አቶ በቀለ ገርባ አማራ ይቅርታ ይጠይቀን ይላሉ፡- ቤተ አማራ ደግሞ ኢትዮ-ኦሮሞ ካሳ ይክፈል ይላል

ለስላሳና ሰላማዊ ተቃዋሚ የሚባሉት አቶ በቀለ ገርባ አማራ በኦሮሞ ላይ በደል ፈጽሟል ይላሉ፡፡ ይህንን ጥፋት ማመን የግድ ነው፤ አለማመን ግን አሁንም አብሮ ለመኖር አያስችልም አይነት ንግግር ሰፋ አድርገው ተናገሩ፡፡ በእርግጥ ኦሮሞን የበደሉት “የአማራ ገዥ መደቦች” ናቸው አሉ፡፡ ቀጥለውም አማራ እንደ ህዝብ አልበደለም፤ ከአማራ የወጡት ገዥ መደቦች ናቸው እንጅ አይነት ነገር አሉ፡፡ የንግግራቸው መጀመሪያ “ከአንዳንድ ብሔረሰቦች የወጡ ገዥዎች ከእነሱ ውጭ የሆነውን ሁሉ በድለው የኖሩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በኦሮሞ ላይ የደረሰውም ይሄው ነው” የሚል ነው፡፡ ይህ እንግዲህ መልኩን እና አራማጆቹን እየቀያየረ እስካሁን የዘለቀው የኦነግ አስተሳሰብ ነው፡፡ በደሉን ያደረሱት “የአማራ ገዥ መደቦች ናቸው” እናም “አማራ አልበደለንም” ከተባለ ማነው ታዲያ ዛሬ ስህተቱን የሚያምነው እና ይቅርታ የሚጠይቀው? ገዥ መደቦች ሞተዋል፡፡ እኛ አሁን በዚህ ዘመን የምንኖር አማሮች ደግሞ በሾርኔ “እናንተ አልበደላችሁንም” ተብለናል፡፡ ስለዚህ ማን ነው አሁን በህይወት በሌሉ ገዥ መደቦች ስም ስህተቱን የሚያምነውና ይቅርታ የሚጠይቀው? ገዥ መደቦች በድለዋል ከተባለ እንኳ የትኞቹ ገዥዎች እንደበደሉ ግልጽ አልተደረገልንም፡፡ አሁን ይቅርታ እንዲጠይቁና እና ስህተታቸውን እንዲያምኑ የተፈለጉት የአጼ ምኒልክ ዘሮች ናቸውን? የአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘሮች ናቸውን? ወይስ የአጼ ቴዎድሮሰው ዘሮች ናቸው?

ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ ለአፍ ያክል ገዥ መደብና ሌላው አማራ ብለው ይከፍሉናል እንጅ እውነተኛው መልእክታቸው አማራ ኢትዮ-ኦሮሞን ጨቁኗል ነው፡፡ ወያኔም በል ሲለው እንዲህ ነው ከፋፍሎ የሚገልጸን፡፡ ይህ “አማራ ጨቋኝ ነው” የሚለው ፖለቲካዊ እሳቤ (1) በ1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጎልቶ ይሰማ የነበረ ነው፡፡ (2) ሻእብያ ሲያራምደው የነበረው የቅኝ ተገዥነት ጥያቄን ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርግበት የነበረ አስተሳሰብ ነው፡፡ (3) ወያኔ “አማራ ብሔራዊ ጨቋኝ ነው”፤ “አማራ የትግራይን ህዝብ ጨቋኝ ነው” እናም “መጥፋት አለበት” ብሎ ሲሰራበት እና የትግራይን ህዝብ ሲያነሳሳበት የቆየው ዋና አስተሳሰብ ነው፡፡ (4) ኦነግ በተመሳሳይ አማራ ጨቋኝ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ቅኝ ገዥ ነው ብሎ አሁንም ድረስ የሚያራምደው አስተሳሰብ ነው፡፡ አምስተኛ ረድፈኛ ለስላሳ የሚባሉትም የኦሮሞ ድርጅቶአች የሚያራምዱት ይህንኑ ጸረ አማራ አስተሳሰብ ነው፡፡ አቶ በቀለ ገርባም የዚህ አይነት አስተሳሰብን ነው በኢሳት ቀርበው የነገሩን፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም ብለውም ይህንኑ አይነት አስተሳሰብ ደጋግሞው አንጸባርቀዋል፡፡

