አቶ አላሙዲንን እንደ በጎ አድራጊ፣ ቸር እና ደግ ሰው የምትቆጥሩ ሰወች በጣም አስቂኝ ናችሁ

Alamudi 2አላሙዲ ሞራል እና ስነምግባር የጎደለው ሰው ነው፣ አላሙዲ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ትዳር አፍርሷል፣ አላሙዲ ወርቅን ያክል የኢትዮጵያ ሀብት በብቸኝነት ያለ ማንም ከልካይ እየዘረፈ ያለ ሰው ነው።

ብዙወች አላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያንቀሳቅሰው ንግድ ትርፍ እንደሌለው እና ይልቁንም በተለያየ ጊዜ ለግለሰቦች በሚያደርገው የገንዘብ ዳረጎት ብዙ ሚሊዮን ብሮች የሚከስር ግለሰብ አድርገው ማየታቸው አንድም ካለማወቅ ነው በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ሰውየው በተደራጀ መልኩ በጎ ነገሮች በሚያወሩ እና በሚያስወሩ ሰወች ተሸውደው ነው ብለን እናስባለን።

ቢሆንም ግን አላሙዲ ህወሀት/ወያኔወች በራሱ ምንም ሊያደርጉት የማይችል ግለሰብ ነው፤ ምክንያቱም እሱ የአይነኬወቹ ሰይጣን አምላኪ ኢሉምናቲወች አባል ነው (ይህን አላምንም የሚል ሞባይል እና ለፕቶፕ ላይ አፍጥጦ ፎቶ ላይክ ከማድረግ ይመርምር)፤ እስከዛሬ ህወሀት/ወያኔወች በእሱ ምክንያት አይናቸው እየቀላ ምንም ሊያዳርጉት ያልቻሉት ሰው ነው፤ ስለዚህ ምርጫቸው እና የሚያዋጣቸው አብረው ተሞዳሙደው መዝረፍ ነው።

በአጠቃላይ አቶ አላሙዲ (ሼኽ የማልለው ሙስሊም ስላልሆነ ነው) መታየት ካለበት እንደ በጎ አድራጊ ሳይሆን እንደ ሞራል እና ምግባር የሌለው ዘራፊ ሰው ነው፤ ሊመሰገን አይገባውም። ምናልባት የወሎ ሰወች ከሚዘርፈው ነገር ቆንጥሮ ስታዲዬም ገንብቶላቸዋል፣ ኮምቦልቻ ላይ የህወሀት/ወያኔን መሰፍን ኢንጅነሪንግ ጉሮሮ የሚዘጋ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ሊገነባላቸው መሰረት ድንጋይ ጥሏል፣ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሚሆን ቴሪሸሪ/ ሦስተኛ ደረጃ የህክምና ማዕከልም ሊገነባላቸው ስለሆነ ቢያመሰግኑት አይከፋኝም።

ይህን የፃፍኩት አሁን በታክሲ ስሄድ ማንነቱን ባላወቅኩት ኤፍ ኤም ራዲዮ አንድ የሰውየውን ዳረጎት የሚፈልግ አይነት ጋዜጠኛ ሰውየውን ሲያቆለጳጵስ፣ ሲክብ እና ሲያሽቃብጥ ሳልፈልግ ሰማቼ አድርባይነታችን አብሽቆኝ ነው።

ዓበጋዝ ዤዓንግት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.