በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተፈፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የአማራ ህዝብ ለፍትህ፣ለነፃነት እና ለአብሮነት ሲታገል ቢኖርም እስካሁን በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም፣ፍትህና የህግ የበላይነት ሰፍኖ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በሰላም ፣ በነፃነት እና በደስታ መኖር የሚቻልባት አገር ባለቤት መሆን አልተቻለም።ይልቁንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግፍና መከራው አየተጠናከረ በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋና በገፍ መፈናቀሉ ተስፋፍቶ ቀጥሏል።
ይህንን ሁኔታ ለመረዳት ብዙም ሩቅ ሳንሄድ ይህንን አንድ አመት ብቻ ወስዶ አዝማሚያውን መገምገሙ ብቻ በቂ ነው።ከጥቅምት እስከ ጥቅምት ያለው አንድ አመት ብቻ በግልፅ የሚነግረን ግፍና መከራው ተጠክሮ መቀጠሉን ነው። ማለቂያ የሌለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣በገፍ መፈናቀል፣የዘመናት የልፋት ውጤት የሆነ ንብረት ውድመት የየሳምንቱ መርዶ መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል።
ስለሆነም ነገሩን ላለማባባስ ሲባል በዝምታ ማለፋ የሚጎዳ መሆኑን በተግባር እያየነው በመሆኑ ያገባናል ባዮች በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል።ይህ በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመ ያለው በማንም ህዝብ ሳይሆን በጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች ሴራ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ በአጋርነት የሚያሰልፍ የትግል አቅጣጫ ነድፎና ስትራቴጅያዊ ግብ ወስኖ በጋራ መንቀሳቀስ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም። በክስተት ላይ ያነጣጠረ ጩኸት አልቃሻ ከማድረግ የዘለለ ጥቅም የለውምና። – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

5 thoughts on “በጉራ ፈርዳ ወረዳ የተፈፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

 1. በጣም የሚገርም ነው። ለአቶ ገዱ አና ደርጅታችሀው ከሆዴድ ጋር ተለጥፎ ከአማራ ክልል ውጭ ላሉት የትጨፈጨፉት አማሮች ለምን ይሆን ለቅሶ ደራሽነት ሚና እንክዋን የሌለው? አለን ለማለት ካሆነ በቀር ለህዝቡ ያደረጋችሁት ምንም የለም

 2. Ethiopians open a foreign currency account. The National Central Bank of Ethiopia encourages Foreign Currency Accounts.

