ሐምሌ 9, 2007 ዓ.ም ኢሳት ዜና

የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል የፓርቲያችሁ አባሎች የትጥቅ ትግልን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በመርህ ደረጃ ኢህአዴግን ብሶት ከወለደው ሰው ጠመንጃ የማያነሳው ለምን ድነው ሲሉ ጠይቀዋል። ሰው መኖር ካልቻለ ምን አማራጭ አለ ሲሉ የጠየቁት ኢ/ር ይልቃል ሰው መቀመጫ መሄጃ ሲያጣ ቢሀድ ምን ይገርማል፣ አትሂድስ ለምን ይባላል? ብለዋል። እንዴውም ወጣቱ ባይሄድ ነው የሚገርመኝ ያሉት ኢ/ር ይልቃል፣ “አከርካሪ ያለውና እውነት የሚናገር ሰው እዚህ አገር አይኑር ተብሎአል ሲሉ የችግሩን መጠን አስረድተዋል። ኢህአዴግ የሚከተለው አካሄድ ለእነሱም አይጠቅምም ፣ አገራችንንም ይጎዳል በማለት ስርአቱ መንገዱን እንዲያስተካክል መክረዋል።

* “ኢህአዴግን ብሶት ከወለደው ሰው ጠመንጃ የማያነሳው ለምንድ ነው ? እስኪ ልጠይቃችሁ… በቃ መቆም መቀመጥ አትችሉም። አንዳንዶቹ እኮ አሁንም ይሄዳሉ። እዚህ ከኖርን ከሥራ ያባርሩናል፣ እዚህ ከኖርን ያስሩናል፣ እዚህ ከኖርን ቤተሰባችን ይበተናል:: ስለዚህ እየገደልን እንሙት ቢሉ ምኑ ነው ነውሩ? እነሱ ህወሓት የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው አይደል እንዴ በረኸ የገቡት? መሄጃ መቀመጫ ሲያጣ ሰዉ እንዴት አይሄድ?! ቢቀር ነው የሚገርመው::”
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት

* የነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በግንቦት 7 ስም ለተከሰሱ ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቶዛዝ ሰጥቷል። አቃቤ ሕግ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሕዝባጽው መብታቸው ተሽሯል ይላል። ፍርዴ ቤቱ የአቃቤ ሕግን ተቃውሞ ውድቅ አድርጎታል

* 6 ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን በተፈቱባቸው ቀናት ጋዜጠኛ ሐብታሙ ምናለ በኢህአዴግ ስልጣን ጠባቂዎች በሌሊት ታፍኖ ተወሰዷል። ሐብታሙ ከ3 የሶርያ እና በርካታ የሶማሊያ ዜግነት ካላቸው ሰዎች ጋር ከአልሻባብ ጋር ሽብር ልትፈጽም ነው ተብሎ ታስሯል። ቤተሰቦቹ ስለሁኔታው ለሚዲያ እንዳይናገሩ ማስጠንቀቂያ ተስጥቷቸዋል።
ከሱ በተጨማሪ ንፁሐን ዜጎች ወደ እስር ቤት እየተጋዙ መሆናችው ተረጋግጧል
ከአንድነት:
ወይዘሮ እመቤት ኃይሌ፣ ወይዘሮ አስቴር ስዩም፣ ወይዘሮ ሐዲያ መሐመድ፣ አሻግሬ መሸሻ፣ ዘነበ ደሳለኝ፣ ቴዎድሮስ ሐብቴ፣ መንግስቱ ደባይ፣ በቀለ

ከሰማያዊ:- አበበ ቸኮል፣ መርከቡ ኃይሌ፣ ደብሬ አሸናፊ

ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ህወሓት ካሰራቸው ኢትዮጵያዊያን መካከል ለአብነት የሚጠቀሱት ናቸው::

**የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ተቃወማችሁ ተብለው ከታሰሩ ብዙዎች መካከል አልሳን ሀሰን የተባለ ተማሪ በፖሊስ ተገድሏል። በወቅቱ መንግስት ራሱን ገደለ ብሎ መናገሩ ይታወሳል። ከአልሳን ጋር ከታሰሩት መካከል 8ቱ ባለፈው ሳምንት ካስር ተፈቱ ቢባልም መረጃው ሀሰት ነው ተብሏል። ቶፊቅ ረሺድ የተባለ ተማሪ ብቻ ተለቋል።

