የክሪስቲያኖ ሮናልዶ እዚህ መድረስ ሁነኛው ምስጢር‬:-

ሮናልዶ እንዲህ ይላል…

 
“ለኔ ለዚህ ስኬት መድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረገልኝን የልጅነት ጓደኛዬን አልበርት ፎንትራኦን አመሰግነዋለሁ! በጊዜዉ እኔና እሱ ከ18 አመት በታች ለታዳጊ ሻምፕዮና በአንድ ክለብ አብረን እንጫወት ነበር…አንድ ቀን የሊዝበን አሰልጣኝ ወደ እኛ መጣና እንዲህ አለን:- “ዛሬ ብዙ ጎል ያስቆጠረ ወደ እኛ አካዳሚ ይገባል” አለን! በእለቱም ጨዋታውን 3ለ0 ስናሸንፍ ጎሎቹንም የመጀመሪያውን እኔ 2ኛውን ደግሞ አልበርት በሚያምር የጭንቅላት ኳስ አስቆጠረ:: 3ኛዋ ጎል ግን ለኛ አጅጉን ወሳኝ ነበረች… ከዛም አልበርት እቺን ወሳኝ ጎል ለማስቆጠር ከግብ ጠባቂዉ አንድ ለ አንድ ተገናኘ በዛ ላይ እሱ ግብ ጠባቂውን አልፎ ለመሄድም ችሎታው ነበረው ግን ኳሷን ከመረብ ጋር ፈፅሞ ማገናኘትን አላሰበም እኔ ወደፊት ስሮጥ አይቶኝ ነበርና ያለቀለት ኳስ አቀበለኝ እኔም አስቆጠርኳት! ከዛም ወደ ሊዝበን የሚያስገባኝን ትኬት አገኘሁ:: ጨዋታው እንዳለቀም ወደ እሱ ሄጄ አመሰገንኩትና አንተ እኮ ማስቆጠር ትችል ነበር ግን ለምን..? ብዬ ጠየቅኩት አልበርትም “አንተ ከኔ ስለተሻልክ ነው” አለኝ::


እናም እኔ እዚህ ደረስኩ”
ታዲያ ይሄን ታሪክ በፊፋ ፎረም ያነበቡ ጋዜጠኞች የድምፅ መቅጃ ይዘው ወደ አልበርት ቤት አቀኑ…
እንዲህም ብለው ጠየቁት
‪#‎ጋዜጠኛ‬: ይሄ ታሪክ ምን ያህል እውነት ነዉ?
‪#‎አልበርት‬: በትክክል የሆነ ነገር ነዉ የዛኔ ሮናልዶን ሳየው ድንቅ እንደሚሆን አሰብኩ እኔም የ እግር ኳስ ህይወቴን የዛኔ ነዉ ያቆምኩት እንዳልተሳሳትኩም ይኸው አረጋገጠልኝ
#ጋዜጠኛ: ታዲያ አሁን በምን አይነት ስራ ላይ ነው የተሰማራኸው?
#አልበርት: ምንም ስራ የለኝም::
አዎ አልበርት ምንም ስራ የለውም ግን የሚገርም ቪላ ቤትና እየቀያየረ የሚያሽከረክራቸዉ ዘመናዊ መኪኖችና ቤተሰቡን በሙሉ በእንክብካቤ እያስተዳደረ ይኖራል::
#ጋዜጠኛ: ኑሮህ የሀብታም ነዉ ታዲያ የዚህ ሁሉ ምንጭ ከየት ነው?
#አልበርት: በኩራት ሁሉም ነገር ከክሪስቲያኖ ሮናልዶ ነዉ::
ምስሉ ላይ አልበርት ፎንትራኦና ሮናልዶ አምና በቻምፕዮንስ ሊግ ፍፃሜ ሪያል ማድሪድ አትሌቲኮ ማድሪድን 4ለ1 ባሸነፈበት ጨዋታ ሮናልዶ 4ኛውን ጎል አስቆጥሮ ሮጦ ወደ አልበርት በመሄድ ተቃቅፈው ደስታቸዉን ሲገልፁ..

አሰግድ ታመነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.