እኛም /ዜጎች ሆነ እኛ አገር መሪዎች  ከቀደመ ታሪክ  እና ከሌላዉ ዓለም የሚማሩት መቸ ይሆን – ማላጅ

በዓለማችን በተለያየ ጊዚ በሚፈጠሩ እና በሚከሰቱ ችግሮች የዜጎች የሕይወት ድህንነት አደጋ ላይ ወድቆ ማየት አይደለም በአስተዳደር እና በአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች ቅሬታ ሲኖር ወይም መኖሩ ሲረጋገጥ የሚመለከተዉ አካል ወይም ባለስልጣን ይቅርት የመጠየቅ፣ የማስተካከል እና እልፍ ሲል ከስልጣን መሰናበት/ መልቀቅ (Resignation) ይታያል፡፡

ይህንም በቀላሉ በቤሩት በደረሰዉ የፀረ ተባይ ክምችት መጋዘን ፍንዳታ እና ይህን ተከትሎ በሆነዉ አደጋ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሳይቀር ተበትኗል፡፡

ወደ እኛ አገር ስንመለስ ከግል አስከ መንግስት መዋቅር  ግለሰብን ሆነ አገርን /ህዝብን ለደረሰ ጥፋት ኃላፊነት መዉሰድ እና ይቅርታ መጠየቅ በተለይ ለመንግስት ባለስልጣን የማይተሰብ እና እንደሃጢያት ይቆጠራል፡፡

እንግዲህ በዚህ ዓይነት ጥፋተኛ ፣ ወንጀለኛ ፣ ራስ ወዳድ እና ራሱን ከህዝብ እና አገር በላይ በማድረግ የፈለገዉን በማድረግ እንዲኖር የሚፈቀድለት እና ሌላዉ ደግሞ በሀብት ንብረቱ አይደለም በራሱ ሠባዊነት የማይከበር እና የህግ ጥበቃ እና ከለላ የማያገኝ ከሆነ እንዴት ያለ ዕድገት እና አገራዊ አንድነት እንዲኖር እንደምንፈልግ ማሰብ እንኳን ያቃተን ይመስላል፡፡

እጁ በህዝብ ላብ እና ሠዉ ደም የጨቀየ ተጠያቂ በማይሆንበት እዉነተኛ ብሄራዊ ዕድገት እና ብልፅግና ማሰብ ክፋት ባይኖረዉም ያለተጨባጭ አርምጃ  ግን ከፍተኛ ጉዳት ያለዉ የጨለማ ጉዞ እና የሕልም ሩጫ(እንጀራ) ነዉ ፡፡

ለአብነት በአገራችን ለተጀመረዉ የለዉጥ ጉዞ ደንቀራ እና መንስኤ የነበረዉ የህገመንገስት ይዘት ፣የፌደራል ግዛቶች አደረጃጀት እና አወቃቀር እንዲሁም የምርጫ ስርዓት ዉጤት በዜጎች መካከል  ጥላቻ እና ፍራቻ አርግዞ በመዉለድ  የዚህች አገር አንድነት እና የህዝቦቿን/ዜጎች የዘመናት አብሮነት አደጋ ላይ በመጣል የዜጎችን ህይዎት ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ ሲታወቅ የአጋም  እሾህ መንቀል አለመፈለግ የሚያሳየዉ ከታሪክም ሆነ ከዓለም አለመማር እና ለህዝብ እና አገር ደህንነት ተገቢዉን ከብር እና ህብር አለመስጠት እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ ፡፡

የቅርብ ጊዜ እና ጎረቢት ሱዳን አሁን በጀነራል ሀሚድ ጥምር መንግስት የምትመራዋ የዕድሜ ልክ የስልጣን ባለጉልት ጀነራል ዑመር አልበሽርን በኅዝዋ አመጽ ከተባረሩ ማግስት ለሶስት አሰርት አመታት ይመሩበት የነበረዉ የፖለቲካ ስርዓት ርዕተ ዓለም እና ህገመንግስት ታግዷል፡፡

እኮ እኛ አገር የህዝብን እና አገርን ልዑዋላዊነት በተደጋጋሚ በሚፈታተኑ  ፈርጀ ብዙ ዉስብስብ ችግሮች እየተናጥን ይህ ሁሉ ዕንባ እና ደም አስከ መቸ እና ምን ደረጃ አስኪደርስ ነዉ ከራስም ሆነ ከሌሎች የሚበጀዉን ተሞክሮ እና ልምድ ላለመዉሰድ በግትርነት እና በቀቢፀ ተስፋነት  በጥፋት እና ዉድቀት ጎርፍ እየተገፋን በሰመመን የምንነረዉ አስከ መቸ እንደሆነ ስናስብ ዕድለ ቢስነት ይመስላል ፡፡

ማላጅ

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር

2 thoughts on “እኛም /ዜጎች ሆነ እኛ አገር መሪዎች  ከቀደመ ታሪክ  እና ከሌላዉ ዓለም የሚማሩት መቸ ይሆን – ማላጅ

 1. I just read an interview ” የሕግ የበላይነትና የፍትህ ጉዳዮችን ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርጎ መውሰድን የምንፀየፈው ነገር ነው – ናትናኤል ፈለቀ – የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ” the EZEMA’S public relations head gave to whoever he or she was asking the questions , I couldn’t find out the identity of the person asking the questions during the interview because the person failed to introduce herself or himself, maybe on purpose because she or he failed to ask important questions such as

  -What is Ezema’s stand on the current arbitrary arrests of close to ten thousands people claiming it was done to quiet down the violence which took place right after Hachalu Hundessa was killed?

  – Does EZEMA feel it is just to arrest Eskinder Nega and charge him with terrorism?

  -Why did Ezema took time until the election was postponed to initiate a study about the handing out of the Addis Ababa Condos? Is it to give enough time for the government to handout enough condos?

  -What are the Ezema offices in Oromia and Benishsngul Gumuz region reporting about the ongoing slaughtering of people based on their ethnicities and based on their religions? Does Ezema think there is a crime against humanity ongoing genocide taking place?

  -What is Ezema’s stand on the GERD negotiation issues?

  -What is Ezema’s office in Tigray planing to do to bring good relations instead of the current deteriorated relationship between the current Tigray regional government and the Ethiopian federal central government?

  -Do Ezema’s leaders feel lucky or do Ezema’s leaders feel innocent for not being imprisoned while many other opposition political figures suffered imprisonments in the past few months ? Do they have suggestions for opposition politicians how to avoid being imprisoned as the Ezema leaders did avoid imprisonment? Are any of Ezema’s members imprisoned accused of participating or accused of planing to participate in the violence that took place right after Hachalu’s death?

  -Does Ezema feel Ethiopia currently got a failed state?

  -Does Ezema feel Ethiopia is under a state terrorism?

  https://www.ethiopianpoint.com/amharic/2020/10/የሕግ-የበላይነትና-የፍትህ-ጉዳዮችን-ለፖ/

  የሕግ የበላይነትና የፍትህ ጉዳዮችን ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድርጎ መውሰድን የምንፀየፈው ነገር ነው – ናትናኤል ፈለቀ – የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

 2. We the middle aged and older aged Ethiopians must close our eyes and get fooled by PM Abiy Ahmed inorder to prevent a civil war. Otherwise if we the middle aged and older aged Ethiopians keep our eyes open and resist being fooled the young and the youth will surely engage in an endless civil war, that is why it is so important for all the middle aged and older aged Ethiopians to lead by example , we need to show the youth how to get fooled by keeping our eyes closed . If we failed to do that then the youth will for sure start an all out civil war with no quick end, since there will be no winner.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.