ትግሬ እንዳይቀየም አማራ ይሙት (ሄኖክ የሺጥላ)

ትግሬ እንዳይቀየም አማራ ይሙት ( ሄኖክ የሺጥላ )

ፖለቲካ አስቀያሚ ነገር ነው ፣ ምክንያቱም ውሸታም ስለሚያደርግ ። እውነት እና ፖለቲካ ተዋውቀው የሚያውቁም አይመስለኝ ። እንደው ሳስበው ማለት ነው ። ባንድ ወቅት እጅግ የምወዳቸው ታላቁ ምሁር መስፍን ወልደማርያም ፣ ከአንድ የትግራይ ተወላጅ የኔ-ቢጤ ( ለማኝ ) ጋ ስላደረጉት ጨዋታ የጻፉትን እና የተሰማቸውን ሳነብ ፣ ምናለ እኔንም እንደሳቸው አንድ የትግሬ ለማኝ አጋጥሞኝ ትግሬ ሁሉ በዚህ ስርዓት ተጠቃሚ አለመሆኑን የሚያሳይ ጽሑፍ በጻፍኩ ብዬ ነበር ። ግን ፣ግን የምኖረው አማሪካ ነውና ፣ የምኖርበት አማሪካ ትግሬ ባይጠፋም ( አረ እንደውም ብዙ አለ ። ደሞ ብዙ ብቻ አይደለም ፣ ማንነትህን ለማወቅ <> ወይም ደሞ <> ሁሉ ይሉሃል ። ቼክ ፖይንት መሆኗ እኮ ነው ! እና ያለሁበት አማሪካ ትግሬ ቢኖርም ፣ በግልጽ በአደባባይ እንደሀገራችን ጨርቁን አንጥፎ የሚለምን የትግሬ ለማኝ አጋጥሞኝ አያውቅም ። አለመታደል ነው !

አዎ እንደነገርኳችሁ ፖለቲካ አስቀያሚ ነገር ነው ። አስቀያምነቱ ደሞ ፣ የሚሰማህን ደብቀህ ፣ የማይሰምን የምትናገርበት ዓለም ስለሆነ ። ለዚህም ይመስለኛል ፣ ፖለቲካ እና እባብ ከልጅነቴ አልወድም ። እፈራለሁ አላልኩም ! ምክንያቱም እውነት ስናገር ብቻ እንደሚያምርብኝ ስለማውቅ ! እውነት ብዬ የምለው ራሱ አንጻራዊ እንደሆነ ሁሉ !

ዛሬ ትግሬ እንዳይቀየም እንዴት አማራ ይሙት እያልን እንደኖርን ትንሽ ለመጻፍ ተገደድኩ ። አውጥቼ አውርጄ ፣ የነገሩን አሳሳቢነት መዝኘ ፣ እንዴት ብጽፈው ልክ ይሆናል ብዬ ተጨንቄ አይደለም የምጽፈው ። መነሻዬ ማንነታችን ነው ፣ መድረሻዬ ማንነት አልባነታችን ነው ። ስለዚህ ብዙ መጨነቅ አይጠይቅም ።

ሁላችሁም እንደምታውቁት ህወሓት አማራን ለማጥፋት ጫካ የገባ ድርጅት ነው ። ከተማ ቁጭ ብሎም ፣ ለ 25 አመታት አማራን እንዴት ማጥፋት እንዳለበት ሲዶልት እና ዱለታውን ሲተገብር የኖረ ፣ እስካለ ድረስም የሚኖር ድርጅት ነው ። ህወሓት ትርጉሙ ( ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ) ማለት ሲሆን ከስሙ እንደምንረዳው የትግራይ ነጻ አውጪ ማለት ነው ። ይህ እኩይ ቡድን ይሄንን ስሙን ዝም ብሎ ከጉም ላይ መዞ ያወጣው ስም አይደለም ። ለዚህ ስም ዘብ የቆሙ ፣ ;አዚህ ስም ራሳቸውን የሰው ፣ የሚሰው የትግራይ ልጆችን ከጀርባው አሰልፎ እንጂ ። ይሄ ሐሰት ነው የምትሉ ከሆነ ፣ ለምን ሐሰት እንደሆነ አስረዱን ። ካቃታችሁ ደሞ ያው እንደለመዳችሁት ስደቡን ። እኛ በይሉኝታ የምንሞት ፣ በይሉኝታ የምንታረድ ፣ በይሉኝታ የምንሰቃይ ፣ ዋጋ ቢስ ህዝቦች ስለሆነን ይገባናልና !

