ይድረስ በመላዉ አለም ላላችሁ የመኢአድ ደጋፊዎች !!!

ይድረስ በመላዉ አለም ላላችሁ የመኢአድ ደጋፊዎች:-

(ከለገሰ ወልደሃና:- የመኢአድ ም/የህዝብ ግንኙነት)
==================
ጉዳዩ:- እስኪ በሉ ኑ ሰለ መኢአድ እንወቃቀስ::እናንተ እኛ ላይ ወቀሳ አላችሁ? እኛ እናንተ ላይ ወቀሳ አለን !
ወያኔ ዘንድሮ በመኢአድ ላይ ጨከነችበት:: መኢአድ ካልጠፋ ብላ መኢአድን እየቀጠቀጠችዉ ነዉ:: አባላትና አመራር እንደጉድ ይታሰራሉ:: ይቀጠቀጣሉ:: መኢአድ ላይ እየወረደ ያለዉ ዱላ ማንም ፓርቲ ላይ አልወረደም:: ያም ሆኖ መኢአድ እንደ ብረት የነጠሩ አባላትና አመራር ስላሉት ኢትዮጵያን ነጻ እስኪያወጣ ሳያወላዉል የሚታገል ፓርቲ ነዉ:: ወያኔ ግን መኢአድን ለማጥፋት ያላት ጭካኔ ተነግሮ አያልቅም::
ቢሆንም ከወያኔ ጭካኔ ይልቅ እዚያ አሜሪካ: አዉሮፓ: እና በመላዉ አለም ተበትናችሁ የምትገኙ የመኢአድ ደጋፊዎችና አባላት ጭካኔ አናዶናል:: አስገርሞናልም::
በመላዉ አለም በየቤታችሁ ተደብቃችሁ ያላችሁ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎችን ጭካኔ የሚስተካከል ጭካኔ ከቶስ ይኖር ይሆን? በዚህ በቀዉጢ ቀን እንዴት ከመኢአድ ትሸሻላችሁ? ምን ሆናችሁ ነዉ እንዲህ አያገባንም ብላችሁ በየስርቻዉ ተወሽቃችሁ ጀግኖች በትግል ሜዳ ላይ ሲዋደቁ ድርጅቱን ለመርዳት የፈራችሁ? እንቢስ ያላችሁት? ወኔስ ያጣችሁት? እኮ ምክንያታችሁ ምንድን ነዉ?
እዚህ ሀገር ቤት ያለን የመኢአድ አባላት በእውነቱ በጣም በጣም ነው ያዘነዉ:: ቆይ እኛ ምን እስክንሆን ነው የምትጠብቁት? ተራብን ! ታረዝን! ተሰቃየ! ታሰርን! ተደበደብን! ተንካራተትን! አመራሮቻችን ምርጡን መሪያችንን ማሙሸት አማረን ጨምሮ በሀሰት ታሰሩብን:: በርካታ መሪዎቻችን እስር ቤት ዉስጥ እየተቀጠቀጡ ነዉ:: አባላሎቻችን እስር ቤት ናቸው:: ቤተሰባቸው ለረሀብ ተዳርገዋል::
አብዛኛው የኛ አባል እስር ቤት ውስጥ ጠያቂ የውም:: የለበሱት ልብስ እላያቸው ላይ አልቇል:: በወር ውስጥ የሚጠይቅ አንድ ሠው የሌላቸው ናቸው:: እኔም ሆንኩ አንዳንድ ሰዎች እስር ቤት እንዳንሄድ ያለው ነገር ይታወቃል:: እንደዛም ሆኖ አልፎ አልፎ እየሄድን እየጠየቅናቸዉ ነዉ:: እስር ቤት ብንሄድም እኛም መናጢ ድሆች ነን:: እኛ ለምንወደዉ ሀገራችን ህይወታችንን እና ነብሳችንን አሳልፈን ሰጥተናል:: ሆኖም በድህነታችን ዉስጥም ሆነን ልናደርግ የሚገባውን የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እሞከርን ነው::
የታሣሪን ቤተሰብ ስልክ ደውሎ የማያጽናና ደጋፊ እንኳን አንድም የለም:: ከመኢአድ ደጋፊዎችና አባላት ይልቅ እኔ ፌስቡክ ላይ የማውቃቸው ሰዎች ብዙ ነገር አድርገዋል:: አንዳንድ የታሳሪ ቤተሰብን እየረዱ ነው::
እናንተ በመላዉ አለም የተደበቃችሁ የመኢአድ አባላትና አመራሮች ቢያንስ እንዴት ስልክ መደወል እና የታሳሪ ቤተሰቦችን ማጽናናት አቃታችሁ ? እንዴት ገንዘብ አሰባስባችሁ የመኢአድ አባላትን ከእስር ቤት ለማስፈታት መረባረብ አቃታችሁ? እጅግ አፍረንባችኋል::
ለመኢአድ አባላት ትናንት ከተፈጠሩ ድርጅቶች አባላት ልብስ እየለመኑ መልበስ ሞት ነው:: እናንተ በመላዉ አለም ያላችሁ የመኢአድ ደጋፊዎችና አባላት አንዳንዶቻችሁ በሞቀበት ከበሮ ትመታላችሁ:: አንዳንዶቻችሁ እርስ በእርስ ተጠላልታችሁ መኢአድን የግለሰብ ጉዳይ አድርጋችሁታል:: አንዳንዶቻችሁ መኢአድን ከግለሰቦች ዝና ጋር አሽቀንጥራችሁ ጥላችሁታል::በመላዉ አለም ያለዉ የመኢአድ ደጋፊ እርስ በእርሱ ለመነጋገር የከበደዉ ምንድን ነዉ? እርስ በ እርሳችሁ ነብስ አልተጠፋፋችሁ:: ለምሆኑ ነገ ሀገር ሊመራ የሚዘጋጅ ፓርቲ ዉስጥ ያላችሁ ሰውች ይቅርታ መባባል ካልቻላችሁ ነገ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እንዴት አብሮ መስራት ይቻላል?
