ሰበር ዜና፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ

ፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡

የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በነፃ የተሰናበቱት፣ የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል፡፡

በውሳኔው መሠረት አቶ ሀብታሙ የሚጠየቁበት ወይም ሌላ የሚፈለጉበት ጉዳይ ከሌለ በዛሬው ዕለት እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ወስኗል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.