የሆነው ሆኖ የኛን ፖለቲካ ሳስበው አንዳንዴ <> አይነት ነገር ይመስለኛል ። ለነገሩ ምናለበት አማራ ቢሞት ! አማራ እንደሁ ጨቋኝ ነው ። ምናልባት ማርክ ትዋይን ( ወይም ሳሙዔል ክሌመንትስ ) አማራ ቢሆን ኖሮ እንዲህ ብሎ ይጽፍ ነበር ።

አማራ ነኝ! አማራ በመሆኔ ብቻ ጨቋኝ የመሆን የማይገሰስ መብት አለኝ ፣ አማራ ነኝ ፣ እየራበኝ <> ተብዬ ስሰደብ ያለ አንዳች ጥርጥር <> ብዬ ራሴን የምጠይቅ ፣ አማራ ነኝ ፣ በተወለድኩበት እንዳልኖር ፣ ሀገሬን እንድከዳ ፣ ማንነቴን እንድጠላ ፣ ደግሞ ደጋግሞ ገዳይ እንደሆንኩ የሚነገረኝ ። እውነት ይሆን ? ገዳይ እሆን ብዬ የገደልኩት እሬሳ ለማየት ስወጣ ፣ የሞተው የኔው የራሴ ልጅ ነው ። ፊውዳል ነህ! የሚሉትን ሰምቼ ፣ ከተራራው ጫፍ ላይ ወጥቼ ሃገሩን ሳማትረው ፣ መሬቱም ፣ አድባሩም ፣ አንዱም እኔን አያውቀኝም ።
ታዲያ እኔ ከሆንኩ ጨቋኝ ፣ እኔ ከሆንኩ ገዳይ ፣ የገደልኳቸው የት ገቡ ? የሚል ይመስለኛል ።

እና ዛሬም አማራ ሲፈናቀል ፣ አማራ ሲገደል ፣ አማራ ሲራብ ፣ አማራ የማምከኛ መርፌ ሲወጋ ፣ እውነቱን ብናውቀውም ፣ ትግሬ ያስቀይምብናልና ፣ ዝም እንበል ! አዎ ትግሬ ከሚቀየም አማራ ይሙት ! ይህ እኛ ነን ! ይህ ሰው መሆን ያቃተው አማራ ስብእና ነው ።

ለዚያ ነው ፖለቲካ የምጠላው ። ፖለቲካ ለኔ ለሄኖክ የሺጥላ አይሆንም ። ፖለቲከኞቻችን ይህንን ጉዳይ ዘረኝነት ነው ይሉታል ። እኔ ደሞ አድር ባይነት ነው እለዋለሁ ። ማስመሰል ነው ። አማራው ከትግሬው ጋ ተከባብሮ እና ተፋቅሮ ነው የሚኖረው የምትሉት የትግራይ ልጆች ፣ እናንተ ዘብ በቆማችሁለት ስርዓት ፣ አማራው ቀኖረብት ሲፈናቀል ምን አላችሁ ? ምን ልትሉ ! እናንተ ምን አጠፋችሁ ። ጥፋቱ ያለው <>። የሚበቃ ይመስለኛል ። ወይ አብረን ፣ እኩል ሆነን እንኖራለን ። ወይም አብረን እንጠፋለን ። እኔ በበኩሌ የትግሬ ለማኝ ፈልጎ ለማግኘት ጊዜ የለኝም ። የትግሬ እውነተኛ እንጂ !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.