ኢህአዴግ ለጅቡቲና ለኤርትራ አፋሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ

የውስጥ ምንጮች እንደገለጹት ኢህአዴግ የጅቡቲ አፋር እና የኤርትራ አፋር ተቃዋሚዎችን በማሰባሰብ የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የታጠቁ ሀይሎች በሚል የቀጥታ የመሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል።
ሰልጣኞቹ አስመራ ድረስ በመሄድ ስልጣን እንደሚይዙ ተስፋ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የኤርትራ ስደተኞች ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ጨና እያሳደረ እንደሚገኝም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ኢህአዴግ አንዳንድ የአፋር ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በማሰባሰብ ፣ በአፋር በኩል ሊሰነዘርበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል እየሞከረ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

Source:: Ethsat

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.