ኦባማ አዲስ አበባ ገባ። እነ እንትና ግን በጣም ገርመውኛል። እስቲ እነ እንትናን እንትን እንበላቸው።(ከተማ ዋቅጅራ)

ኦባማ አዲስ አበባ ከመድረሱ ጥቂት ደቂቃ በፊት በቦሌ አየር ማረፊያ ግቤ ውስጥ ከሰማይ የተወረወረች ቀስተ ዳመና ተተክሎ ታይቷል። ይህ ቀስተ ደመና ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መላ ምት የሰጠበት አጋጣሚ ነው። ግማሹ የአጋጣሚ ጉዳይ ነው። ገሚሱ ዝናብ በመጣሉ የመጣ ነው። ገሚሱ ደግሞ  የኦባማ መምጣትና ቀስተ ደማናው መታየቱ የዝግጅቱ ድምቀት አድርጎ የወሰደውም አለ። እኔ ግን እንዲህ እላለው።

ቀስተ ደመና ከሰማይ ላይ ተነስቶ ወደ ምድር መተከል የጀመረው በኖህ ዘመን ነው። ኖህ ጻድቅና እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። በእርሱ ዘመን የነበሩት ደግሞ ሃጥያተኛ እና እግዚአብሔርን የማይፈሩ ነበሩ። የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኖህ እንዲህ ሲል መጣ፡- ህዝቤ ሃጥያትን ሰርቷል ከበደላቸው ይመለሱ ዘንድ ንገራቸው ለዚህም አንድ መቶ ሃያ አመት የንስሃ ግዜ ሰጥቼአቸዋለው። አለው ኖህም ወደ ህዝቡ ሄዶ  እንግዚአብሔር ስራችሁን አይቶ  ተቆጥቷል ከክፋት ስራችሁ ተመለሱ የመመለሻም ግዜ አንድ መቶ ሃያ ዘምን ሰጥቷችኋል ብሎ  ነገራቸው። ህዝቡ ግን ተሳለቁበት በመቶ አመት ዘለን ጬፍረን በሃያ አመት ንስሃ እንገባለን ብለው ከክፋት ስራቸው አልመለስም አሉ። መቶ አመቱ አለቀ አሁን ኖህ ነገራቸው በአስሯ ጨፍረን በአስሯ ንስሃ እንገባለን አሉት። አስሩም አመት አለቀ እንደገናም በአምስቱ ጨፍረን በአምስቱ ንስሃ እንገባለን አሉ። አምስቱም አለቀ ባራቱ እንጨፍርና በቀሪው አንድ አመት ንስሃ እንገባለን አሉ። አራት አመቱም አለቀ። እንዲ እንዲ እያሉ እግዚአብሔር ለንስሃ የሰጣቸው የንስሃ ዘመን ተፈጸመ። በዚህን ግዜ ከሰማይ የማያባራ ዝናብ ከምርድም የሚፍለቀለቅ ውሃ ወደ ምድር ላከ፡ ምድርም በውሃ መሞላት ጀመረች ይሄንንም አይተው ከክፋታቸው ከመመለስ ይልቅ ቆይ ጉልበታችን ጋር ሲደርስ እንመለሳለን ጉልበታቸው ጋር ሲደርስ ቆይ ወገባችን ጋር ወገባቸው ጋር ሲደርስ ቆይ አንገታችን ጋር እያሉ እግዚአብሔ በክፋታቸው ምክንያት በላከባቸው መዓት በኖህ ዘመን የነበሩ ትውልድ በሙሉ በቁጣው በንፍር ውሃ ጠፉ። የዚህን ግዜ ኖህ አዘነ እግዚአብሔርም ለኖህ ቃል ኪዳን ገባለት። ከአሁን በኋላ ይሄንን ትውልድ በንፍር ውሃ አላጠፋም ሲል ለኖህ ተናገረው። ለዚህም ቃል ኪዳኔ ምልክት ይሆንህ ዘንድ ቀስተ ዳመናዬን በሰማ ላይ እተክለዋለው ይህን ለዘላላም ቃል ኪዳን ሆኖ  ይኖራል አለው። ለኖህ ቃል ኪዳን የገባለት ምልክት እስከዛሬ ድረስ ይታያል።