አቶ በቀለ ገርባ ቃል በቃ አማራ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰውን በደል “መካድ ቀጥሎ አብሮ ለመኖር በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል” ብለው ተናግረዋል፡፡ በአደባባይ እንዲህ ከተነገረ እንግዲህ በውስጣዊ ስብሰባ ምን ሊባል እንደሚችል መገመት ነው፡፡ ስናስበው በውስጥ ስብሰባ “አማራን አንገቱን በሜንጫ መቁረጥ ነው” እንደሚባል አንጠራጠርም፡፡ ለዚህ ጥርጣሬ ማስረጃው አቶ በቀለ አማራን አንገቱን እቆርጣለሁ ከሚለው የኦነጉ ፊታውራሪ አቶ ጃዋር አየር ማረፊያ ላይ እቅፍ አበባ ከመልካም መስተንግዶ ጋር የተበረከተላቸው መሆኑ ነው፡፡ ቀጣዩ የጃዋር ምክርም “በል አበባየን እንደወሰድክ ሜንጫየንም እንካ” የሚል ይሆናል ብለን እንጠረጥራለን፡፡

ግን አማራ እንዴት አሳዛኝ ፍጥረት ነው? ይሄ ሁሉ ቀልድ ገና ባልሞትነውና በቆምነው አማሮች ሁሉ የሚቀለድብን ምን አይነት ድንዛዜ ውስት ብንገባ ነው ግን? አርባ አመት ሙሉ የተቀለደበት ህዝብ፡፡ ለቀልዱ ሳቅ የሚያዋጡት የራሱ ልጆች የሆኑበት ህዝብ፡፡ ማንም የሚናገርለት እና የሚከራከርለት ያልነበረው ህዝብ፡፡ “የአማራም የራሱ ችግር አለበት እኮ” ብሎ የሚናገርለት አጥቶ የኖረ ህዝብ፡፡ በራሱ ልጆች የተከዳ፤ የተካደ አመድ አፋሽ ህዝብ፡፡ የዛሬው ተረኛ ቀልደኛ አቶ በቀለ ገርባ እንግዲህ ልክ እንደኦነግ ታሪክን የሚጀምሩት አጼ ምኒልክ ላይ ነው፡፡ ኦነግ ታሪክ ከአጼ ምኒልክ ዘመን ወደኋላ እንዳይሄድ ይፈልጋል፡፡ በተመሳሳይ እነዚህ ለስላሳ ኦሮሞዎች የሚባሉትም የታሪክ ጠርዛቸው ምኒልክ ላይ ነው፡፡ ይሄን ላሉበትም ሀሳባቸው አማሮች የሚበዙበት አካባቢ ፉጨትና ጭብጨባ እየጎረፈላቸው ነው፡፡ የንግግሩ ይዘትም አብረን እንድንኖር በግድ አማራ የሰራውን ስህተት ማመን እና ይቅርታ መጠየቅ አለበት፤ አለበለዚያ ዋ! ነው፡፡ ወደው አይስቁ አሉ፡፡

