ግብጽ የኅዳሴ ግድብ እንደምታፈርስ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ኢትዮጵያ ከ120 ቢሊዮን ብር በላይ ያወጣችበትን ታላቁ የኅዳሴ ግድብ ግብጽ እንደምታፈርስ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ ግድቡን እንድትገነባ ግብጽ መፍቀድ አልነበረባትም ብለዋል። ይኸን ያሉት ትናንት አርብ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ሱዳን እና እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት መጀመራቸውን በማስመልከት ከጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ነው።
ከሱዳን ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ እና ከእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት ድንገት የኅዳሴ ግድብን ጉዳይ ያነሱት ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት አስተያየት “ግድቡ እንዳለመታደል ሆኖ ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ ያቆማል” ሲሉ ተደምጠዋል።
“ሥምምነት አቅርቤላቸው ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ሥምምነቱን ሳትቀበል ቀርታለች። እንደዚያ ማድረግ አልነበረባቸውም። ያ ትልቅ ስህተት ነው” የሚል አስተያየት የሰጡት ዶናልድ ትራምፕ በዚሁ ምክንያት አገራቸው ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን “በርካታ ዕርዳታ” ማቆሟን አረጋግጠዋል።
“እንደዚያ በማድረጋቸው በርካታ ዕርዳታ መክፈል አቁመናል። ሥምምነቱን ካልተቀበሉ በቀር ያንን ገንዘብ አያዩትም። ውኃ ወደ ናይል እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገንብተዋል። ግብጽ ትንሽ በመበሳጨቷ ልትወቅሷት አትችሉም” ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በጉዳዩ ላይ ከሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ አስተያየት ጠይቀው ነበር።
ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ በወገናቸው አሜሪካ በዋሽንግተን ሶስቱን አገሮች ለማሸማገል አደረገች ያሉትን ጥረት አድንቀው ለኢትዮጵያ፣ ለሱዳን እና ለግብጽ ከሚጠቅም ሥምምነት ለመድረስ “ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

DW

2 thoughts on “ግብጽ የኅዳሴ ግድብ እንደምታፈርስ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተናገሩ

 1. The majority of the third World War will be fought in the open within the Saharan desert if the current cold war which is being fought about the GERD is not put to rest soon. The weapons manufacturers of the world are betting once the third World War starts it will last for decades before it ends.

