ዬአጋዚ ጦር ና የወያኔ ሴራ በውስጥ አወቅ ሲጋለጥ!! (የውስጥ መልዕክት)

ወንድሜ ሆይ ይህን ለኢትዮጵያ ህዝብ አድርስልኝ።ነገሩ እንዲህ ነው። ምንአልባት አጋዚ ስለሚባል ልዬ ሃይል ሰምተህ ይሆናል። አጋዚ ማለት ከትግራይ ገጠር ቦታወች የሚመለመሉ ወጣቶች ስብስብ ነው። እኒህ ወጣቶች ገና የስምንት አመት እድሜ እያሉ ነው የሚመለመሉት። ከትግረኛ ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቋንቋ አይናገሩም። እንዲማሩም አይፈለግም። እኒህ ወጣቶች ከየቤተሰቦቻቸው ሲመለመሉ ለቤተሰቦቻቸው የሚነገረው ነገር በመንግስት አዳሪ ትምህርት ቤት ተምረው ትልቅ ደረጃ ይደርሳሉ በሚል ነው። እውነቱ ግን ይህ አይደለም።

እኒህ ወጣቶች የሚማሩት ትምህርት ካለ ስለ ትግራይ ህዝብ ታላቅነት፣በታሪክ ሌላው ህዝብ የትግራይን ህዝብ ሲያጠፍ የኖረ፣ የትግራይ ህዝብ እንዲኖር የማይፈልግ ነው የሚል ነው። ለዚህም ነው እጅግ ፈታኝ የሆነውን የትግል ፈተና ተወጥተን እዚህ የደረስነው እየተባሉ በቃል ይማራሉ። ፊደል እንዲቆጥሩ አይፈለግም። የሚማሩት ነገር ካለ በሙሉ የተግባር የውትድርና ትምህርት ብቻ ነው። በአመት አዳዲስ ህፃናት እየተመለመሉ ልዮ ሃይሉን ይቀላቀላሉ። እስካሁን ባለኝ አፋዊ መረጃ 23 ሺህ አካባቢ የሚደርሱ አጋዚወች አሉ።

ይህ ልዮ ሃይል ዋና መሰረቱ ትግራይ ነው። የትግራይ ሰራዊት ነው ማለት ነው። ይህ ልዬ ሃይል በሦስት ካምፓች ውስጥ የሚኖር ሲሆን እያንድንዱ ካምፕ ዘመናዊ የእርሻ መሬት፣ የእንስሳት እርባታ አላቸው። ከሌላው ቁንቁ ተናጋሪ ጋር በፍፁም የሚገናኙበት ሁኔታ የለም። ዝመቱ ተብሎ ጥሪ ሲደረግላቸው የትግራይ ጠላቶች ተነስተዋል በሚል ነው። ይህን እውነታ ስንቱ ኢትዮጵያዊ እንደሚያቅ አላውቅም። ለማንኛውም ወደፊት እንደቻልኩ ይህ ቡድን በወልቃይት፣ በአምቦ፣በኦጋዴን እና በሃረር የፈፀማቸውን ዘግናኝ የታሪክ ጉዶች ለማካፈል እሞክራለሁ። እስከዚያው ቸር ይግጠመን”

ምንጭ:-ደመቀ ገሰሰ የኔአየሁ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.