እኛ ቤተ አማሮአች ግን እንዲህ እንላለን፡፡ ኢትዮ-ኦሮሞ በአማራ ምድር ላይ የሚኖር ወራሪና ሰፋሪ ህዝብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው ኦሮሞ ትክክለኛ መጠሪያው ኢትዮ-ኦሮሞ ነው፡፡ ምክንያቱም የኬንያ ኦሮሞዎች አሉ፡፡ የሶማሊያ ኦሮሞዎች አሉ፡፡ የሯንዳ ኦሮሞዎች አሉ፡፡ የቡሩንዲ ኦሮሞዎች አሉ፡፡ ብዙም የማእከላዊ እና ምስራቅ አፍሪካ አገሮች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ኦሮሞዎች አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ኦሮሞ ምንጭ ናቸው፡፡ ከመካከለኛውና ከምስራቅ አፍሪካ ፈልሶ የመጣው ይህ ኢትዮ-ኦሮሞ የአማራን ምድር ሁሉ ታሪክ በፈጠረለት ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ወርሮ ያዘ፡፡ ወርሮ መያዙ ብቻ ሳይሆን በውስጡ የሚኖሩትን አማሮችና ሌሎች ነባር ነገዶች አጠፋቸው፡፡ እስካሁንም እያጠፋ ይገኛል፡፡ አሁንም አማራን ጨርሶ የመዋጥ ከፍተኛ ፍላጎት አለው፡፡ ይህንንም በፖለቲከኞቻቸው በኩል እያየን ነው፡፡ ዛሬ በቀለ ጨቋኝ የአማራ ገዥ መደብ የሚላቸው ሰዎች ኦሮሞን ከተበታተነበት የሰበሰቡና አንድ ያደረጉ፤ በኬንያ የሚኖረው ኦሮሞ ማንነቱና ባህሉ ሲደፈጠጥ የኢትዮጵያ ኦሮሞ ግን አሁን እስከሚኩራራበት እና ሌላውን ሊያጠፋበት እስከሚከጅልበት ታሪክና ማንነቱ አቆዩት፡፡ ይሄ ኢትዮ-ኦሮሞ ዛሬ የሚረገሙት አማሮች ባይሰበስቡት ኑሮ ከራሱ ከውስጡ በመነጨ ሁኔታ የመሰባሰብ እድል አልነበረውም፤ የመሰባሰብ ሀሳቡም አልነበረውም፡፡ ምክንያቱም የኦሮሞ ባህል ተበታትኖ ወደአፈተተው መንጎድ እንጅ መሰባሰብ ስላልሆነ፡፡ በተለይም አጼ ምንሊክ ኦሮሞን በማሰባሰብ እና አንድ ላይ በማድረግ ተወዳዳሪ የሌላቸው ባለውለታ ናቸው፡፡ ግን አማራ እጁ አመድ አፋሽ ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ውለታ መልሱ የተገላቢጦሽ ነው የሆነው፡፡

እንግዲህ በታሪክ በሚደረግ ሙግት ከሆነ እርቅም ሆነ ፍች የሚፈጸመው፤ ታሪክ መጀመር ያለበት ራሱ ኢትዮ-ኦሮሞ በአማራ ምድር መሀል ከተከሰተበት ታሪካዊ ጊዜ ላይ ነው፡፡ ታሪክን ሸርፎ ለራስ በሚያመች መንገድ ብቻ ቀንብቦ መተርጎም አይቻልም፡፡ ኦሮሞ ከ400 አመታት በፊት አማራን እና ሌሎች ነባር ነገዶችን ሲወር ብዙ ጉዳት አድርሶ ነው፡፡ አማራንና እነዚሁን ነባር ነገዶች በጭካኔ አጠፋቸው፡፡ የተረፉትን በግድ ኦሮሞ አደረጋቸው፡፡ የአማራን ስልጣኔ ሁሉ አወደመ፡፡ መሬቱን በግድ ወርሮ ያዘ፡፡ ስለዚህ አማራ ሳይሆን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት ኢትዮ-ኦሮሞ ነው፡፡ ኢትዮ-ኦሮሞ አማራን ይቅርታ መጠየቁ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ካሳ መክፈልም ይገባዋል፡፡ በአማራ ምድር በጉልበት ገብቶ እስካሁን ለኖረበት ካሳ ሊከፍል እና መሬቱን ለባለቤቱ እንዲመልስ ያስፈልጋል፡፡ መሬቱን መልቀቅ ካልቻለ ከእንግዲህ የሰፋሪነት ታክስ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ እስካሁን ለተገለገለበት እና አሁን እየተገለገለበት ላለው የአማራ ምድር ሁሉ ካሳ እና ግብር መክፈል አለበት፡፡ ከአራት መቶ አመታት በፊት እስከዛሬ አመት ተኩል ገደማ አምቦ ላይ እስካረዳቸው አማሮች ድረስ ካሳ መክፈል አለበት፡፡ ለ400 አመታት ላቃጠለው ገዳምና አብያተ ክርስቲያናት ካሳ መክፈል ይጠበቅበታል፤ ላወደመው ስልጣኔ ካሳ መክፈል ይኖርበታል፡፡ በጅምላ የዘር ማጥፋት ለፈጸመባቸው አማራ እና ሌሎች ነገዶች ካሳ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