 2. አንድ ጓደኛዬ ሁልጊዜ ለጀሮ የማይጥም ነገር ስለሚናገር ሌላው ጓደኛችን እንዴ አንተ ሰው ይጥልሃል ቢለው ምነው ጭቃ ወይም አቧራ ልብሴ ላይ አየህ እንዴ ብሎ ያስቀን ነበር፡፡ ፕሬዚደንቱ ችግር ያለበት ሰው ነው፡፡ ጭንቅላቱ ልክ አይመስለኝም፡፡ ከአውሮፓ እስከ እስያ፤ ከደቡብ አሜሪካ እስከ አፍሪቃ በሃሳብ ያልሰደበው፤ ያልተጋጨው አመራር አይገኝም፡፡ የዶናልድ ጓደኞች የግብጽ አልሲሲ፤ የሰሜን ኮሪያው፤ የቱርኩ፤ የራሽያውና የመሳሰሉት መሪዎች ናቸው። ጥቁር ህዝብን ጭራሽ ይጠላል። ለዚህም ነው በአሜሪካ በብዛት በነጮች የሚደገፈው። አንዳንድ ለሆድ አደር የሆኑ ጥቁሮችም ሃበሾችን ጨምሮ ስለዚህ ሰው ሲከራከሩ መስማት ናላ ያዞራል። ከእርሱ ጋር በ 2016 ቆምረው አብረው ስልጣን ተካፍለው ዛሬ እስር ላይ ያሉ፤ በምርመራ ላይ የሆኑ፤ በእርሱ በየጊዜው የተባረሩ ሰዎችን ስም ዝርዝር እዚህ ላይ ለመጻፍ ስፍራ አይበቃም። እንዴት የኖቬል ሽልማት ሳይሰጠኝ ቀረ በማለት ከዶ/ር አብይ ጋር ቅራኔ ውስጥ የገባው ይህ ደንፊ ሰው ለአሜሪካ ህዝብም ሆነ ለዓለም ህዝብ አይበጅም። አንዳንድ ከእውነት ጋር የተጋጩ በህዝብ ተመርጦ ነው ስልጣን የወጣው ይሉናል። መመረጥ ብቻውን አንዲትን ሃገርን ዲሞክራሲያዊ አያደርጋትም፡፤ የአመራር ስልት እንጂ። ሂትለር እኮ በጀርመን ህዝብ ተመርጦ ነው ያን ሁሉ መከራ ያዘነበው።
  ቀደም ባለው ንግግሩ ትራምፕ ታላቅ ጦርነት እንዳይሆን ታግዬ አቆምኩ ብሎን ነበር። ይህን የተናገረው ከአልሲሲ ጋር ከተወያየ በህዋላ ነበር፡፤ አሁን ግብጽ የአባይን ግድብ እንድታፈርስ በጎን አረንጓዴ መብራት ማብራቱ ምን ያህል የአለምን ጂኦ ፓለቲካ የማያገናዝብ በደንበር ገተር የሚመራ የፓለቲካ ሾተላይ እንደሆነ ያሳያል። ይህ ሰው ለሁለተኛ ጊዜ ከተመረጠ ወዮ ለአሜሪካ ወዪ ለዓለም ሰላምና ጸጥታ። ጭራሽ አስፈሪ ነው። አሁን የኮቪድን ሁኔታ ተቆጣጥረነዋል የሚለው ከእውነት የራቀው የትራምፕ ዲስኩር የሚሞተው እንዲሞት የተፈረደበት መሆኑን እንደርሱ ያሉት ግን ያለቅጥ የወፈሩና በሌላም በሽታ የሚጠቁ ለእነርሱ ብቻ በተዘጋጀ የህክምና ብልሃት ድነው በሌላው ላይ የሚያፌዙበት አሜሪካ ተራፊና አትራፊ ላይኖርባት ይችላል። በመሰረቱ ኮቪድ ታሞ ተሻለው ማለት ደጋሚ በበሽታው አይጠቃም ማለትም እንዳልሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ። ተሻለኝም የሚል ካለ በኮቪዱ ምክንያት የቅርብና የሩቅ የጤና መቃወስን የሚያስከትል ለመሆኑ ሳይንቲስቶች ይጠቁማሉ። ባጭሩ ዓለማችን ጨለማ ውስጥ ናት። በዚህ ላይ እንደ ትራምፕ ያሉ ሰዎች ስልጣናቸው ከቀጠለ እጅግ አስፈሪ ይሆናል። አንድ ጉልበተኛ ሆኖ ሌላውን የሚያሽከረክርበት አለም እያበቃ ይመስለኛል፡፤ አሁን ባለው የሃይል አሰላለፍ ሁሉ እሳት አምራችና ሽያጭ ሆኗል። ቻይና አሜሪካን ለመብለጥ ለዘመናት ሰርታ አሁን ጫፍ ላይ ቆማለች። በኢኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ ጉልበት አሜሪካን በቅርብ እንደምታልፋት ብዙ ጠበብቶች ይናገራሉ። የአሜሪካ ፓለቲካ ሁልጊዜም ጥቁርና ነጭ ነው። አንድ የሩቅ ጓደኛዬ የሆነ ነጭ አሜሪካዊ እጅግ ተምሬአለሁ የሚል እንዲህ አለኝ። ኮቪድ የሚባል ነገር የለም። ከምርጫው በህዋላ ይጠፋል። ይህ ለፓለቲካ ተብሎ የተፈጠረ በሽታ ነው ቢለኝ። እኮ በል መሬት ጠፍጣፋ ናት ብለህ ታምናለህ ስለው ከት ብሎ ሳቀና እኔም ሳቁን በስላቅ መልሼ ለመሆኑ የሰው ልጅ ጨረቃን ነክቶ መመለሱን ትቀበላለህ ስለው እሱም ውሸት ነው ብሎኝ እርፍ። የዚህን ሰው ሃሳብ የሚጋሩ ብዙዎች ናቸው። ኮቪዱ ከምርጫ በህዋላ ይጠፋል። ትራምፕ እንዳይመረጠ ተብሎ የተፈጠረ ወሬ ነው ብለው ያምናሉ። ባጭሩ የትራምፕ የአባይን ግድብ በግብጽ ለማስደምሰስ መጣርና መመሪያ መስጠት ለጥቁር ህዝብ ካለው ጥላቻ የመነጨ ነው። ይህን ለማመን የዘገያችሁ የሚከተሉትን መጽሃፍት አንብቡ።
  Too much and Never Enough – Mary Trump
  Fire and Fury – Michael Wolff
  Let me Finish – Chris Christie
  The Room Where it Happened – John Bolton አንብቦ ማገናዘብ በቂ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እኔም በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.