ግጭት ወደአለበት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ አሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትናንት ረቡእ ገለጸ ። በየመን ያለው የጸጥታ ሁኔታ አደገኛ ቢሆንም በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ስደተኞች አሁንም ድረስ ወደ ሀገሪቱ እየገቡ መሆናቸውን ረቡእ ከጄኔቫ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ የሰጡ የደርጅቱ ሀላፊዎች አስታውቀዋል። ከኢትዮጵያኑ በተጨማሪ የሶማሊያ ተወላጆች ወደየመን እየተሰደዱ እንደሆነ የገለጸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ ሆኖ እንደሚገኝ አመልክቷል ። በየመን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ተወካይ የሆኑት ጆሀንስ ቫን ዳር ከመጋቢት ወር ማጠናቂያ ጀምሮ 10 ሺ ስደተኞች ወደ የመን መሰደዳቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ወደ ሀገሪቱ ስለሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን እና ሶማሊያዊያን ጉዳይ ግራ ተጋብተናል የሚሉት ተወካዩ ስደተኞቹ የየመንን ወቅታዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ አስገብተው ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል። በየመን የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ 1 ሺ 670 ሰዎች መገደላቸውን እና ወደ 4 ሺ የሚጠጉ ሰዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ወደየመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን ሲዘግቡ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጲያውያንም በተጨማሪ አሁንም ድረስ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን እየጎረፉ መሆናቸውን ለኢሳት አስረድተዋል። የችግሩ አሳሳቢነትን በመረዳትም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያና በሶማሊያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን ለመስጠት መወሰኑን ሀላፊዎች ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ወደየመን እየጎረፉ ነው ተባለ

ግጭት ወደአለበት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ አሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትናንት ረቡእ ገለጸ ።

በየመን ያለው የጸጥታ ሁኔታ አደገኛ ቢሆንም በብዙ ሺ የሚቆጠሩት ስደተኞች አሁንም ድረስ ወደ ሀገሪቱ እየገቡ መሆናቸውን ረቡእ ከጄኔቫ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ የሰጡ የደርጅቱ ሀላፊዎች አስታውቀዋል።

ከኢትዮጵያኑ በተጨማሪ የሶማሊያ ተወላጆች ወደየመን እየተሰደዱ እንደሆነ የገለጸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩ በጣም አሳሳቢ ሆኖ እንደሚገኝ አመልክቷል ።

በየመን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ተወካይ የሆኑት ጆሀንስ ቫን ዳር ከመጋቢት ወር ማጠናቂያ ጀምሮ 10 ሺ ስደተኞች ወደ የመን መሰደዳቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ወደ ሀገሪቱ ስለሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን እና ሶማሊያዊያን ጉዳይ ግራ ተጋብተናል የሚሉት ተወካዩ ስደተኞቹ የየመንን ወቅታዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ አስገብተው ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

በየመን የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ 1 ሺ 670 ሰዎች መገደላቸውን እና ወደ 4 ሺ የሚጠጉ ሰዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ወደየመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን ሲዘግቡ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጲያውያንም በተጨማሪ አሁንም ድረስ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን እየጎረፉ መሆናቸውን ለኢሳት አስረድተዋል።
የችግሩ አሳሳቢነትን በመረዳትም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያና በሶማሊያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን ለመስጠት መወሰኑን ሀላፊዎች ገልጸዋል።