እንዴት አልገባ አላችሁ ጃል? የምርጫ 97 የመሰረት ድንጋይ የሆን እኛ ነን:: በማላዉ ሀገሪቱ ለሚንቦለቦለዉ ትግል መሰረቶች እኛ ነን:: ሁለ የተዉእለደዉ ከመኢአድ ማህጽን ነዉ:: እናንተ ደግሞ ገና አንዳንድ ሚዲያ አግኝቶ ከበሮ ካስደለቀ ጋር አብራችሁ ከበሮ የምትመቱ ሰዎች ነገ መኢአድ በዚህ መከራ ዉስጥ አልፎ ወደ ጠንካራ ደረጃ ቢመጣ ከለ እኛ እንደምታጨበጭቡ እናቃላነ::
አንዳንዶቻችሁ ስላዋጣችሁት መቶና ሁለት መቶ ዶላር እንደ ቁምነገር ታወሩታላችሁ:: እኛስ ምን እንበል? ህይወታችንን ለጨካኞች አሳልፈን ሰጠተን አይደል እየታገልን ያለንዉ:: እስኪ በአለም አቀፍም ሆነ በኢትዮጵያ እትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር:: አንድ መንግስት : አንድ ህዝብ: አንድ ሀገር ብሎ በግልጽ መፈክር ከወያኔ ጋር ለሃያ አምስት አመታት የታገለ ፓርቲ ማን ነዉ? ማንም የለም:: ብዙዉ አፋዳይ እና አረብራቢ ነዉ:: ግማሹ የብሄር ፖለቲካን በግማሽ ተቀብሎ ኢትዮጵያን በድርበቡ አዉቆ ንግድና ፕሮፖጋንዳ የሚሰራ ነዉ:: ዛሬም ደረታችንን ጠፍጥፈን ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና ዲሞክራሲ በጠራራ ጸሀይ እየተገደልን ያለን እኛ መኢአዶች ነን:: በርግጥ እንዳንዳንድ ነጋዴዴ ፓርቲዎች ማድረግ ያልቻልነዉ አንድ ነገር አለ:: ብዙ ማዉራትና ፕሮፖጋንዳ:: ብልጠትና የፖለቲካ ንግድ:: ቢሆንም አናደርገዉም:: ኢትዮጵያን እንወዳታለን:: እንደወደድናት እንሞታለን:: በቃ:: የሚረዱን ይረዱና:: የማይረዱን ተነጥከዉን ይሄዳሉ:: ግን ጊዜ አንድ እዉነት ይነግራቸዋል:: ይሄዉም የ እኛ የትግል ጽናት ፍሬ ሲያፈራ ያሳያቸዋል::
ኑ ቅረቡ ስህተት ካለብን ቀርባችሁ ማርምና ማስተካከል ነዉ እንጅ እንደቦና ዝናብ አሉ መቱ ማለት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ቢያምጡት ጤዛ የማያመነጭ አካሄድ ነዉና እራሳችሁን አርማችሁ ወደ ትግል ሜዳ ትመለሱ ዘንድ መኢአድ ጥሪ ያቀርባል:: የጀግና ሰ ዓቱ አሁን ነዉ:: ፓርቲዉን ማዳኛዉ ሰዓቱ አሁን ነዉ::
እስኪ በሉ ኑ ሰለ መኢአድ እንወቃቀስ::እናንተ እኛ ላይ ወቀሳ አላችሁ? እኛ እናንተ ላይ ወቀሳ አለን !
አትፍሩ: አትሽሹ: አትጠራጠሩ:: ትግሉ እሞቀበት በማድራት ለዉጥ የሚያመጣ ሂደት የለዉም:: መኢአድ ዛሬም ነገም በርሃብና መመክራ ዉስጥ እየተራመዱ ለዉጥ የሚያመጡ አመራሮችና አባላት አሉት:: ግን በዉጭ ያላችሁ ደጋፊዎቻችን ላይ ቅሬታ አለን:: ይሄን ቅሬታዬን ጽፌላችኋለሁ:: የሁላችሁም አድራሻ ስለሌለኝ አንድኛችሁ ላንድኛችሁ እንድታስተላልፉት አደራ እላለሁ:: የምትወቅሱን ነገር ካለ ጻፉልን::
ደጋፊና አባል ማለት እኮ በመከራ ሰዓት ነዉ አለኝታነቱን የሚያሳዬዉ:: እናንተ ግን መኢአድ ሲዳከም አይታችሁ ሸሻችሁን:: ለምን? መኢአድ ሲጠናከር ልትጠይቁን? መኢአድ ሲበረታ ልትደግፉን? ልታዉቁት የሚገባዉ ነገር በዚህ በመከራ ወቅይት እንኳን መኢአድ በኢትዮጵያ ካሉ ፓርቲዎች ሁሉ በርካታ አባላት ያለዉ ፓርቲ ነዉ:: በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ አባላት የቁሳቁስ አቅም ስለሌለዉ ነዉ እንጅ አሁንም ከመኢአድ ጋር ሙጭኝ ብሎ ለትግል እስከመጨረሻዉ እራሱን አሳልፎ የሰጠ ሀይል ነዉ:: እናንትስ ? ምን ሆናችሁ?
ለገሰ ወልደሃና