ውህደቱን ለማክሸፍ በተሞከረ የድንጋይ ውርወራ የአንድነትና የመኢአድ አባላት ጉዳት ደረሰባቸው

ቅድመ ውህደት ስምምነቱን ለመፈራረም በአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ፓርቲዎቹ ቢከለከሉም በመኢአድ ጽ/ቤት የቅድመ ውህደት ስምምነታቸውን ከመፈራረማቸው ቀደም ብሎ ወደ ጽ/ቤቱ እንግባ በሚሉ የተወሰኑ ሰዎች ግርግር ለመፍጠር ቢሞክሩም ሙከራቸው ባለመሳካቱ የግቢውን በር በድንጋይ በመደብደብ ከአንድነት ውህደቱ እንዲሳካ በውህደቱ ኮሚቴ አባልነት የበኩሉን አስተዋጽኦ ካደረጉት አንዱ አቶ ፀጋዬ አላምረው እንዲሁም ከመኢአድ አቶ ደመላሽ ካሣ በድንጋይ ውርወራ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የተወሰኑት በፖሊስ ተይዘዋል፡፡

 

 

ድንጋይ በመወርወር ውህደቱን ለማደናቀፍ ከሞከሩት እነዚሁ መካከል የአንዱን ማንነት ለማጣራት በተደረገ ሙከራ ውስጥ ለኢህአዴግ የወር መዋጮ የከፈለበት ደረሰኝ ኪሱ ውስጥ ተገኝቷል፡፡ የመኢአድ አባል ነኝ ሲል የነበረው የኢህአዴግ አባል ወጣት ደረሰኙ ከተገኘበት በኋላ በጥፋተኝነት ስሜት አንገቱን አቀርቅሯል፡፡ 10450

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.