አንድ-የልዩ-ሃይል-አባል-6-ጓደኞቹን-አቁስሎ ገንዘብ ይዞ ተሰወረ

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድርጊቱ የተፈጸመው ንብረትነቱ የቱርክ የሆነና በጥጥ ማምረት ስራ ላይ የተሰማራውን የቶረን የእርሻ ኩባንያ ገንዘብ ጭኖ በመጓዝ ላይ ባለ መኪና ላይ ነው። የኩባንያው ሃላፊዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአሜሪካ ዶላርና ብር ይዘው በ7 የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት ታጅበው ወደ ወንዶ ጎጊ ወረዳ በሚጓዝበት ወቅት፣ አንደኛው ወታደር ለመጸዳዳት በሚል መንገድ ላይ ከወረደ በሁዋላ፣ ጥይቱን አቀባብሎ በመመለስ 6ቱን ጓደኞቹን አቁስሎ ገንዘቡን ይዞ ተሰውሯል። ቆስለው በመቱ ሆስፒታል ከተኙት ወታደሮች መካከል አንደኛው ዛሬ ህይወቱ አልፏል። ድርጊቱን የፈጸመው ወታደር አለመያዙን ምንጮች ገልጸዋል። ኩባንያው እኤአ በ2011 በጋምቤላ ክልል የጥጥ ምርት ለማምረት 12 ሺ ሄክታር መሬት ተረክቦ ስራ በመስራት ላይ ነው።

Source:: Ethsat

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.