 3. እኔ የሚገርመኝ የአማራን ህዝብ እንወክላለን የሚሉ ሾተላዪች በየጊዜው የሚያወጡት መግለጫ ነው። ሻቢያና ወያኔ ሲፈጠሩ ጀምሮ የፓለቲካ መሪ ቃል አድርገው የያዙት አማራን ማዳከምና ማጥፋት ነው። ወያኔ ከሻቢያ የተጋተው የጥላቻ መርዝ እጅግ ስር ሰዶበት በበረሃ እያለ በጎንደር ቆላማ ስፍራዎች በወሎና በሌሎችም ይንቀሳቀስ በነበረባቸው ስፍራዎች ሁሉ ያደረሰው ያፈናና የግድያ ጭካኔ በራሳቸው ሰዎች የተነገረ በመሆኑ እዚህ ላይ መዘርዘር አያስፈልግም። ዘረኝነት ቋንቋና ድንበርን ተገን ያደረገ የማንነት ጥያቄ ለድር አራዊቶች እንጂ ለሰው ልጆች አይጠቅምም። ግን ጉዳዪ በወያኔና በሻቢያ እጅግ ተለጥጦ አሁን ደግሞ በኦሮሞዎች ጣራ ደርሶ ሰው አንገቱ ሲቀላ፤ ቤቱ ነዳጅ እየተርከፈከፈ ሲገደል፤ ከመኖሪያው ተሰዶ በየጫካው ነፍሴ አውጭኝ በማለት መጠጊያ ሲፈልግ በዛሬዎቹ አለቆቻችን የምንሰማው ተደጋጋሚ ነገር እያረጋጋን ነው የሚል ነው። ችግሩ እኮ ቀደም ሲል አረጋጋን ወደ ስፍራቸው መለስን ባሏቸው ተራፊ ሰዎች ላይ ነው አሁን እንደገና በደሉ የሚደርሰው። ግን የአማራን ህዝብ እንዲህ በሻቢያ፤ በወያኔና በኦሮሞ ጽንፈኞች መከራ ውስጥ የከተተው በእውን አማራ ጨቋኝ ነበርን? የፈጠራ ታሪክ ማጣቀሻ የለውም። መንጋው ከሚያልፍ ውሃ የሚጋተው አተላ እንጂ። አዎን ጥቂቶች በአማራ ህዝብ ስም በጊዜአቸው ናጥጠው፤ ዘርፈውና አዘርፈው አልፎ ተርፎም ጨቁነው ይሆናል። ግን እንጨት በጀርባዋ ተሸክማ ልጅ የምታሳድገው ደሃ እናት አማራ በመሆኗ ብቻ ለምን ትገደል? ደግሞስ ሰው ምርጫ አለው እንዴ እኔ ከኦሮሞ ወይም ከአማራ ወይም ከአደሬ እወለዳለሁ ብሎ ይወለዳል? የሃበሻው የፓለቲካ እብደት ሰማይ የደረሰው በወያኔ ቢሆንም እንደ ኦሮሞዎቹ እብደቱን ያጋጋለው የለም። መስሎአቸው ነው እንጂ የወለጋው ኦሮሞ ከሃረሩ፤ የሽዋው ከወሎው ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የለም። አብሮ መኖርን የጠላ ሲገዳደል ነው የሚኖረው። ታዲያ እንደ ገዱ አንዳርጋቸው፤ እንደ ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮነን ያሉት አሁን ነው እንዴ የሚነቁት? ጄ/አሳምነው ጽጌ በአማራ አመራሮች ላይ የወሰደው እርምጃ (ባለኝ መረጃ መሰረት ራሱ በመራቸው ሰዎች ነው የተገደሉት) ብሎ ብሎ አልሰማ ስላሉት ተስፋ ከመቁረጥ አንጻር የወሰደው እርምጃ ይመስለኛል። በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን እና ሊደርስ የሚችለውን ነገር ሁሉ ለጄ/አሳምነው ፍንትው ብሎ ሲታየው በጊዜው ላይ በስልጣን ላይ ለነበሩት አመራሮች ግን አልታያቸውም። ዛሬ እሱ የለም። ግን በአማራ ላይ ግድያው እንደ ሃምሌ ዝናብ አላባራም። የገደለን የማይገድል መንግስት መንግስት ሊሆን አይችልም። እልፍ ቆንጭራ እንጋችን ከማስጠንቀቂያ ባሻገር አልቆም ካለ መግደል ተገቢ ነው። ግን ፓሊሱ ኦሮሞ፤ ልዪ ሃይሉ ኦሮሞ፤ ክልሉ ኦሮሞ እየተባለ ያደገ አለም አቀፋዊ እይታ የሌለው ቆንጨራና ገዥራ አንጋች ራሴን ይመስላሉ ከሚላቸው በስተቀር ሰው ሰው መሆኑን በምን ይገባዋል? የአማራ ህዝብ ራሱን ለመከላከልና ያልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ ገድሎ ከመሞት ሌላ አማራጭ የለውም። መንግስት የለም። አሁን እንሆ አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ቋንቋ ካልተናገርክ ሥራ ቅድሚያ አታገኝም የሚባል ጉድ ሰማን። አንፈልግም። ኦሮምኛ መናገርም መስማትም አልሻም ላለ ሰው እንዴት አርገህ ነው በግድ ኦሮምኛ ማወቅ አለብህ የምትለው? የባቢሎን ከተማ መሰረቷ ተጥሏል። ወዪ ለዛች ሃገር! ለዚያውም ነፈሰ ጡርን እያረድ ሆድ እየቀደድ፤ አዛውንቶችን ቆራርጠው ለሚጥሉ ድርቡሾች በምን ሂሳብ ነው የእነርሱን ቋንቋ በግድ የምጋተው? ግን ጉዳዪ ወዴት እያመራ እንደሆነ ህዝባችን ነቅቶ ቢያየው ወደ ገደል ለመሆኑ ግልጽ ነው። የሚሰራው እና እየተሰራ ያለውን ግፍ ለዓለም ህዝብ ሰው እንዳያሳውቅ፤ ፎቶ አታንሱ፤ አትቅረጽ፤ የሞቱትን እኛ እንቀብራለን እየተባለ “የኦሮሞ ህዝብ ስም ይጠፋል” በሚል ፍራቻ ተደባብሶና ተዳፍኖ ይቀራል። ምንም ይሁን ምንም እውነትን ተመርኩዞ የሚፈጸመውና የተፈጸመው በደል መቀረጽ፤ ፎቶ መነሳት፤ በህይወት ያሉትን የአይን ምስክሮች ቃለ መጠይቅ የማድረግ ግዴታ የሰውን ልጅ በሰውነቱ የሚፈርጅ ሁሉ የመብት ተማጋቾች ተግባር ሊሆን ይገባል። ጎበዝ ወያኔ በትግራይ አሻፈረኝ በማለት ከአዲስ አበባው አመራር ይልቅ ከግብጽ ጋር መምከርን መርጧል። በማህል ሃገርና ኦሮሚያ እየተባለ በሚጠራው ክልል ሰው አውሬ ሆኗል። እንዴት ነው ታዲያ ይህ ህዝብ እህሉን ተምችና አንበጣ ቢበላበት ለእግዜር ወይም ለአላህ አቤት የሚለው። በግፍ የሚገደሉት ደም ሳይደርቅ? ደግሞስ አንበጣው በላቦራቶሪ የተሰራ በአውሮፕላን በሃገሪቱ በጠላት የተነሰነሰ ላለመሆኑ ምን መረጃ አለህ? ኢትዮጵያ እጅግ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች። የዚህች አገር ገመና ጀመረ እንጂ አላለቀም። የአማራው ህዝብም ግድያ ከዚሁ ገመና ጋር አብሮ ይጓዛል። የማይቀረው ሞት ለሁሉም ይደርሳል። ግን እየተጎተቱ ከመታረድ እየተከላከሉ መሞት ይሻላል። የአቶ ገድና የደመቀ መኮነን የሌሎችም ባለስልጣናት ጩኽት የአማራን ህዝብ የበለጠ ያስመታል እንጂ የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞችን ልብ አያራራም። ሰው በተቀናጀ መልኩ በመታጠቅ ራሱን ቤተሰቡን ተከላክሎ ካልሆነም እዚህ ቤት እሳት አለ ብሎ ቆንጨራና ነዳጅ ተሸካሚዎችን ሞት የሁሉም እጣ እንደሆነ ማሳየት አለበት። ሌላው ሁሉ የቁራ ጭኽት ነው። በቃኝ!

