ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ከሶስት ሽህ በላይ የኢህአዴግ ወታደሮች አልሸባብን ለመውጋት በሚል ወደ ጌዶ ዘመቱ

ዘ ደይሊ ኔሽን የኢትዮጵያ ሰራዊት በታንክና በከባድ መሳሪያ ታግዞ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ሰራዊቱ የተንቀሳቀሰው ከኢትዮጵያ መሆኑንም የገለጸው ጋዜጣው፣አልሸባብ የሚቆጣጠረውን የባርደሬ ግዛት ለማስለቀቅ ሳያቅድ እንዳልቀረ ገልጿል።
የአፍሪካ ህብረት ከኢትዮጵያ ያገኘውን ጨምሮ ከ20 ሺ በላይ ሰራዊት በሶማሊያ ቢያሰማራም አልሸባብን ለመደምሰስ አልቻለም።
ታጣቂ ሃይሉ በቅርቡ በኢህአዴግ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት ከ30 በላይ ወታደሮችን ገድሎ በርካቶችን ማቁሰሉን አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ መንግስት ሰጠው አስተያየት የለም። የአልሸባብ ተመልሶ መጠናከር አዲስ አበባው መንግስት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሰራዊቱን ወደ ሶማሊያ በድጋሜ ለማስገባት ሳያስገድደው እንዳልቀረ ወታደራዊ ተንታኞች ይናገራሉ።
አልሸባብ በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል እየተጠናከረ መምጣት ፣ ከኤርትራ ጋር ጦርነት እንደሚያደርግ ፍንጭ ለሰጠው የኢህአዴግ መንግስት ራስ ምታት ሳይሆንበት እንደማይቀር ተንታኞች ይገልጻሉ።
አልሸባብ ከዚህ በፊት ከነበረው አቋሜ ጋር ሲነጻጸር መዳከሙ ቢነገርም፣ አሁንም በተለያዩ የሶማሊያ ግዛቶች እየተዘዋወረ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው።

Source:: Ethsat

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.