በገዢው መንግስት ከፍተኛ አፈና የሚደርስበት የኢሳት የቴሌቪዝን ስርጭት ከሳምንታት ሙከራ በሁዋላ ዛሬ ሙሉ ስርችቱን በ ኤም 44 ሳተላይት ጀምሯል። አዲሱ ሳተላይት ጠንካራ ሲግናል ያለው ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በሙከራው ወቅት ስርጭቱን ለማፈን ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱን የኩባንያው ኢንጂነሮች ገልጸዋል። ተመልካቾች አልፎ አልፎ የድምጽ ወይም የምስል መዛባት ቢያጋጥማቸው ስርጭቱን ለማፈን ከሚደረግ ሙከራ የመጣ መሆኑን እንዲያውቁት ኢንጂነሮች መክረዋል። ኢሳት በዚህ ሳተላይት ለርጅም ጊዜ የሚያቆየውን ስምምነት ፈርሟል። ሌሎች ተጨማሪ ሳተላይቶችን ለመከራየት በድርድር ላይ ሲሆን፣ እንደተሳካለት ለህዝብ ያስታውቃል፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢሳትን ለማፈንና የኢሳት ጋዜጠኞችን ኮምፒዩተሮች ለመሰለለል ብዙ ሚሊዮኖችን እያወጣ ሲሆን፣ ለአንድ አመት ብቻ 1 ሚሊዮን ዩሮ ወይም ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ሀኪንግ ቲም ለተባለ ድርጅት መክፈሉ ሰሞኑን የአለም የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል። ስለላውን ተከትሎ አንድ አሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የከፈተው ክስ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ተከሳሹ ለኢሳት ተናግሯል። ለደህንነት ሲባል ስሙ እንዳይገለጽ የተፈለገው ከሳሽ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሰሞኑ ችሎት ላይ አለመገኘታቸውን ይሁን እንጅ በጠበቆቻቸው አማካኝነት መልስ መስጠታቸውን ገልጿል። ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው የቀጠሩዋቸው ጠበቆች ጠንካራና ታዋቂ ቢሆንም፣ በከሳሽ በኩል የቀረቡት የህግ ባለሙያዎች ለእውነት የቆሙ በመሆናቸው ያሸንፋሉ ብሎ እንደሚገምት ገልጿል። ፍርድ ቤቱ የኢህአዴግን መንግስት ጥፋተኛ ብሎ ከወሰነ ውሳኔው በአለም ላይ ስለላን በተመለከተ አዲስ የህግ አካሄድ እንደሚፈጥር ገልጿል። ውሳኔው በአሜሪካ የስለላ ድርጅት ላይ ሳይቀር ተፈጻሚ ሊሆን እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥቷል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ቀደም ብሎ እንደተዘገበው በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እስረኞች ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችሁዋል ከተባልን፣ አቶ አንዳርጋቸው ቀርበው ይጠየቁልን የሚል መከላከያ መልስ ሰጥተው ነበር። ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው በአገር ውስጥ መኖራቸው ስለማይታወቅ እባካችሁ ሌላ ምስክር ጥሩ ብሎ ቢለምናቸውም እስረኞች ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር። አቃቢ ህግ በጽሁፍ በሰጠው መልስ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ አይችሉም የሚል መከራከሪያ ቢያቀርብም፣ ፍርድ ቤቱ ግን አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት ለዋስ አሊያም ልዩ አዋቂ ምስክር ሆነው ሳይሆን ነበሩበት የተባለውን ጉዳይ ለመናገር ለምስክርነት በመሆኑ፣ ምስክርነትም ግዴታ እንጅ መብት ባለመሆኑ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ለተከሰሱት ተከሳሾች ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ውሳኔ አሳልፏል። ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው የት እንደሚገኙና ማዘዢያው የት ተብሎ ሊፃፍላቸው እንደሚገባ ጠይቀው ለቃሊቲ ማረሚያ ወይንም ለፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ሊጻፍላቸው እንደሚገባ፣ ካልቀረቡላቸውም ክሳቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር የተገናኘ በመሆኑ አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ መግለጻቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ዳኞች የወሰኑት ውሳኔ ተፈጻሚ ይሆናል ብለው እንደማይገምቱ አንድ የህግ ባለሙያ ለኢሳት ገልጸዋል። አቶ አንዳርጋቸው ፍርድ ቤት ቀርበው ይመሰክራሉ ብለው እንደማይጠብቁ፣ ይልቁንም ጉዳዩን የያዙት ዳኞች ሊቀየሩ እንደሚችሉ እኝሁ የህግ ባለሙያ ተናግረዋል። የዳኞችን ውሳኔ ያደነቁት ባለሙያው፣ አስፈጻሚው አካል ውሳኔውን እንደሚቀለብሰው ጥርጥር የለኝም ሲሉ አክለዋል።