ከአቶ በቀለ ገርባ ንግግር የምንረዳው ተጨማሪ ፍርደ ገምድልነት ይህ ነው፡፡ አማራ አርባ ጉጉና በደኖ ላይ ሲጨፈጨፍ ጽድቅ ነው፡፡ ያልነበረ በደል አማራ እንደሰራ ተደርጎ ሲሰበክ ኦሮሞ ይቅርታ ተጠያቂ ነው፡፡ በጣም የሚገርም! በጣም የሚያስቅ፡፡ እስከ አሁን ድረስ በኦሮሞ እጅ የፈሰሰው የአማራ ደም ከበደል አይቆጠርም ማለት ነው፡፡ ትክክለኛው ይቅርታ ሊጠየቅ እና ካሳ ሊከፈለው የሚገባው አማራው እንጅ አቶ በቀለ ገርባ እንደሚሉት ኢትዮ-ኦሮሞው አይደለም፡፡ እሳቸው ያንን የሚሉት ግን አማራ ተናጋሪ ድርጅትም ሆነ ሰው ስላልነበረው እንጅ እውነቱን ልባቸው ያውቀዋል፡፡

ኢትዮ-ኦሮሞና አማራ የሚያደርጉት ማናቸውም ክርክርም ሆነ ንግግር እነሱ ከተከሰቱበት የአጼ ልብነ ድንግል ዘመን ጀምሮ ነው መሆን የሚገባው፡፡ ከዛ ውጭ ፍንክች የለም፡፡ እነሱ የሚፈልጉት ዘመን ላይ ብቻ አይደለም ታሪክ የሚጀምረው፡፡ የአማራ ገዥ ሲጀመር ኦሮሞን በኦሮሞነቱ አልበደለውም፡፡ ይልቁንም ኢትዮ-ኦሮሞው በግፍ ወርሮ በያዘው መሬት ላይ በሰላም እንዲኖር፤ እንደዜጋ እንዲቀመጥ፤ በስልጣን ላይ ስልጣን እንዲይዝ፤ አማራው ያላገኘውን እድል መንገዶችና ፋብሪካዎች እንዲገነቡለት ነው ያደረገው፡፡ የአማራ መሪዎችም ሆኑ አማራ ኦሮሞን እንበድል ብለው እቅድ ይዘው፤ አስበውበት ያደረጉት አንዳች ነገር የለም፡፡ አማራ በኦሮሞ ላይ አደረሰ የሚባለው በሬ ወለደ እና ነጭ ውሸት ብቻ ነው፡፡ ይህ አይነት መሰረተቢስ ህዝባዊ ውንጀላም ለርካሽ የፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ የተጠነሰሰ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ሽህ ጊዜ ቢወነጀልና ቢከሰስ የአማራን ታሪካዊ ንጽህና አንዳች የሚያጎድፈው አይሆንም፡፡ በተቃራኒው አማራ ዘግናኝ በደሎች ሲፈጸምበት የኖረ ህዝብ ነው፡፡ በትክክል በደል እተየፈጸመብን ያለነው አማሮች እንኳ እስካሁን ደፍረን እገሌ ብሔረሰብ ጨቆነን አላልንም፡፡ የሚደርስብንን በደል በመታገሳችን ግን ጭራሽ እንደክፉ እና ጨቋኝ ነው የተቆጠርነው፡፡ ውሸትን ውሸት ብለን ባለመናገራችንም ይህ እስካሁን ሲፈበረክ የነበረው የውሸት ጸረ አማራ ውንጀላ ሁሉ ወደእውነት ሊቀየር ተቃርቧል፡፡