 4. በጉራ ፈረዳ ብቻ አይደለም ማንነትን ያተኮረ ጥቃት የተካሄደው። ምነው በጉራ ፈረዳ ብቻ ታያቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ? የእርሳቸው የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተጠቁባቸው እንዴ በጉራ ፈረዳ?
  ዋናው ቁም ነገሩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በሀገር ውስጥ ስለተካሄደ ጉዳይ ቢናገርም ሚዛን አይደፋም።
  ባይሆን ባይሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ቢናገሩ ትንሽ ተአማኒነት ይኖረው ነበር ሚዛን ለመድፋት።

  በእዛም ላይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ ማን እንደሆነ የተጠቃው ግልጽ አድርገው ለመናገር እንኳን አልደፈሩም። መንግስት ስለ ጉዳዩ መግለጽ ካለበት ነጥቦች ከብዙ በጥቂቱ

  1)፤ምን አይነት ጥቃት እንደሆነ መግለጽ ፣
  2)ማን ጥቃቱን እንደፈጸመ እንደተጠረጠረ ማስታወቅ
  3)ጥቃቱን ለማስቆም ምንስ እርምጃ እንደተወስድ መግለጽ
  4) የውጭ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መረጃቸውን ከየት እንዳገኙ ለፍትህ ሚኒስትር እና ለጠቅላይ ሚኒስቴር ስርጭት ማስታወቅ አለባቸው ።

  እነዚህን በዝርዝር ለመግለጽ ቸልተኝነት ማሳየት ከእጥቂዎች ጋር አብሮ ጥቃቱን አደባብሶ ለማሳለፍ ሰላሳ አመታት ከተደረገው አካሄድ ምንም አይለየውም። ስለዚህ አቶ ገዱ ያሳዩት ተነሳሽነት ሊበረታታ ቢገባውም እርሳቸው ቢናገሩ ኮሌኔል አብይ አፋቸውን ከለጎሙ ድንጋይ ላይ ውሀ ከማፍሰስ አይለይም።

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አይነት አላማ አንግበው በህቡእ ማንን እያስጠቁ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ አሳይ አጋጣሚ እንደሆነ እንዳይዘነጋ።

 5. ደመቀ በትክክል የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ካልክ አንደ ገዱ ወኔህን አሳይ።ለወንበርናለስልጣን ምቾት በአማራ ህዝብ ደም አትወፍር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.