ሲኦል አወረደው። ከዚያም በህዋላ የሆነው የእብደት ፓለቲካ በመሆኑ እዚህ ላይ እንዲህ እና እንዲያ ማለቱ አብሮ ማበድ ነው።
    ጠ/ሚ አብይ ዝርፊያን የሚጠየፍ፤ ያለኝ በቃኝ የሚል ሰው ለመሆኑ በጎኑ የተሰለፉ ይመሰክሩለታል። በቤታቸው ብር ያመርቱ የነበሩ ሁሉ አሁን ምን ይዋጣቸው? በሰሜን አሜሪካ፤ በአውሮፓና በሌሎች ሃገር ሆነው ብር እንመንዝርልህ ይሉ የነበሩ ዘራፊና አዘራፊ ጥልፍልፍ የሃዋላ አግልግሎት ሰጪዎች አሁን ምን ይውጣቸው ይሆን? ወያኔና ሌሎች የዘርና የቋንቋ ፓለቲከኞች ሰው እየገደሉ በጆኒያ ያከማቹት ገንዘብ እንዴት ሊያረጉት ነው? እንድደው እንዳይሞቁት ከረምቱ አለፈ። ለእኔ የተወሰደው የወረቀት ብር ለውጥ ተገቢና ሊደገፍ የሚገባው ጉዳይ ነው። ያው እንደ ተለመደው ግን የቁራ ጩኽት የሚጮሁ፤ ከከርሳቸው ሌላ የህዝብ መመዝበር የማይገባቸው ድልብ ደንቆሮዎች ያው በየጎጣቸው መንጫጫታቸው አይቀሬ ነው። መረጃ አልባ ወሬ፤ ውሸትን እንዳዪት አስመስለው በየኢንተርኔት ላይ የሚለጥፉ የፓለቲካ ሙታኖች እይታቸው ለራሳቸው ብቻ በመሆኑ አክ እንትፍ ሊባሉ ይገባል። ይልቅስ ጠ/ሚሩ ሃገርና ህዝብን የሚለውጠው ራዕያቸው ግብ እንዲመታ በምንችለው ሁሉ የራሳችን አስተዋጾ ብናደርግ ብሩህ ተስፋ በምድሪቱና በህዝቦቿ ላይ ሊፈነጥቅ ይችላል። በቃኝ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.