ባጭሩ የእነ በቀለ ገርባ እና የአንዳንድ የአንድነት ሀይሎች አላማ አሁንም በደርግና በወያኔ ቁም ስቅሉን ሲያይ የኖረውን አማራ ለሌላ ዙር መከራ ማመቻቸት ነው፡፡ ይህም በአማራ ላይ ቁማር መጫዎት እና አማራን ማክሰም የሚለው የቆየ ጸረ አማራ አጀንዳ ተቀጽላ ነው፡፡ ሲጀመር አንድ አገር ላይ አብሮ ለመኖር አንዱ በደለኛ አንዱ ንጹህ ተደርጎ በሚቀርብ የፖለቲካ ሸፍጥ አይደለም መሰረታዊ ንግግርና ክርክር የሚደረገው፡፡ ይህ ቅልብጭ ያለ አማራን እንደህዝብ እንደገና በሌላ ዙር የማንበርከክ ዘመቻ ብቻ ነው፡፡ የአቶ በቀለ ገርባ ንግግር አማራ ጨቁኖኝ ነበር ብቻ አይደለም፡፡ አሁንም እየጨቆነኝ ነውና ከአማራ ጭቆና ለመላቀቅ ነው የምታገለው ነው፡፡ ይህ ጥሬ ሀቅ እንግዲህ እንደቀላል የሚታይ አይደለም፡፡ ነገሩም የአንድ ሰው አቋም ብቻ ተደርጎ የሚወሰድ ሳይሆን የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ተጸንሰው የጎለመሱበት ጸረ አማራ አጀንዳ ነው፡፡

ቤተ አማራ ግን እስካሁን የነበረው አማራን ለሁሉም ነገር የመወንጀል እና የማንበርከክ ፍላጎት ጨዋታው ማብቃቱን አበክሮ ያሳውቃል፡፡ ሁሉም ከአማራ ትከሻ ላይ እንዲወርድ እና ወደፈለገው እንዲሄድ እንጠይቃለን፡፡ አማራን ጨቆነኝ ምናምን እያሉ ከመኖር የራስን እድል በራስ ወስኖ መሄድ ነው የሚያዋጣው፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ በአንድ አገርነት መቀጠልም አይቻልም፡፡ እስካሁን ለአማራው ስር ነቀል በሆነ ሁኔታ የሚናገርለት ስላልነበረ ብዙ ውሸቶች እና ስም ማጥፋቶች ሲፈጸሙበት ቆይተዋል፡፡ አሁን ግን እኛ ተነስተናል፡፡ ለህዝባችንም ድምጻችን ከፍ አድርገን እናሰማለን፡፡ ነጭን በውሸት ጥቁር ማድረግ አይቻልም፡፡ ጥቁር ጥቁር ነው፤ ነጭም ነጭ ነው፡፡

አማራ የሆንክ ሁሉ ብትነቃ ነው የሚሻልህ፡፡ ሁሉም አንተ ላይ ነው ጣቱን የሚቀስረው፡፡ አንተ ራስህ የጥፋት አደጋ ተደቅኖብህ ባለበት ሰአት ሌላው ካንተ ነጻ ለመውጣት ነው እየታገለ ያለው፡፡ ከራስህ በላይ ዘመድ የለህምና ለራስህ ቁም!

ድል ለአማራ ህዝብ
ቤተ አማራ

Comments are closed.