ታዲያ የዚህ ቀስተ ደመና መውጣቱ የኛ ንጽህና እና ቅድስና ሳይሆን የጻድቃኖች ሃይልና የቃል ኪዳናቸው የተሰፋ ቃል ለሁል ግዜ እንዳለ  ለማሳየት ነው። ኦባማ ከምድረ  አሜሪካ ጽድቅ እንደ ሃጥያት ሃጥያት ደግሞ እንደ ጽድቅ ከሚነገርባት አገር የመጣ እንደሆኑ  ሃጥያቱን በአደባባይ የጽድቅ ስራ እንደሆነ እየገለጸ የመጣ ቢሆንም ይህ ስራው በእግዚአብሔር ዘንድ ጸያፍ ሆኖ  በንፍር ውሃ የሚያስቀስፈው ቢሆን ወደዚች ቅድስት አገር ሲመጣ ከነበደሉ እና ከክፋት ሃሳቡ ጋር ቢሆንም እግዚአብሔር ግን ቀድሞ  ለኖህ በገባለት ቃል ኪዳን መሰረት ስለ መረጣቸው ጻድቃን ብሎ ያሳየውን ቀስተ ደመና  በቦሌ አየር መንገድ ላይም ትክሎ  አሳይቶናል። ይቺ አገር በቅዱሳን ቃል ኪዳን እንደምትጠበቅ እና ቅዱሳንም ከበዋት እንዳሉ የሚያሳየውን የቃል ኪዳኑን ምልክት ቀስተ ዳመናውን የአለም  ህዝብ እንዲመለከት አድርጓል።

እኔ ግን በዛ ሰዓት የገረመኝ   እንትና  ናቸው። ግን ግን ምን ነክቶአቸው ነው? ኦባማ  ወደ እነርሱ እየመጣ ሊፈርስ እንዳለ  አጥር ተጣመው ተጣመው ሊወድቁ የደረሱት። አንድ አባባል አለ በአካል ብቻ  ሳይሆን በአእምሮም እደግ ይባላል ስለ እውነት እነ እንትና አሁን ቆም ብላችሁ አስቡ ምን ነክቷችሁ ነው እንደዚህ በራስ መተማመን ጥፍት ብሎባችሁ አንዱ አንዱን እስከሚከልለው ድረስ መንገዱን የዘጋችሁት። ህዝቡ ምን እንዳላችሁ ታውቃላችሁ ይሄ የሚያሳየው በእውቀት አለመብሰልን እና በራስ አለመተማመንን ነው። ኦባማ  መጣ ብለው እንደ አራት አመት እና አምስት አመት ህጻን ከለልከኝ ከለልከኝ አይነት አኳኋን እንግዳቸውን የሚቀበሉ ከሆነ እና በዚህ መልኩ የሚያስተናግዱ ከሆኑ አገር የሚያህል ነገር በነዚህ ፈራሴ አጥር አቋም የምትተዳደረው አገር በራሱ በማይተማመን መመራት ጉዳቱ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ከነ እንትና መሃል  እንትን ሁሉም ጥለውት ሲሄዱ ብቻውን ቀርቶ ከተመለሱ አይነት እጃቸውን ዘርግተው ሙከራ ቢያደርጉም እነ እንትና አልሰማ አሏቸው። እነ እንትና  ደግሞ  እነ እንትና  ለማስተካከል በተለያየ ሁኔታ ሲጥሩ የነበሩም አሉ እነ እንትና ግን የሚሰማ ጆሮም የሚያይም አይን የላቸውም እንጂ። ለማንኛውም እነ እንትና  አቋማቸውን ለአለም ያሳዩበት አጋጣሚ ስለነበረ  አጋጣሚውን ወድጄዋለው። መቼስ እነ እንትና ትችት አይወዱም እነሱን መተቸት ለነሱ የጠላትነት ስሜት ነው ላደጉ አገር ደግሞ ድክመታቸውን የሚያዩበት በጣምም የሚፈልጉት ነገር ነው በተገላቢጦሽ አለም ስለምንኖር ቢያሳዝነንም ድክመቶችን አይቶ ማለፍ ተገቢ አይደለም። ለነ  እንትና  በራስ መተማመናቸውን ከውስጣቸው ሙልጭ አድርጎ ያጠፋባቸው እንትና .. እንትን አድርጎ..  እንትን አሰርቶ…  እንደሆነ ብናውቅም ነገር ግን የአቋም ለውጥ እና የአእምሮ  ብስለት እንዲሁም በራስ የመተማመን ብቃት ያስፈልጋቸዋል። ሊፈርስ ያለው አጥር ይፍረስና በማይፈርስ ቀጥ ባለው እንደ ብረት በጠነከረ በራስ የመተማመን ብቃት ያለው አገር የሚኮራበት አቋም ያለው እንትን ይመስረት እላለው።

ከተማ ዋቅጅራ

31.07.2015

Email waqjirak@yahoo.com

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.